Skip to main content
Most King County offices will be closed on Monday, for Memorial Day.  
King County logo

እነዚህ ግብአቶች ስለ COVID-19 ክትባት፣ የክትባት ማህደርዎን በድህረ-ግጽ ላይ ለመመልከት እንዴት መመዝገብ እንደሚችሉ፣ እና ስለሚስጥራዊነት እና ክፍያ ሌሎት አስፈላጊ መረጃዎችን ይይዛሉ። ስለ COVID-19 ተጨማሪ ጥያቄ ካለዎት፣ እባክዎ በክትባት ቦታ ወይም ሃኪምዎትን ወይም የመጀመሪያ ደረጃ የጤና እርዳታ አቅራቢዎን ይጠይቁ።

ከታች ያሉት እውነታ ገጾች በአምራቹ የተዘጋጁ ሲሆን ስለክትባቱ ዝርዝር መረጃ ይሰጣሉ፣, ማን ክትባቱን ማግኘት እንዳለበት እና እንደሌለበት፣ ክትባቱን ከመውሰድዎ በፊት ክትባቱን ለሚሰጥዎት የክትባት አቅራቢ ምን መጥቀስ እንዳለብዎት፣ እና ሊያጋጥሙ ስለሚችሉ የጎንዮሽ ጉዳቶች ማለት ነው።

በዚህ ገጽ መጨረሻ ላይ በምግብ እና መድሃኒት አስተዳደር (Food and Drug Administration (FDA)) በየድንገተኛ ጊዜ አጠቃቀም ፈቃድ (Emergency Use Authorization (EUA)) ለክትባቶቹ እንዴት እንደተሰጠ አጠር ያለ ማብራሪያ እንዳለ እባክዎ ያስተውሉ። ይህም በእወነታ ገጹ መጀመሪያ ላይ የተጻፈውን እና ምናልባትም ሊያወዛግብ የሚችል አስተያየትን ለማስረዳት ይጠቅማል፡ "የ COVID-19 ን ለመከላከል በአሜሪካ የምግብ እና መድሃኒት አስተዳደር (Food and Drug Administration (FDA)) ፍቃድ ያገኘ ክትባት የለም።"

ስለ COVID-19 ክትባት ፈቃድ አሰጣጥ ማወቅ ያለብዎት ነገሮች፡

  • እነዚህ ክትባቶች በ FDA የድንገተኛ ጊዜ አጠቃቀም ፍቃድ አግኝተዋል፣ ይህም ማለት በብሄራዊ ድንገተኛ አደጋ ጊዜ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ፍቃድ አግኝተዋል፣ ነገር ግን ይህ ማለት ሙሉ ፈቃድ አግኝተዋል ማለት አይደለም።
  • ለእነዚህ ክትባቶች የ FDA የደህንነት እና ውጤታማነት መስፈርቶች ተሟልተዋል። በሺዎች የሞቆጠሩ ሰዎች ከተሳተፉበት እና ከብዙ ምርመራዎች በኋላ በገለልተኛ የህክምና ባለሙያዎች ከተከለሰ በኋላ መስፈርቶቹን የሚያሟሉ ክትባቶች ብቻ ናቸው የድንገተኛ ጊዜ ጥቅም ፈቃድን የሚያገኙት።

የድንገተኛ ጊዜ አጠቃቀም ፈቃድ (Emergency Use Authorization (EUA) ምን ማለት ነው?የሚለውን በብዛት የሚጠይቅ ጥያቄን ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይመልከቱ።

V-safe በስልክ ላይ የተመሰረተ መገልገያ ሲሆን፣ የ COVID-19 ክትባትን ካገኙ በኋላ የስልክ መልእክትን እና የድሀረ-ገጽ ዳሰሳ ጥናትን በመጠቀም ለእርስዎ ተብለው የተዘጋጁ የጤና ምክሮችን ይሰጣል። ሁለተኛ ክትባትዎን እንዲያገኙ ያስታውሶታል። V-safe ን በመጠቀም የ COVID-19 ክትባትን ካገኙ በኋላ የጎንዮሽ ጉዳት ካጋጠምዎት ለሲ.ዲ.ሲ (CDC) ማሳወቅ ይችላሉ።

አላርጂክ የሆነ የሰውነት ምላሽ ያላቸው ሰዎች ካሉ ሁኔታውን ለመለየት እና ምላሽ ለመስጠት በሁሉም የክትባት ቦታዎች ላይ የህክምና ባለሙያዎች ይገኛሉ። ክትባቱን ካገኙ በኋላ ድንገት እርዳታ ካስፈለግዎ ለ 15 ደቂቃዎች ያክል ክትትል ይደረግልዎታል። የትኛውም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት ካጋጠመዎት፣ እባክዎ ለማእከሉ ሰራተኛ ያሳውቁ።

የከፋ የአላርጂክ የሰውነት ምላሽ ካጋጠመዎት፣ 9-1-1 ይደውሉ ወይም በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ ሆስፒታል ይሂዱ። እያሳሰብዎት ያለ የጎንዮሽ ጉዳት ካለ የጤና እርዳታ አቅራቢዎ ጋር ይሂዱ ወይም ትተው ከእዚህ አይሂዱ።

የተወሰኑ የጎንዮሽ ጉዳቶች ሊያጋጥምዎት ይችላሉ፣ እነዚህም ሰውነትዎ የመከላከል አቅም እየገነባ መሆኑን የሚያሳዩ መደበኛ ምልክቶች ናቸው። የተወሰኑ ሰዎች እንደ ራስ ምታት፣ የሚያቃጥል ክንድ፣ ድካም፣ ትኩሳት ወይም የጡንቻ ህመሞችን የመሰሉ ምልክቶች ሊያጋጥሙዋቸው ይችላሉ። እነዚህ የጎንዮሽ ጉዳቶች የእለት ተእለት እንቅስቃሴዎችዎን የመፈጸም አቅምዎ ላይ ትጽእኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ፣ ሆኖም ግን ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ይጠፋሉ። የተወሰኑ ሰዎች ደግሞ ምንም የጎንዮሽ ጉዳት አይገጥማቸውም።

የከፋ የክትባት የጎንዮሽ ጉዳቶችዎን ለFDA/CDC የአሉታዊ ሁነት ሪፖርት ማድረጊያ ሲስተም (Vaccine Adverse Event Reporting System (VAERS)) ሪፖርት ያድርጉ። የ VAERS የስልክ ቁጥር ላይ በ 1-800-822-7967 ይደውሉ ወይም በ https://vaers.hhs.gov/reportevent.html (ድህረ-ግጹ በእንግሊዘኛ ብቻ ነው ያለው)። ድህረ-ገጽ በመግባት ሪፖርት ያድርጉ። በሪፖርት ማድረጊያው #18 ቁጥር ላይ ባለው ሳጥን ወስጥ በመጀመሪያው መስመር ላይ በመግባት የወሰዱትን የክትባት ስም ይጥቀሱ።

የሚስጥራዊነት እና የስምምነት ቅጹን ይጫኑ።(ድህረ-ግጹ በእንግሊዘኛ ብቻ ነው ያለው) ይህ ቅጽ የህዝብ ጤና የእርስዎን የጤና መረጃ በሚስጥራዊነት እንዴት እንደሚይዝ መረጃ እንደሰጥዎት ማረጋገጫ ነው። ኢንሹራንስ ካልዎት፣ በኢንሹራንስዎ በኩል ክፍያ እንዲፈጸምም ማረጋገጫ ነው። ይህ ቅጽ ከህዝብ ጤና - ሲያትል & ኪንግ ካውንቲ ክትባት ("ህክምናው") ለማግኘት ያልዎትን ፈቃደኝነት ይመዘግባል።

ስልጣን ባለው አዋቂ ሰው የተሰጠ ፈቃድ: ዕድሜዎ ከ18 ዓመት በታች ከሆነ: ክትባት ለማግኘት ስልጣን ካለው አዋቂ ሰው ፈቃድ ማግኘት ያስፈልግዎታል። ከቤተሰብ ነጻ ሆነው የሚኖሩ ከሆነ : አዋቂ ሰው አግብተው ከሆነ: ወይም የክትባት ጣቢያው የበሰሉ/አዋቂ ልጅ (mature minor) መሆንዎትን ከወሰነ ለራስዎ ፈቃድ መስጠት ይችላሉ። ሁሉም የክትባት ጣቢያዎች የበሰለ/አዋቂ ልጅ ውሳኔዎችን ሊሰጡ አይችሉም።

ለልጆች ፈቃድ ለመስጠት የሚችሉ ስልጣን ያላቸው አዋቂዎች የሚከተሉትን ያካትታል:

  • የጤና እንክብካቤ ውሳኔዎችን ለእርስዎ መስጠት እንዲችሉ ከፍርድ ቤት ፈቃድ የተሰጣቸው አዋቂዎች (ህጋዊ ሞግዚት: አሳዳጊ: ከቤት ውጭ እንዲሆኑ የታዘዘበት)
  • ወላጅ
  • የጤና እንክብካቤዎትን አስመልክቶ ውሳኔ እንዲሰጥ ከቤተሰብ በጽሁፍ ፈቃድ የተሰጠው አዋቂ ሰው
  • ለጤና እንክብካቤዎት ሃላፊነት ያለበት የቅርብ ዘመድ የሆነ አዋቂ ሰው
  • በአንዳንድ ሁኔታዎች: የት/ቤት ነርስ: የት/ቤት አማካሪ: ወይም መኖርያ ቤት የሌለው ተማሪ ጉዳይ አስፈጻሚ

ስልጣን ያለው አዋቂ ሰው በክትባት ቀጠሮው ላይ ከርስዎ ጋር የማይገኝ ከሆነ ስልጣን ያለውን አዋቂ ሰው ማረጋገጫ ወይም በህግ ነጻ መሆንዎትን የሚያረጋግጡ ማስረጃዎችን ለማሳየት የሚያስፈልጉ ነገሮችን በተመለከተ ክትባቱን ከሚስጥዎት ድርጅት ያጣሩ።

የህብረተሰብ ጤና - የሲያትልና ኪንግ ካውንቲ ለልጆች የCOVID-19 ክትባት ፈቃድ መስጫ ፎርም (PDF)

ይህ ቅጽ በህብረተሰብ ጤና የሲያትል እና ኪንግ ካውንቲ የክትባት መስጫ ጣቢያዎች እንዲሁም በኦበርን እና ኬንት የጋራ የክትባት ጣቢያዎች እና የህብረተስብ ጤና ክሊኒኮች ስራ ላይ ይውላል። ስልጣን ያለው አዋቂ ሰው በክትባት ቀጠሮው ላይ ከርስዎ ጋር የማይገኝ ከሆነ ይህ ቅጽ እንደ ጽሁፍ ማረጋገጫ ሊያገለግል ይችላል። እንዲሁም የህብረተሰብ ጤና ሰራተኛ ስልጣን ካለው አዋቂ ሰው በስልክ የቃል ማረጋገጫ ወይም የጽሁፍ ማስታወሻ ሊቀበል ይችላል። የክትባት ቀጠሮዎት በህብረተሰብ ጤና ጣቢያ ካልሆነ ስልጣን ያለውን አዋቂ ሰው ማረጋገጫ ወይም በህግ ነጻ መሆንዎትን የሚያረጋግጡ ማስረጃዎችን ለማሳየት የሚያስፈልጉ ነገሮችን በተመለከተ ክትባቱን ከሚስጥዎት ድርጅት ያጣሩ።

ከዋሺንግተን ስቴት የጤና ዲፓርትመንት በ "MyIR" በኩል የሚሰጠውን ይፋዊ የቤተሰቦችዎን የክትባት ማህደር ለማግኘት በድህረ-ግጽ ላይ መመዝገብ ይችላሉ።

ስለ COIVD-19 ክትባት ተገኚነት፣ ስለ COIVD-19 ክትባት ደህንነት እና አመራረት መረጃ፣ እና ከህዝብ ጤና - ሲያትል & ኪንግ ካውንቲ በብዛት ስለሚነሱ ጥያቄዎች መረጃዎችን ያግኙ፡ www.kingcounty.gov/covid/vaccine/amharic


Link/share our site at kingcounty.gov/yourvaccine/amharic