Skip to main content

KingCounty.gov is an official government website.

Official government websites use .gov
Website addresses ending in .gov belong to official government organizations in the United States.
Secure .gov websites use HTTPS
A lock or https:// means you've safely connected to the .gov website. Only share sensitive information on official, secure websites.

INSTRUCTIONS FOR CLERK’S FEE WAIVER

በፍርድ ቤት ጉዳይዎ የፀሐፊን ክፍያ(ዎች) ለመክፈል አቅም ካልቻሉ፣ ይቅርታ መጠየቅ ይችላሉ። የክፍያ ማቋረጥ ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱን ለመወሰን ፀሐፊው የመክፈል አቅምዎን ያጠናቅቃል እና የተፈረመ የክፍያ ማቋረጫ ጥያቄን በማቅረብ ላይ የተመሠረተ ነው።

ማረጋገጫውን ለማጠናቀቅ፡

  1. በተዋዋይ ወገኖች ስም ይጻፉ (ከሳሽ/አመልካች እና ተከሳሽ/ተጠሪ).
  2. የመዝገብ ቁርት ያስገቡ.
  3. 3. ከታች ባለው የጉዳይ ቁጥር፣ ከሚጠይቋቸው የክፍያ ስረዛ አንዱን ወይም ከዚያ በላይ ያረጋግጡ.
  4. በተጠቀሰው መስመር ላይ ስምዎን በግልጽ ይጻፉ.
  5. የክፍያ መሰረዝን ለመጠየቅ ብቁ መሆንዎን በተሻለ የሚደግፈውን ሳጥን ላይ ምልክት ያድርጉ (ከዚህ በታች ይመልከቱ)፡፡ እንደ አስፈላጊነቱ ደጋፊ ሰነዶችዎን አብረው ያያይዙ፡፡
  6. ሰነዱ ላይ ቀን መጻፍና መፈረም፡፡

የክፍያ ስረዛ የብቃት ማረጋገጫ መስፈርቶች፡

ጥቅማጥቅም ሽልማት ደብዳቤ፡

በአሁኑ ጊዜ በፍላጎት ላይ የተመሰረተ፣ በሚከተለው የተረጋገጠ የእርዳታ ፕሮግራም ስር እርዳታ በማግኘት ላይ ነዎት፡

  • የፌዴራል ጊዜያዊ ድጋፍ ለተቸገሩ ቤተሰቦች (TANF)
  • ሥራ አጥ ለሆኑ ግለሰቦች በግዛቱ የተሰጠ አጠቃላይ ድጋፍ (GA-U ወይም GA-X)
  • የፌዴራል ተጨማሪ ደህንነት ገቢ (SSI)
  • ከፌዴራል ድህነት ጋር የተዛመዱ የአርበኛ ጥቅማጥቅሞች
  • የራሽን እደላ ፕሮግራም (FSP)

የፋይናንስ መግለጫ ቅጽ፡

ሰ የቤተሰብዎ ገቢ ከፌዴራል የድህነት ደረጃ አንጻር በ 125% ያነሰ ነው (ከዚህ በታች ይመልከቱ)፡፡

የቤተሰብ መጠን 1 2 3 4 5 6 7 8 9 ወይም ከዛ በላይ
ከፍተኛ ወርሀዊ ገቢ* $1,663 $2,254 $2,846 $3,438 $4,029 $4,621 $5,213 $5,804 ለእያንዳንዱ ተጨማሪ ሰው $592 ይጨምሩ
ከፍተኛ ዓመታዊ ገቢ* $19,950 $27,050 $34,150 $41,250 $48,350 $55,450 $62,550 $69,650 ለእያንዳንዱ ተጨማሪ ሰው $7,100 ይጨምሩ

*“ገቢ” ማለት ታክስና የልጅ እንክብካቤ ወጪዎች ከተቀነሱ በኋላ የሚገኘው የተጣራ ገቢ ነው፡፡

የፍርድ ቤት ትእዛዝ ክፍያ የመተው፡-

በዚህ ጉዳይ ላይ የማመልከቻ ክፍያዎችን እና ተጨማሪ ክፍያዎችን ለመተው የፍርድ ቤት ትእዛዝ አለህ ይህም ጉዳዩ እስኪዘጋ ድረስ ወይም በቤተሰብ ህግ ጉዳዮች አሁን ያለው የእርምጃ መንስኤ እልባት እስኪያገኝ ድረስ ነው።

የተሞላውን የማሰረዣ ጥያቄ ይመለሱ ወይም ቅጹን በኦንላይን ላይ ይሙሉ፡፡ እነዚህ አማራጮች አሉ፡

በኦላይን – KC Script Portal (የተመረጠ ዘዴ)፡

ወደሚከተለው ይሂዱ፡ይህድህረገጽ: https://dja-prd-ecexap1.kingcounty.gov/?q=Home

በእኛ የ KC Script Portal በኩል ከክፍያ ነጻ መሆንን እንዴት እንደሚጠይቁ መመሪያዎችን ለማግኘት እዚህ ጠቅ ላይ ያድርጉ፡ https://kingcounty.gov/en/dept/dja/courts-jails-legal-system/case-records/records-access/portal-instructions-spanish

በአካል በመገኘት፡

የተሟሉ ጥያቄዎችንና ደጋፊ ሰነዶችን ለጸሀፊው ቢሮ ገንዘብ ተቀባይ ከቀኑ ከ 8፡30 ኤኤም - 4፡30 ፒኤም፣ ከሰኞ እስከ አርብ (ከ 12፡15 - 1፡15 ፒኤም መካከል ያለው የተገደበ አገልግሎት) ይመልሱ (አድራሻው ከታች አለ)

በፖስታ፡

የተሟሉ ጥያቄዎችንና ደጋፊ ሰነዶችን ወደ አንዱ ቦታ ይላኩ፡

Regional Justice Center
Attn: Clerks Office
401 Fourth Avenue North Room 2C
Kent, WA 98032-4429

King County Superior Court
Attn: Clerks Office
516 Third Avenue Room E609
Seattle, WA 98104-2386

ጥያቄዎንዎንና ደጋፊ ሰነዶችን መምጣት ካልቻሉ እባክዎን ለእርዳታ በ 206-296-9300 ላይ ይደውሉ፡፡

የጸሐፊ ክፍያ ማቋረጥ የሚከተሉትን አገልግሎቶች ያካትታል፡-

  • Ex Parte በፀሐፊው አቀራረብ
  • የተመዘገቡ ሰነዶች ቅጂዎች
  • ሰነዶችን በፀሐፊው መስጠት
  • የተመዘገቡ ችሎቶች ቅጂዎች

*የe(ኢ)-ስራ ቅጂዎች ማቅረቢያዎች በፀሐፊው ክፍያ ማቋረጥ ውስጥ አይካተቱም።*

የስራ ቅጂዎችን ያለክፍያ ስለማስገባት ተጨማሪ መረጃ የፍርድ ቤቱን ድህረ ገጽ ይጎብኙ፡- https://kingcounty.gov/en/court/superior-court/about-superior-court/judges-staff/judges/delivering-documents

ይህን ትርጉም በተመለከተ አስተያየት ስለሰጡን እናመሰግናለን።