Skip to main content
King County logo

የኮቪድ-19 ክትባት ለድንገተኛ ግዜ ጥቅም በምግብና መድኃኒት አስተዳደር (FDA) ጸድቋል። የስያትልና ኪንግ ካዉንቲ ሕዝብ ጤና ከዋንሽግተን ስቴት ጤና ክፍል ጋር በመተባበር በክትባት ስርጭት ዕቅዶች ላይ እየሠራ ነዉ።

 • የመጀመሪያ የክትባት አቅርቦቶች የተወሰኑ ናቸዉ፤ መጀመሪያ ከፍተኛ ስጋት ላለባቸዉ የተወሰኑ ቡድኖች እንደ ጤና እንክብካቤ ዉስጥ ያሉ ሠራተኞች ና በነርሲንግ ቤቶች፣ ሌሎች የረጅም ግዜ እንክብካቤ መስጫ ተቋማት ዉስጥ ላሉ እና በዕድሜ ለገፉ ሰዎች ይሰጣል።
 • የኮቪድ-19 ክትባት ለተወሰኑ ወራት ዉስን እንደሆነ ይቀጥላል። በመጨረሻ ክትባቱ በተመከሩ ቡድኖች ላለ ሰዉ ሁሉ ይቀርባል።
 • የክትባት ደህንነት ቅድሚያ ይሰጠዋል። ሁሉም የኮቪድ-19 ክትባቶች ጥቅም ላይ ከመዋላቸው በፊት በጠንካራና እርምጃ-ብዙ ሙከራ፣ ግምገማ እንዲሁም የማጽደቅ ሂደት ማለፍ አለባቸዉ። የFDA የደህንነትና ዉጤታማነት ደረጃዎች ሲያልፉ ብቻ ነዉ ፈቃድ ማግኘት የሚችሉት። ክትባቶቹ ኣንዴ ከተሰጡ በኋላም የደህንነት ቁጥጥር ይካሄድባቸዋል።  

ክትባቱን እንዴት ማግኝት እንደሚቻል ያሉ መረጃዎች በተደጋጋሚ ይሻሻላሉ። እነዚህ ማሻሻያዎች በፍጥነት እንዲተረጎሙ እየሰራን ቢሆንም፣ ትርጉሙን ለመስራት እና ድህረ-ገጽ ላይ ለመለጠፍ በሚወሰደው ጊዜ ምክኒያት መጓተት ሊኖር ይችላል። ለትእግስትዎ እናመሰግናለን።

በእንግሊዘኛ ያሉ በጣም በቅርብ ጊዜ የተሻሻሉ መረጃዎችን ከ kingcounty.gov/covid/vaccine (ድህረ-ገጹ በእንግሊዘኛ ብቻ ነው ያለው) ማግኘት ይችላሉ።

በመጨረሻ ክትባት የሚፈልግ ሁሉ ያገኛል። ሆኖም ግን ክትባቱ መጀመሪያ ሲቀርብ የአቅርቦት ገደብ አለ። ከትባቱ በመጀመሪያ የሚሰጠዉ በኮቪድ-19 የመያዝ ከፍተኛ ስጋት ላለባቸዉ የተወሰኑ ሰዎች ወይንም በኮቪድ-19 ከተያዙ ሌላ ከባድ የጤና ሁኔታ ያለባቸዉ እንደ ጤና እንክብካቤ ሠራተኞች፣ ነርሲንግ ሆም ወይንም እርዳታ-ሰጭ (ኣሲስትድ ሊቪንግ) ተቋማት ውስጥ የሚኖሩ አዋቂዎች፣ እንዲሁም ሌሎች ወሳኝ ሠራተኞች ይሆናል።

የዋሽንግተን ስቴት ጤና ዲፓርትመንት (DOH) ለበርካታ ሆስፒታሎች፣ መድኃኒት ቤቶች፣ እና ክትባቱን ለመቀበል ለተመዘገቡ የጤና ስርዓቶች ክትባቱን አቅርቧል። DOH እና የስያትልና ኪንግ ካዉንቲ ማህበረሰብ ጤና የክትባት መስጫ ጣቢያዎችን እና የከተባቱን ተደራሽነት ለመጨመር ከብዙ ሽሪኮች ጋር እየሰሩ ነዉ።

ከጃንዋሪ 18 ቀን 2021 ጀምሮ የዋሽንግተን ስቴት ጤና ዲፓርትመንት የክትባት ስርጭትን በዙር 1b1 በኩል ከፍቲአል።

ክትባቱ በአሁኑ ሰዓት ክፍት የሆነላቸዉ ሰዎች፡

 • ለዙር 1a ብቁ ለሆኑ (ድህረ ገጹ በእንግልዝኛ ብቻ ነዉ): በኮቪድ-19 የመያዝ ወይም ማሰራጨት ስጋት ላለባቸዉ የጤና እንክብካቤ ቦታዎች ያሉ ሠራተኞች ሁሉ ፣ የረጅም ግዜ እንክብካቤ መስጫ ተቋማት ሠራተኞችና ነዋሪዎች፣ የቤት ዉስጥ ተንካባካቢ ረዳቶች።
 • ለዙር 1b1 ብቁ ለሆኑ፡
  • 65 ዓመታት ዕድሜ እና ከዚያ በላይ ለሆኑ
  • 50 ዓመታት ዕድሜ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ትዉልዶች ቤተሰብ የሚኖሩ ከሆነ (እንደ ሽማግሌ እና የልጅ ልጅ)፣ እና እነዚህን መስፈርቶች የሚያሟሉ፡
   • ራሳቸዉን ችለዉ መኖር የማይችሉና ከዘመድ ወይም ተንከባካቢ (ተከፍሎ ወይንም ያለክፍያ) ወይም ከቤት ዉጪ የሚሠራ ሰዉ
   • ከህጻን ልጆች ጋር የሚኖርና የሚንከባከብ፣ እንደ አያት የልጅ ልጅ ጋር እንደሚኖር።

በዚህ ዙር ብቁ ያልሆኑ፡

 • ከ50 ዓመት በታች የሆነ ሰዉ
 • 50 ዓመት ከዚያ በላይ የሆነ ጓደኛ ወይም አጋር የሚንከባከብ
 • ራሱን ችሎ መኖር የሚችል አዋቂና ዘመድ/ልጅ የሚንከባከብ

ስለብቁነት የበለጠ ይወቁ እና ኪንግ ካዉንቲ ካዉንቲ ዉስጥ ክትባት ማግኘት

 • የኮቪድ ክትባት በሜዲኬር፣ ሜዲኬድ ና በርካታ የግል ኢንሹራንስ ይሸፈናል፤ የክትባቱ ወጪ ኢንሹራንስ ለሌላቸዉ ሰዎችም ይሸፈናል። በኢንሹራንስ ዕቅድዎ ወይንም ክትባት ለማግኘት የሚያዩት ሓኪም መሰረት የወጪ መጋራት ክፍያ ወይንም የቢሮ ጉብኝት ክፍያ ሊኖር ይችላል።
 • የክትባት ኣቅርቦት ሲኖር፡ የሕዝብ ጤና በአነስተኛ ወጪ ወይንም በነጻ ክትባት የማግኘት ዕድል በሚሰጡ ክሊኒኮች እያቀደ ነዉ።

የኮቪድ-19 ክትባቶች ብዙ ሺ የጥናት ተሳታፊዎች ክትባት የሚቀበሉበት ጠንካራና/ጥብቅ በሆኑ የክሊኒክ ሙከራዎች ማለፍ አለባቸዉ። የምግብና መድኃኒት አስተዳደር (FDA) የያንዳንዱን ክትባት ደህንነትና ዉጤታማነት ለመወሰን ከነዚህ ጥናቶች የሚገኙትን መረጃዎች ይገመግማል። FDA በገለልተኛ ሳይንቲስቶችና ባለሙያዎች አማካሪ ቡድን ትንተናና ምክረ ሃሳቦች ላይ ይመረኮዛል፣ Vaccines and Related Biological Products Advisory Committee (VRBPAC)። የ VRBPAC ስብሰባዎች  ለህዝብ ክፍት ናቸዉ።

ክትባቱ የ FDA ደህንነትና ዉጤታማነት መስፈርቶች የሚያሟላ ከሆነ፡ FDA ክትባቱ አሜሪካ ዉስጥ ጥቅም ላይ እንዲዉል ሁኔታዎች ማመቻቸት ይችላል።

FDA ኣም ከወሰደ በኋላ ሁለተኛ ገለልተኛ የሆነ ሁለተኛ የክትባት ባለሙያዎች አማካሪ አካል፤ የኣሜሪካ Advisory Committee on Immunization Practices (ACIP), የክትባቱን ደህንነትና ዉጤታማነት መረጃ ያይና ሊሲዲሲ ስለ ክትባቱ ምክረ ሃሳብ ይሰጣል።

የክትባት የደህንነት ቁጥጥር:

ክትባቱ ጥቅም ላይ እንዲዉል ከተፈቀደ በኋላ፡ ሊከሰቱ የሚችሉ የጎንዮሽ ጉዳት ለማየት በርካታ የደህንነት ቁጥጥር ስርዓቶች  ይኖራሉያልታሰበ ከባድ የጎንዮሽ ጉዳት ከታየ ባለሙያዎች በተቻለ ፍጥነት እዉነተኛ የደህንነት ስጋት መሆኑን ለማረጋገጥ ይሠራሉ። የክሊኒክ ሙከራዎቹ ካለቁ በኋላ እንኳን ይህ እንደ ተከታታይ የደህንነት ግምገማ ሆኖ ያገለግላል። ለኮቪድ-19 ክትባት፡ ደህንነታቸውን በወቅቱ ለመገምገም እና የኮቪድ ክትባቱ ዓቅም እስከፈቀደው መጠን ደህንነቱን የተጠበቀ እንደሆነ ለማረጋገጥ ሲዲሲ እና FDA የደህንነት መቆጣጠርያ ስርዓትን ኣስፍተዋል።

ፈቃድ ያላሸዉና የሰለጠኑ የጤና ባለሙያዎች ብቻ ናቸዉ ክትባቶች ሊሰጡ የሚችሉት


ክትባት ለመስጠት ፈቃድ ያላቸውና የሰለጠኑ ግለሰቦች ብቻ ናቸዉ ክትባት መስጠት የሚችሉት። አንዴ ክትባቱ ለጠቅላላ ማህበረሰብ በሰፊዉ መቅረብ ከጀመረ ብዙ ዓይነት የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎች ክትባት ይሰጣሉ። እነዚህ አቅራቢዎች በክሊኒኮች ና ሆስፒታሎች እንዲሁም ተንቀሳቃሽ ወይም በየግዜው ህብረተሰቡ ውስጥ ብቅ የሚሉ ኩነቶች ላይ ክትባቶች ሊሰጡ ይችላሉ። 

 • ደህንነቱ የተጠበቀ ና ዉጤታማ የኮቪድ-19 ክትባት ትልቅ እምርታ ነዉ። ኝ ክትባት ብቻዉን ወረርሽኙን አሁኑኑ አያስቆምም።
 • ክትባቱ ከቀረበ በኋላ እንኳን ወረርሽኙን ማስቆም ሁሉም ራሳቸዉንና ሌሎችን ለመከላከል በአሁኑ ያሉትን ሁሉንም መመሪያዎች መከተልን ይጠይቃል ምንም እንኳን ተከትቦም ቢሆን። ይህም ማስክ መልበስ፣ ከሌሎች ቢያንስ 6 ጨማ መራቅ፣ ከቤት ዉጭ እንቅስቃሴዎችን መገደብና ሰዉ የበዘበትን ማስወገድ፣ በየግዜዉ እጅ መታጠብ፣ የሲዲሲን የጉዞ መመሪያ መከተል፣ እና ኮቪድ-19 ከየዘዉ ሰዉ ጋ ከተጋለጡ በኋላ የለይቶ ማቆያ መመሪያ መከተልን ያካትታል።