Skip to main content
King County logo

ቤስት ስታርትስ ፎር ኪድስ/ምርጥ ጅምር ለህጻናተ ወደ ስድስተኛ ዓምቱ እየገባ ነው እናም በመላው ኪንግ ኮውንቲ ውስጥ ባሉ ማህበረሰቦች ውስጥ ኢንቬስት ማድርጋችንን እንቀጥላለን። የቤስት ስታርትስ ፎር ኪድስ/ምርጥ ጅምር ለህጻናተ የትሰኝው የዳሰሳ ጥናት የልጆቻችን ክፍተኛ ጥንካሬዎች እና ፍላጎቶች እንዲሁም በማህበርሰባችን ውስጥ የተከሰቱ ለውጦችን እንድንገነዘብ ይረዳናል። ወላጅ መሆን ጠንክሮ መስራትን ይጠይቃል። እንደወላጅ ፡ የልጅ ጤንነት የጤናማ ቤተስብ ጥንካሬ እንዲሁም የማህበረሰብ ድጋፍ ተሞክሮዎ የእርሶንም ልጆች ጨምሮ በኪንግ ካውንቲ ውስጥ የሚግኙት ልጆች ደስተኛ እና ጤናማ ሆነው እንዲያድጉ እንደሚረዳ ተስፋችን ነው። 

ቤስት ስታርትስ ፎር ኪድስ/ምርጥ ጅምር ለህጻናተ የተሰኝ ጤንነትን የተመለከተ የዳሰሳ ጥናት ምንድን ነው? 

 • በኪንግ ኮውንቲ ውስጥ ስለትንንሽ ልጆች እና ስለቤተሰቦቻቸው ጤንነት ሁለተናዊ ደህንነት ጥንካሬ እና ፍላጎት ለማወቅ የሚደረግ የዳሰሳ ጥናት ነው። 

 • የልጆች የጤና ዳሰሳ ጥናቱ የሚያተኩረው በኪንግ ኮውንቲ ይሚኖሩ እና የመጀመሪያ ደርጃ ትምህርት ቤት ወይም ከዚያ በታች ያሉ ልጆች ያሉዋቸውን ቤተሰቦች ላይ ነው። 
 • የልጆች የጤና ዳሰሳ ጥናቱ ስለልጆች ጤንነት ይጠይቃል። ለምሳሌ፦ 

ስለል ሁለተናዊ ደህንነት 
ስለጤናማ ክብደት 
ስለማህበረሰብ ድጋፍ 
ስለወላጅና የልጅ ግንኙነት 
ስለአካል ብቃት እንቅስቃሴ
ስለመሰረታዊ ፍላጎቶች 
ስለጡት ማጥባተ 
ስለትምህርት ቤት ተሞክሮ 
ስለቤተሰብ ጥንካሬ 
ይቅድመ ልጅነት ተሞክሮ  
ስለልጆች እንክብካቤ እና ከት/ቤት በኃላ ስላለ እንክብካቤ
ስለወላጅ ድጋፍ  

 

Best Starts for Kids Health Survey

ማን ሊሳተፍ ይችላል? 

 • በኪንግ ኮውንቲ የሚኖሩ እና የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ልጆች ያላቸው ወላጆች በ2021 መጀመሪያ ላይ የልጆቹን የጤና የጥናት ዳሰሳ እንዲወስዱ ተጋብዘዋል። የጥናት ዳሰሳው ከዚህ ቀጥሎ በተዘረዘሩት 7 ቃንቃወች ተስጥቶል ። በእንጊሊዘኛ በቻይኒስ በኮሪያን በራሻን በስፓኒሽ በሱማሌኛ እና በቬትናሚስ። 

 • ከጀንዋሪ - ማርች 2021 15000 ለሚሆኑ በኪንግ ካውንቲ የሚኖሩ ወላጆች ወይም ሞግዚቶች በዘፈቀደ እንዲሳተፉ ይመረጣሉ ። ቤተሰቦ ክተመሪጠ የልጆችን ጤንነት በተመለክተውን የዳሰሳ ጥናት እንዲሞሉ የሚጋብዝና እንዴት እንድሚሞሉ ይሚገልጽ ደብዳቤ ይደርሶታል። 

 • ከኤፕሪል - ጁን 2021 የልጆች ጤና የዳሰሳ ጥናቱ የሽ

ቤስት ስታርት ፎር ኪድስ ከዩንቨርስቲ ኦፍ ዋሽንግተን የሶሻል ወርክ ዲፓርትመንት ጋር በመተባበር የልጆች ጠንነትን የተመለከተውን የዳሰሳ ጥናት ያከናውናል። በዳሰሳ ጥናቱ ላይ የሚሳተፉ ተሳታፊወች በስልክ በደብዳቤ እንዲጋበዙ ይደረግና የዳሰሳ ጥናቱን በኦላይን በስልክ ወይም በወረቀት እንዲሞሉ ይደረጋል። 

ለምን መሳተፍ ይኖርብኛል? 

 • የእርሶ ድምጽ አስፈላጊ ነው። 

 • በልጆች የጤና ጥናት ዳሰሳ በኩል በወላጆች የተሰጠው መረጃ መራጮችቤስት ስታርት ፎር ኪድስ የተሰኝውን ተነሳሽነት እንዲያጸድቁ አቅጣጫ ይመራቸዋል።  

 • ቤስት ስታርት የአናተን ጨምሮ እያንዳንዱ ልጅ በህይወቱ ውስጥ ስኬታማ ለመሆን ምርጥ እድል እንዲኖረው ያረጋግጣል። 
 • የልጆች የጤንነት ዳሰሳ ጥናት በመላው ኪንግ ካውንቲ የተለያዩ ባህሎች እና ቃንቃዎች መካከል በማህበረሰብ ውስጥ ያሉትን ታላላቅ ጥንካሬወች እና ፍላጎቶች እንድንገነዘብ ይረዳናል። 
 • ቤስት ስታርት ፎር ኪድስ ከልጆች ይጤና ዳሰሳ ጥናት የተማረውን በብሎግ እና በድረ ግፁ ላየ ያካፍላል።
 • የዳሰሳ ጥናቱ በኪንግ ካውንቲ ያሉ ልጆች ጤና ላይ ለወጥ እያመጣን መሆናችንን ለመከታተል ከጊዜ ወደ ጊዜ ይቀጥላል። 
 • ተሳትፎዎ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ነው እናም ማንኛውንም ጥያቄ መዝለል ወይም በማንኛውም ጊዜ ጥያቄዎችን መመለስ ማቆም ይችላሉ። 

ልጄ እንዴት ነው በዘፈቀደ ሊመረጥ የሚችለው? 

 • ለቤተሰብዎ ደብዳቤ ከተላከ ልጅዎ እንዲሳተፍ ተመርጡዋል ማለት ነው። 

  • የልጅዎ ስም እና የወላጆቻቸው/የአሳዳጊዎቻቸው የግነኙነት መረጃ በዋሽንግተን እስቴት የጤና መመሪያ እና ከኪንግ ካውንቲ ይሕዝብ ትምህርት ቤት ዲስትሪክት ጋር በመተባበር በሲያትልና በኪንግ ካውንቲውስጥ ደህንነቱን በጠበቀ ሁኔታ ተሰብስቦል። 
  • በዘፈቀድ መመሪጡ በኪንግ ኮውንቲ ውስጥ የሚኖሩ ትንንሽ ልጆ/ ች ያላቸውን ቤተስቦች ሀሳብና ልምዶችን ለማንፀባረቅ የተሻለ እድል ይኖራል። 

ጥናቱ የእኔን መረጃ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ሚስጥራዊ እንዲሆን የሚያደርገው እንዴት ነው? 

 • ሁሉም መልሶች ማየት ይሚችሉት ሚስጥራዊ ከሆኑ መረጃዎች ጋር ለመስራት ፈቃድ ያላቸው የሰለጠኑ ሰራተኞች ብቻ ሲሆኑ ደህንነቱ የተጠበቀ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ሁሉም መረጃዎች በጥንቃቄ የቀመጣሉ።
 • ምላሾችን በሚስጥር ለመጠበቅ የልጆች ስም ተወግዱዋል። የተግኙ ውጤቶችን ብቻ ተጨምቆ በይፍ ይጋራል። ማንም ቤተሰብ ወይም ግለሰብ ተለይቶ ሊታወቅ አይችልም። መረጃውም የሚሰበሰበው ለቤስት ስታርት ፎር ኪድስ ፕሮግራም ብቻ ነው። 
 • መርጃዎ በበይነመረቡ/በኢተርኔት ለማቅረብ ደህንነቱ የተጠበቀ ነው። ሁሉም የዳሰሳ ጥናት መረጃዎች የተሰበሰቡት ጥብቅ የደህንነት እና ይምስጥር ደረጃዎችን በመጠበቅ ነው። 
 • እኛ የእርሶዎንም ሆነ የልጅዎን ከዚህ በታች ያሉትን መርጃዎች አንጠይቅም
  • የሶሻል ሴኩሪቲ ቁጥር 
  • የክሬዲት ካርድ መረጃ 
  • የባንክ እካውንት መረጃ 
  • ገንዘብ ወይም እርዳታ 

ለበለጠ መረጃ ከዚ በታች ያለውን መረጃ በመጠቀም ጥያቄዎን ማቅረብ ይቻላሉ 

ኢትዮጵያ አለምነህን  - Ethiopia Alemneh
(206)788-7576

Amharic.BSK@KingCounty.gov

 

Contact Us

Phone 206-263-9105

TTY Relay: 711

Fax: 206-296-5260