RapidRide R Line
ወደ ደቡብ Seattle ስንመጣ
የተሻለ፣ የበለጠ አስተማማኝ የአውቶቡስ አገልግሎት እና ተስማሚነቶችን ለማቅረብ RapidRide ን ወደ ደቡብ Seattle እንዲወስድ ለማድረግ እየሰራን ነው! የ RapidRide R መስመር መንገድ 7ን ደረጃ ከማሻሻል በተጨማሪ Chinatown-International Districtን፣ Mount Bakerን፣ Columbia Cityን፣ Hillman Cityን፣ Brighton እና Dunlapን ጨምሮ በ Seattle እና Rainier Beach መካከል ለሚገኙ መኖሪያ መንደሮች አገልግሎት ይሰጣል።
የኪንግ ካውንቲ Metro እና የSeattle የትራንስፖርት መምሪያ (SDOT) በደቡብ Seattle የዕቅድ ዝግጅት፣ ስምሪት እና የተሳትፎ ጥረቶች ላይ በጋራ እየሰሩ ነው። ስለ Rainier Avenue S፤ የአውቶቡስ መንገድ ፕሮጀክት ግንባታ በተመለከተ ተጨማሪ ለማወቅ የSDOTድረገጽን ይመልከቱ።
የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ምልከታ
መንገድ 7 ለደቡብ ሲያትል ማህበረሰቦች ወጥ የሆነ የመጓጓዣ አይነት አይነት ሲሆን—ይህ ለአኗኗር ወሳኝ የሆነ መንገድ ለብዙ በታሪክ ውስጥ ዝቅተኛ ግልጋሎት ላገኙ ማህበረሰቦች የእኔነት ስሜት ፈጥሯል። ይህ መንገድ በቀን ከ9,000 ለሚበልጡ አሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚሰጥ በጣም ከሚጨናነቁ የSeattle መንገዶች መካከል አንዱ በመሆኑ በ RapidRide መስመር መተካት አስፈላጊ ነው። መንገዱ በተጨማሪም ከአምስቱ የወደፊት አሽከርካሪዎችን ለተሻሉ ግንኙነቶች እና አስተማማኝ አገልግሎት ተደራሽ ከሚያደርጉት እያደገ የሚሄድ የMetro ትራንዚት ሲስተም አካል ከሆነው ከ RapidRide መስመሮች መካከል አንዱ ነው።
የRapidRide R መስመር:
- መንገዱ በSeattle መሀል ከተማ የሚያልፍ ሲሆን ከ Rainier Beach Link የቀላል ባቡር ጣቢያ ጋር በአዲስ መልኩ ያገናኛል።
- የደቡብ ሲያትልን Seattle ተደራሽነትና ተደጋጋሚ ምልልስን ያሳድጋል።
- የመንገዱን ጥራት ያሻሽዋል እንዲሁም መሰረተ ልማትን፣ ተስማሚነትን እና አሽከርካሪዎች ወደ ትራንዚቱ ለመድረስ የሚጠቀሙበትን ቴክኖሎጂ ጨምሮ ከትራንዚቱ ጋር በአስተማማኝ ሁኔታ መገናኘትን ያቀላል።
የRapidRide R መስመር ግቦች የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ:
- በደቡብ Seattle ውስጥ ለበለጠ አስተማማኝ የትራንዚት አገልግሎት ተደራሽ መሆን
- የመንገዱን ጥራት ማሻሻል እና በእግረኛ መንገድ፣ በደረጃ መወጣጫ እና የማቋረጫ ማሻሻያዎች አማካኝነት ከትራንዚት ጋር በአስተማማኝ ሁኔታ መገናኘትን ማቅለል
- በማቋረጫዎች እና በመንገዱ ላይ የሚያጋጥሙ መዘግየቶችን ማቅለል
- በተሸሻሉ አውቶቡሶች፣ የተሻሻሉ የመጫኛ ቦታዎች፣ አዳዲስ መጠለያዎችና መቀመጫዎች፣ የተሻሻሉ መብራቶች እና በጣቢያዎች በሚለጠፍ የሪል ታይም የአውቶቡስ መድረሻ አማካኝነት የአሽከርካሪዎችን አጠቃላይ ተሞክሮ ማሻሻል
የ RapidRide ጥቅሞች
ለአውቶቡሶች ቅድሚያ መስጠት
በ RapidRide በብዙ ቦታዎች ለፈጣን አገልግሎት ሰዓት በተሞላላቸው ልዩ የትራፊክ መብራቶች በቀይ “ለአውቶብሶች ብቻ” የሚለረ በተሰመረባቸው መንገዶች መጓዝ።
የበለጠ ተደራሽነት
በሁሉም በሮች መሳፈር ይችላሉ። በአውቶቡስ ጣቢያ ወይም በአውቶቡስ ውስጥ በየትኛውም በሮች ለመክፈል የ ORCA ካርድዎን ይጫኑ።
የበለጠ ፍጥነት
አውቶቡሶች የበለጠ በፍጥነት በመምጣት ወጥ አገልግሎቶችን ያቀርባሉ።
በ2019 Metro የአውቶቡስ ጣቢያዎችን ለመለየት፣ የአውቶቡስ ፍጥነትና አስተማማኝነትን የሚያሻሽሉ ለውጦችን ለማቀድ፣ እና መንገዱን ለሰዎች ወደ አውቶቡሶች ለመድረስና ከአውቶቡሶች ለመውረድ ቀላልና አስተማማኝ የሚያደርጉ ለውጦችን ለማድረግ ከማህበረሰቡ ጋር በትብብር ሰርቷል።
የማህበረሰብ ተሳትፎ ለአጋው ድርጅቶች የተደረጉ ገለጻዎችን፣ ተራኪና የማህራሪያ ጽፉፍ የያዙ ገለጻዎችን በአማርኛ፣ ቻይኒኛ (በማንደሪን የተቃለለ ቻይኒኛ፣ በካንቶኒስና ማንደሪን የተቃለለ ቻይኒኛ የተደረገ ገለጻን)፣ በስፓኒሽ፣ ሱማሊኛ እና ቬትናሚኛ የተደረገ ገለጻን ያጠቃልላል።
በተጨማሪም ሁለት የቨርቹዋል የከተማ አዳራሽ ገለጻዎች ከቀጥታ የአማርኛ፣ ካንቶኒስ፣ ማንዳሪን፣ ሱማሊኛ፣ ስፓኒሽና ቬትናሚኛ የማስተርጎም አገልግሎቶች ጋር እንዲሁም በተለያዩ ቋንቋዎች የፕሮጀክቱን የተመለከተ መረጃ ማዘጋጀትና ማሰራጨት ነበሩ።
በ2020 በCOVID-19 ወረርሽኝ ምክንያት የተፈጠረው የገቢ መቀነስ Metroን የRapidRide R መስመርን የዲዛይን ስራ እንዲያቆም አስገድዶታል። ከመጋቢት 2020 እስከ ታህሳስ 2020 Metro የንድፈ ሀሳብ ዕቅዱን የተመለከተ መረጃ በኦንላይን አጋርቷል።
ምን እንደሰማን
ስራው ከመቆሙ በፊት Metro በደቡብ Seattle መንገድ ዙሪያ ከሚኖሩ፣ ከሚሰሩ እና በመንገዱ ላይ ከሚጓዙ የማህበረሰብ አባላት ግብረ መልስ ሰብስቧል። የሚከተሉት ከማህበረሰቡ የተሰበሰቡ ጭብጦች የRapidRide R መስመርን ዲዛይን ቅርጽ ለማስያዝ ረድቷል፥
ደህንነት እና ተደራሽነት
- በተለይም የመንቀሳቀስ ችግር ላለባቸው ሰዎች የተሻለ፣ አስተማማኝ የአውቶቡስ ጣቢያዎች ተደራሽነት
- የግል ደህንነትን የተመለከቱ ስጋቶች
ማህበረሰብ እና ስምሪት
- RapidRide ያልተለመደ ነው
- ማህበረሰብ እንዴት እና መቼ በውሳኔዎች ላይ ተጽእኖ ማሳደር እንደሚችል በግልጽ ማሳወቅ
- ክፍያዎችና የክፍያ አፈጻጸምን የተመለከተ ስጋት
የተሻሻለ አገልግሎት
- ለደቡብ S. Henderson Street አሽከርካሪዎች አገልግሎትን የተመለከቱ ስጋቶች
- በደቡብ Seattle ውስጥ አስተማማኝ አገልግሎት እና ከሌሎች የትራንዚት አማራጮች ጋር የተሻሻሉ ግንኙነቶች
- በመንገድ 7 ላይ ለወሳኝ አገልግሎቶች ተደራሽ የመሆን የማህበረሰብ እሴት
- በአውቶቡስ ጣቢያዎች መካከል ያለውን ርቀት የተመለከቱ ስጋቶች
- የማህበረሰብ አባላት በዝቅተኛ ደረጃ አገልግሎት ሲያገኙ የቆዩ በመሆኑ በተቻለ ፍጥነት የተሻሉ አገልግሎቶችን ማግኘት ይገባቸዋል
ምን እንደሰማን በተመለከተ እና ዝርዝር የተሳትፎ አሰራራችን፣ የቀደሙ ሪፖርቶችን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማወቅ መረጃውን ከእኛ የመረጃ ምንጭ ላይበራሪ ላይ ማግኘት ይችላሉ።
በ2023 የ Seattle የትራንስፖርት መምሪያ በRainier Avenue S ላይ የአውቶቡስ ብቻ መንገዶች እና አዲስ የትራፊክ ምልክቶችን፣ የእግረኛ መንገድ ማሻሻያዎችን፣ አዲስ የእግረኛ መንገድ ማቋረጫዎችን እና ADAን ያከበሩ የደረጃ መወጣጫዎችን ጨምሮ እንደ የመንገድ 7 – የትራንዚት ፕላስ መልቲሞዳል ኮሪደር ፕሮጀክት (በእንግሊዘኛ) አንድ ክፍል የተለያዩ የመንገድ ማሻሻያዎችን አድርጓል።
-
ከ2019 እስከ 2020
የእቅድ ዝግጅት: የንድፈ ሀሳብ ዕቅድ
Metro የአውቶቡስ ጣቢያዎች ዲዛይን ለማዘጋጀት፣ አውቶቡስን አስተማማኝ የሚያደርጉ ለውጦችን ለማድረግ፣ መንገዱን ለሰዎች ለእግር መንገድ፣ ለራይድ ወይም ለአውቶቡስ የበለጠ ቀላል የሚያደርጉ ለውጦችን ለማድረግ፣ እና በአውቶቡስ መጓዝን የበለጠ ምቹ የሚያደርጉ ለውጦችን ለማድረግ የማህበረሰብ አባላትን፣ ማህበረሰብ ተኮር ድርጅቶችን፣ የንግድ ድርጅቶችና የድርጅት አጋሮችን አሳትፏል።
ማስታወሻ፦ ፕሮጀክቱ በ2020 መጨረሻ ላይ በተሳፋሪዎች ደህንነት ላይ ለማተኮር እና በCOVID-19 ወረርሽኝ ምክንያት ከተፈጠረው የገቢ ማጣት ለማገገም ሲባል ቆሞ ነበር።
-
2024
የእቅድ ዝግጅት: የንድፈ ሀሳብ ዕቅድ ማሻሻያ
Metro ከSDOT ጋር በመተባበር ፕሮጀክቱን በ2025 እንደገና ለማስጀመር እየተዘጋጀ ነው። ማህበረሰቡን በማሳተፍ የአቀማመጥና የታቀዱ የአውቶቡስ ጣቢያዎች ቦታዎችን ጨምሮ በ RapidRide R መስመር የንድፈ ሀሳብ ዕቅድ ላይ ወቅታዊ መረጃ የምናጋራ ሲሆን ይህም ለወደፊት ስራችን መሰረት ይጥርልናል። አሁን ካለው መንገድ ጋር ተደጋጋሚ የመንገድ 7 የአውቶቡስ አገልግሎት የRapidRide R መስመር እስከሚጀምር ድረስ ይቀጥላል።
-
የወደፊት የፕሮጀክቱ ዙሮች
በወደፊት የዲዛይን ዙሮች ላይ የማህበረሰብ ተሳትፎ የሚቀጥል ሲሆን ይህም ቀስ በቀስ ወደ አዲስ የአውቶቡስ ጣቢያዎችን፣ የመንገድ ማሻሻያዎችን እና ሌሎች አስተማማኝ፣ ምቹ የRapidRide ተሞክሮ የሚፈጥሩ ክፍሎችን ወደመገንባት ያመራል።
የRapidRide R መስመር ትግበራ፥ የ R መስመር አገልግሎት የግንባታውን መጠናቀቅ ተከትሎ ይጀምራል።