Skip to main content
King County logo

ደረጃ 3: ኣሁን የምግብ ቤቶችና ሱቆች ተጨማሪ ደምበኞች ማስተናገድ ይችላሉ

ኪንግ ካውንቲ፡ ከጤናማ ዋሽንግተን (Healthy Washington) ምድቦች በደረጃ 3 ይገኛል - መልሶ የመቋቋም ዕቅዱ፡ ተጨማሪ እንቅስቃሴዎች እንደድሮ እንዲጀምሩ ይፈቅዳል። እንደ ፕሮፈሽናልና የኮሌጅ ስፖርቶች በኣካል ሂዶ መመልከትን ያጠቃልላል። የንግድ ቦታዎች፣ ምግብ ቤቶች፣ የኣካል ብቃት እንቅስቃሴ ቦታዎችና (ጂም) ቤተ መዘክሮች በኣንድ ግዜ የሚያስተናግዱትን የሰው ብዛት ዓቅም ከ 25% ወደ 50% ከፍ ይላል።

ስለ Healthy Washington plan ተጨማሪ መረጃ ለማግኘ (የገዢው ጤናማ ዋሽንግተን ድህረ-ገጽ) Governor's Healthy Washington site ይጎብኙ።

ኣዲስ እና ከፍተኛ የተላላፊነት ዓቅም ያላቸው የቫይረሱ መልኮች በምንገጥምበት ግዜ የንግድ ተቋማት ክፍት ሆነው እንዲቆዩ እና የኮቪድ ክስተቶች እያሽቆለቆሉ እንዲሄዱ ከመቸውም በበለጠ ንቁ ሆነን እንድንጠብቅ ይኖርብናል። በደምበ የሚገጥም  የፊት መሸፈኛ  ከመልበሳችን እና ከሌሎች ያለን ርቀት ከመጠበቃችን በተጨማሪ፡ ህንፃ ውስጥ ኣገልግሎት የሚሰጡ የንግድ ተቋማትና ድርጅቶች ለ ቨንቲሌሽን እና የኣየር ዝውውር፣ ከህንጻ ውጭ እንዲሁም ቴክ ኣውት እና የደጅ ኣፍ(curbside) ኣገልግሎት ላይ ትኩረት እንዲሰጡ ስያትል እና ኪንግ ካውንቲ - ሕዝብ ጤና ያበረታታል።

ለስራ ቦታኮሚዩኒቲና እምነትን መሰረት ያደረጉ ማሕበራትትምህርት ቤቶችና መዋዕለ ሕጻናት የሚበጁ የፋንናንስና ዳግም ስለመከፈት እገዛና የመረጃ ምንጮች ይህንን ድህረ-ገጽ ይጎብኙ።

ክፍት የሚሆነው ምንድን ነው?

ደረጃ 3 - ጤናማ ዋሽንግተን (Healthy Washington)

ዝርዝርመመሪያውንይህንን ድህረ-ገጽያንብቡ (እንግሊዘኛ ብቻ).

መጋቢት 22ተሻሽሎ የቀረበ

እንቅስቃሴዎች

ደረጃ 3


ማህበራዊ እና መኖርያ ቤት ውስጥ የመሰባሰብ መጠን - ሕንፃ ውስጥ

ኣብሮዎት የማይኖሩ ሰዎች ከ 10 መብለጥ የለባቸውም

ማህበራዊ እና መኖርያ ቤት ውስጥ የመሰባሰብ መጠን - ሕንፃ ውጭ (outdoor)

ከ 50 ሰው የማይበልጥ

የኣምልኮ ኣገልግሎቶች

ሕንፃ ውስጥ - ከሕንፃው ዓቅም 50% ያልበለጠ

የችርቻሮ ሱቆች (የአርሶ አደሮችን ገበያዎች ፣ የምግብ ሸቀጣሸቀጦች እና ምቹ መደብሮች ፣ ፋርማሲዎችን ያጠቃልላል)

ከተቋሙ ዓቅም 50% ያልበለጠ። የደጅ-ኣፍ ኣገልግሎት (curbside pick-up) እናበረታታለን

የባለሙያ ኣገልግሎቶች

ከሩቅ መስራት በጥብቅ እናበረታታለን፣ካልተቻለ ከተቋሙ ዓቅም ከ50% ያልበለጠ

የምግብና የመጠጥ ተቋማት (ለ 21+ ዕድሜ ብቻ ኣገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት - የምግብ ኣገልግሎት ዝግ ሆኖ ኣይቀርም)

ከሕንፃ ውስጥ ሆኖ መመገብ ኣለ - ከተቋሙ ዓቅም ከ 50% ያልበለጠ፡ የኣልኮሆል ኣገልግሎት/ኣቅርቦት 12 AM ይቁም። ከሕንጻ ውጭ ወይም ክፍት ኣየር (open-air) ሆኖ መመገብ ፡ - በጠረጴዛ ቢበዛ 10 ሰው።

ሠርግና የቀብር ስነ-ስርዓት

የበዓል ስነ ስርዓቶችና የሕንፃ ውስጥ እንግዶት፣ ፍትሓት ወይም ተዝካር፣ ወይም ከሁኔታው ተሳስረው የሚሄዱ ተመሳሳይ ስብስቦች ተፈቅደዋል፡ ተገቢ የቦታው መስፈርቶችን ግን መከበር ኣለባቸው። የምግብና የመጠጥ ኣገልግሎት የሚቀርብ ከሆነ ለምግብና መጠጥ ቦታዎች የወጡ መስፈርቶች መከበር ኣለባቸው። መደነስ ክልክል ነው።

የሕንፃ ውስጥ መዝናኛ እና የኣካል ብቃት እንቅስቃሴ ተቋማት (ጂም፣ የኣካል ብቃት ድርጅቶች፣ የሕንፃ ውስጥ መዝናኛ ስፖርት፣ የሕንፃ ውስጥ መዋኛ፣ የሕንፃ ውስጥ K-12 ስፖርት፣ የሕንፃ ውስጥ ስፖርት፣ የሕንፃ ውስጥ የግል ማሰልጠኛ፣ የሕንፃ ውስጥ ዳንስ፣ ንክኪ የሌለበት ማርሻል ኣርት፣ ጂምናስቲክ፡ ክላይምቢንን - climbing) ያጠቃልላል።

በሁሉም የአደገኛ ምድቦች ውስጥ የተፈቀ የስፖርት ውድድሮች የኣካል ብቃትና ስልጠና እንዲሁም የሕንፃ ውስጥ ስፖርት ከሕንፃው ዓቅም 50% ያልበለጠ። የሰውነት መታጠብያ (Showers) ተፈቅደዋል።

ከሕንፃ ውጭ (outdoor) ስፖርትና የኣካል ብቃት ተቋማት (ከሕንፃ ውጭ የኣካል ብቃት ተቋማት፣ ከሕንጻ ውጭ የመዝናኛ ስፖርት፣ ከሕንፃ ውጭ መዋኛ፣ ከሕንፃ ውጭ መናፈሻዎችና የእግር ጉዞ መንገዶች (parks and hiking trails)፣ ከሕንፃ ውጭ ካምፖች (campsites)፣ ከሕንፃ ውጭ K-12 ስፖርት፣ ከሕንፃ ውጭ ስፖርት፣ ከሕንጻ ውጭ የግል ማሰልጠኛ፣ ከሕንጻ ውጭ ዳንስ፣ ከሕንፃ ውጭ የሞተር ስፖርት)

የስፖርት ውድድሮችና ቶርናመቶች በማንኛውም የኣደጋ ምድብ ተፈቅደዋል፡ የተመልካች ብዛት ከ 400 መብለጥ የለበትም፡ እንደየ ተቋሙ የሕንፃ ዓቅም ገደቦች መከበር ኣለባቸው። በመሪ (guide) የሚሰጡ እንቅስቃሴዎች/ጉብኝቶች ያለገደብ (hard cap) ተፈቅደዋል፡ ገደቦችን ግምት ውስጥ ያስገባል።

ሕንፃ ውስጥ የመዝናኛ ተቋማት (Indoor entertainment) (ኣኳርየም፣ ሕንፃ ውስጥ ቲያትር ቤት፣ ሕንፃ ውስጥ ኣዳራሽ (arenas)፣ ሕንፃ ውስጥ የኮንሰርት ኣዳራሽ፣ ሕንፃ ውስጥ የኣትክልት ቦታ፣ ሕንፃ ውስጥ ቤተ መዘክር፣ ሕንፃ ውስጥ ቦውሊንግ፣ ሕንፃ ውስጥ ትራምፖሊን ተቋም፣ ሕንፃ ውስጥ የካርድ ጨዋታ፣ ማንኛውም የሕንፃ ውስጥ የመዝናኛ እንቅስቃሴ፥ ሕንፃ ውስጥ የኢቨንት ቦታዎችን ያጠቃልላል)

ከሕንጻው ዓቅም ከ 50% የማይበልጥ ወይም 400 ሰው፡ ከሁለቱም ኣነስተኛው። የምግብና የመጠጥ ኣገልግሎት የሚቀርብ ከሆነ ለምግብና መጠጥ ቦታዎች የወጡ መስፈርቶች መከበር ኣለባቸው።

ሕንፃ ውጭ የመዝናኛ ተቋማት ( የእንስሳት ስፍራ (zoos)፣ ሕንፃ ውጭ የኣትክልት ስፍራዎች (gardens)፣ ሕንፃ ውጭ ኣኳርየም፣ ሕንፃ ውጭ ትያትር ስፍራ፣ ክፍት ስተድየም፣ ሕንፃ ውጭ፣የዝግጅት ቦታዎች ፣ ከቤት ውጭ መድረኮች ፣ ከቤት ውጭ ኮንሰርት ሥፍራዎች ፣ሮድዮ (የካውቦይ ስፖርት) ያጠቃልላል)

ገደቦችን በማክበር በኣካል ትኬቶች መሸጥ/መግዛት ተፈቅደዎል። በተቋሙ ላይ በመመርኮዝ 400 ተመልካቾች ከአቅም ውስንነት ጋር ተፈቅደዋል።

ማሳሰብያ: የህያው መዝናኛ (Live entertainment) ገደብ ኣብቅተዋል፡ ነገር ግን ለተገቢው ቦታ ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን መመርያዎች መከተል ኣለባቸው። የረጅም ግዜ እንክብካቤ ተቋማት (Long-term care)፣ የፕሮፈሽናል እና የኮለጅ ስፖርት ከዚህ መመርያ ውጪ በሆነ የገዛ ራሳቸው መመርያ/ኣዋጆች እንደሚተዳደሩ ሆነው ይቆያሉ።