Metro Flex
Metro Flex የእርስዎ በትዕዛዝ ላይ የተመሠረተ የአጎራባች አካባቢዎች የመጓጓዣ አገልግሎት ነው። በአንድ ቀላል መተግበሪያ - እና ጥቂት ጊዜ ነካ በማድረግ ብቻ - ሁሉም ከአውቶቡስ ጉዞ ተመሳሳይ ዋጋ ጋር፣ በአገልግሎት ክልል ውስጥ በማንኛውም ቦታ መጓዝ ይችላሉ። የ Metro Flex ምቹ፣ ፈጣን፣ ተመጣጣኝ መጓጓዣ በጣቶችዎ ጫፍ ላይ ነው።
Metro Flex ምንድን ነው
Metro Flex በበርካታ የ ኪንግ ካውንቲ ሰፈሮች ውስጥ መጓጓዣዎችን የሚያቀርብ በፍላጎት ላይ የተመሠረተ የመጓጓዣ አገልግሎት ነው። በዘመናዊ ምቹ ሚኒቫኖቻችን በአንድ ዝቅተኛ ዋጋ ወደሚፈልጉበት ቦታ ይድረሱ። ወደ ገበያ ይሂዱ፣ ለምሳ ከጓደኞችዎ ጋር ይገናኙ ወይም ወደ ቀጠሮዎች ይሂዱ። በአገልግሎት ክልል ውስጥ መድረሻዎ ምንም ይሁን ምን፣ Metro Flex ወደዚያ ይወስድዎታል።
- ምቹ
ለMetro Flex የት እንዳሉ እና የት መሄድ እንደሚፈልጉ ለመንገር ስልክዎን ይጠቀሙ። በቅርብ ርቀት እርምጃ ላይ የሚገኝ የመነሻ ቦታ ያገኛሉ። - ፈጣን
ጉዞዎን ማስያዝ ፈጣን እና ቀላል ነው! መተግበሪያው ለእርስዎ Metro Flex ተሽከርካሪ የሚገመተውን የመድረሻ ጊዜ ይልክልዎታል። - ተመጣጣኝ
ከ Metro የአውቶቡስ ጉዞ ጋር በተመሳሳይ ወጪ በMetro Flex ይጓዙ። እና በ ORCA ካርድዎ ከ ወይም ወደ አውቶቡስ፣ Sound Transit Link ቀላል ባቡር ወይም Sounder በነጻ ማስተላለፍ ይችላሉ። - የጉዞ አማራጭ ማሳወቂያዎችን ያካትታል
አዲሱ መተግበሪያ በእርስዎ የመነሻና እና የመድረሻ ቦታዎች ላይ በመመሥረት — የMetro Flex መጓጓዣ ይሁን ፣ በአውቶቡስ ላይ የሚደረግ ጉዞ ወይም ሌላ የመተላለፊያ አገልግሎት የእርስዎን ምርጥ የመተላለፊያ ምርጫዎች ይዘረዝራል።
የMetro Flex መተግበሪያን ያውርዱ
የMetro Flex የበዓል ቀናት መርሃግብር
Metro Flex በአዲስ ዓመት ቀን፣ በመታሰቢያ ቀን፣ በነፃነት ቀን፣ በሠራተኞች ቀን፣ በምስጋና ቀን እና በገና ቀን በእሁድ የአገልግሎት መርሃ ግብር ይሠራል።
እንዴት እንደሚጓጓዙ
ጉዞዎን በMetro Flex መተግበሪያ ሲያስይዙ፣ በጣም የተሟላ የጉዞ መረጃ ያገኛሉ። ይህ የቀጥታ ተሽከርካሪ ክትትልን እና ሌሎች የመጓጓዣ አማራጮችን ዝርዝር ያካትታል።
በመተግበሪያው ውስጥ
- መተግበሪያውን ያውርዱ እና መገለጫዎን ያዋቅሩ። ማንኛውንም የመንቀሳቀስ ፍላጎቶችን ወይም ልዩ ክፍያዎችን ለማመልከት የእርስዎን “የክፍያ ዓይነት”(payment type) እና በመቀጠል “ታሪፍ/አገልግሎት ዓይነት” (fare/service type) የሚለውን ይምረጡ።
- ለእርስዎ እና እስከ 4 ለሚደርሱ ሌሎች መንገደኞች መጓዣ ለመጠየቅ መተግበሪያውን ይክፈቱ።
- የመድረሻ ሰዓት እና በአቅራቢያዎ የሚገኝ መነሻ ቦታ ያገኛሉ - በመነሻና መዉረጃ ቦታዎችአጭር የእግር ጉዞ ሊያስፈልግ ይችላል።
በዊል ቼር/ተሽከርካሪ ወንበር የሚደረስ ተሽከርካሪ የሚጠይቁ የመንቀሳቀስ ፍላጎቶች ካሎት፣ ይህንን መረጃ በMetro Flex መገለጫዎ ውስጥ ያካትቱ። ከዚያ በኋላ ለሁሉም ጉዞዎችዎ ተደራሽ የሆነ ተሽከርካሪ በቀጥታ ይመደብልዎታል እና ምንም የእግር ጉዞ አያስፈልግዎትም።
በስልክ
- ለደንበኛ አገልግሎት በ206-258-7739 ይደውሉ እና የት እንዳሉ እና የት መሄድ እንደሚፈልጉ ያሳውቋቸው።
- ስላሎት ማንኛውም የመንቀሳቀስ ፍላጎት እና ክፍያዎን እንዴት እንደሚከፍሉ መረጃ ያቅርቡ።
- የመድረሻ ሰዓቱን እና ሹፌርዎን የት እንደሚያገኙ ወኪልዎ የጉዞዎን ዝርዝሮች ያቀርባል።
መስመር ላይ
- መለያዎን ለመፍጠር እና/ወይም ወደ መለያዎ ለመግባት ወደ metroflex.app.ridewithvia.com tይሂዱ።
- መነሻ እና መድረሻ ቦታዎን ያስገቡ፣ ቦታዎችን ያረጋግጡ (ወይም ካርታውን ሁለቴ ነካ ያድርጉ)።
- ማንኛውም የመንቀሳቀስ ፍላጎት እና/ወይም ተጨማሪ ተሳፋሪዎችን በ“1 ተሳፋሪ”(1 Passenger) ተቆልቋይ ስር ያመልክቱ።
- የጉዞ አማራጮችን ይገምግሙ እና “የጉዞዬን ቦታ ያስይዙ”(book my ride) የሚለውን ይምረጡ።
- የመድረሻ ሰዓቱን እና ሹፌርዎን የት እንደሚያገኙ ጨምሮ የጉዞ ዝርዝሮችዎ ይደርሰዎታል።
ታሪፍ እና ክፍያ
የ Metro Flex የጉዞ ወጪ ከMetro አውቶቡስ ጉዞ ጋር ተመሳሳይ ነው። በሚሳፈሩበት ጊዜ ይክፈሉ ወይም ለአሽከርካሪዎ የክፍያ ማረጋገጫ ያሳዩ።
የአሁኑን Metro ታሪፎችን እና ክፍያን ይመልከቱ
ORCA ካርድ
የORCA ካርድ መጠቀም በMetro Flex እና አውቶቡሶች፣ Sound Transit Link ቀላል ባቡር ወይም Sounder መካከል ለመሸጋገር ያስችልዎታል። በORCA ካርድ የቦርድ ካርድ አንባቢን (በአሽከርካሪዎ ራስ መቀመጫ ጀርባ ላይ የሚገኘውን) ነካ ያድርጉ።
Transit GO Ticket
በስልክዎ ላይ Transit GO Ticketን መጠቀም በMetro Flex እና በሌሎች Metro አውቶቡሶች መካከል ለመሸጋገር ያስችልዎታል። ወደ Link ቀላል ባቡር እና Sounder ባቡር የሚደረጉ ሽግግሮችአይሸፈኑም። የእርስዎን Transit GO Ticket (በስልክ መተግበሪያዎ ላይ) ለሹፌሩ ያሳዩ።
ክሬዲት ካርዶች፣ ዴቢት ካርዶች እና የቅድመ ክፍያ ካርዶች
ክፍያው ተቀባይነት የሚያገኘው በስልክ ከደንበኛ አገልግሎት ወኪል ጋር ወይም በMetro Flex መተግበሪያ በኩል ብቻ ነው። የመለያ መረጃን ወደ Metro Flex መተግበሪያ በማስገባት በክሬዲት ወይም በዴቢት ካርድ ይክፈሉ።
ይህ ዘዴ በሚከፈልበት Metro Flex ታሪፍ ወደ አውቶቡሶች፣ Link ቀላል ባቡር ወይም Sounder ለማስተላለፍ አይፈቅድልዎትም። በሌላ አገላለጽ፣ በሌሎች የመጓጓዣ ተሽከርካሪዎች ለመጓዝ እንደገና መክፈል ያስፈልግዎታል።
የተቀነሱ ታሪፎች
ሁሉም ነባር የ የኪንግ ካውንቲ ሜትሮ የተቀነሱ ዋጋ ፕሮግራሞች፣ ORCA LIFTን ጨምሮ፣ ተቀባይነት አላቸው።
ማስተባበያ፦ መደበኛ የMetro ዋጋዎች ተፈጻሚ ናቸው። የገንዘብ ታሪፎች እና የወረቀት ዝውውሮች/ትኬቶች በMetro Flex ተሽከርካሪዎች ላይ ተቀባይነት የላቸውም። 18 እና ከዚያ በታች ያሉ ተጓዦች ሁልጊዜ በMetro Flex እና በክልሉ ውስጥ ባሉ ሌሎች መጓጓዣዎች ላይ በነጻ ይጓዛሉ።
ተደራሽነት
ለዊል ቼር/ተሽከርካሪ ወንበር የሚመች ተሽከርካሪ ከፈለጉ፣ ሌላ የመንቀሳቀስ ድጋፍ ከፈለጉ ወይም በአጭር ርቀት ለመራመድ ከተቸገሩ፣ እባክዎ ሁሉንም ፍላጎቶች በMetro Flex መገለጫዎ ውስጥ ያመልክቱ። ጉዞዎችን በስልክ ካስያዙ ስለግል ጉዞ ድጋፍ ፍላጎቶችዎ ለደንበኛ አገልግሎት ወኪልዎ ይንገሯቸው።
እባክዎ ያስተውሉ፣ ለእያንዳንዱ Metro Flex ተሽከርካሪ አንድ የዊል ቼር/የተሽከርካሪ ወንበር መንገደኛ ብቻ ነው የሚቀመጠው። በተሽከርካሪው የኋላ ክፍል ውስጥ የሚገኘው የዊል ቼር/ተሽከርካሪ ወንበር መወጣጫ እስከ 800 ፓውንድ እና እስከ 36 ኢንች ስፋት ያለው የዊል ቼር/ተሽከርካሪ ወንበሮችን ለማስተናገድ የተነደፈ ነው።
አጠቃላይ የደንበኛ ድጋፍ
ለአጠቃላይ Metro ጥያቄዎች ወይም አስተያየቶች (ማለትም፣ የአገልግሎት ግብረመልስ ለመስጠት፣ በጉዞ እቅድ ወይም በORCA ካርድዎ ላይ እገዛን ለማግኘት) እባክዎ የኪንግ ካውንቲ ሜትሮ ን ያግኙ
ስልክ፦ 206-553-3000
(የትርጉም አገልግሎቶች ይገኛሉ።)
የስራ አጋር የዜሮ መቻቻል መመሪያ (Operating Partner Zero Tolerance Policy)
Translate

