Skip to main content
close

KingCounty.gov is an official government website. Here's how you knowexpand_moreexpand_less

account_balance

Official government websites use .gov

Website addresses ending in .gov belong to official government organizations in the United States.

lock

Secure .gov websites use HTTPS

A lock lock or https:// means you've safely connected to the .gov website. Only share sensitive information on official, secure websites.

Metro Flex

Metro Flex የእርስዎ በትዕዛዝ ላይ የተመሠረተ የአጎራባች አካባቢዎች የመጓጓዣ አገልግሎት ነው። በአንድ ቀላል መተግበሪያ - እና ጥቂት ጊዜ ነካ በማድረግ ብቻ - ሁሉም ከአውቶቡስ ጉዞ ተመሳሳይ ዋጋ ጋር፣ በአገልግሎት ክልል ውስጥ በማንኛውም ቦታ መጓዝ ይችላሉ። የ Metro Flex ምቹ፣ ፈጣን፣ ተመጣጣኝ መጓጓዣ በጣቶችዎ ጫፍ ላይ ነው።

Metro Flex ምንድን ነው

Metro Flex በበርካታ የ ኪንግ ካውንቲ ሰፈሮች ውስጥ መጓጓዣዎችን የሚያቀርብ በፍላጎት ላይ የተመሠረተ የመጓጓዣ አገልግሎት ነው። በዘመናዊ ምቹ ሚኒቫኖቻችን በአንድ ዝቅተኛ ዋጋ ወደሚፈልጉበት ቦታ ይድረሱ። ወደ ገበያ ይሂዱ፣ ለምሳ ከጓደኞችዎ ጋር ይገናኙ ወይም ወደ ቀጠሮዎች ይሂዱ። በአገልግሎት ክልል ውስጥ መድረሻዎ ምንም ይሁን ምን፣ Metro Flex ወደዚያ ይወስድዎታል።

  • ምቹ
    Metro Flex የት እንዳሉ እና የት መሄድ እንደሚፈልጉ ለመንገር ስልክዎን ይጠቀሙ። በቅርብ ርቀት እርምጃ ላይ የሚገኝ የመነሻ ቦታ ያገኛሉ።
  • ፈጣን
    ጉዞዎን ማስያዝ ፈጣን እና ቀላል ነው! መተግበሪያው ለእርስዎ Metro Flex ተሽከርካሪ የሚገመተውን የመድረሻ ጊዜ ይልክልዎታል።
  • ተመጣጣኝ
    Metro የአውቶቡስ ጉዞ ጋር በተመሳሳይ ወጪ በMetro Flex ይጓዙ። እና በ ORCA ካርድዎ ከ ወይም ወደ አውቶቡስ፣ Sound Transit Link ቀላል ባቡር ወይም Sounder በነጻ ማስተላለፍ ይችላሉ።
  • የጉዞ አማራጭ ማሳወቂያዎችን ያካትታል
    አዲሱ መተግበሪያ በእርስዎ የመነሻና እና የመድረሻ ቦታዎች ላይ በመመሥረት — የMetro Flex መጓጓዣ ይሁን ፣ በአውቶቡስ ላይ የሚደረግ ጉዞ ወይም ሌላ የመተላለፊያ አገልግሎት የእርስዎን ምርጥ የመተላለፊያ ምርጫዎች ይዘረዝራል።

Metro Flex መተግበሪያን ያውርዱ

Download the iOS appDownload the app from Google Play

ሰዓቶች እና ቦታዎች

Delridge/South Park

በስራ ቀናት ከጠዋት 6 ሰዓት እስከ ምሽት 11 ሰዓት

ቅዳሜና እሁድ ከጠዋት 6 ሰዓት እስከ ምሽት 11 ሰዓት

Issaquah/Sammamish

በስራ ቀናት ከጠዋት 7 ሰዓት እስከ ሰዓት 6 ሰዓት

ቅዳሜ ከጠዋት 9 ሰዓት እስከ ሰዓት 6 ሰዓት

Juanita

በስራ ቀናት ከጠዋት 7 ሰዓት እስከ ምሽት 7 ሰዓት

ቅዳሜና እሁድ ምንም አገልግሎት የለም

Kent

በስራ ቀናት ከጠዋት 5 ሰዓት እስከ ምሽት 7 ሰዓት

ቅዳሜና እሁድ ከጠዋት 7 ሰዓት እስከ ምሽት 7 ሰዓት

Northshore

በስራ ቀናት ከጠዋት 7 ሰዓት እስከ ምሽት 7 ሰዓት

ቅዳሜና እሁድ ምንም አገልግሎት የለም

Othello፣ Rainier Beach/Skyway፣ Renton Highlands እና Tukwila

በስራ ቀናት ከጠዋት 5 ሰዓት እስከ ሌሊት 1 ሰዓት

ቅዳሜ ከጠዋት 5 ሰዓት እስከ ሌሊት 1 ሰዓት

እሁድ ከጠዋት 6 ሰዓት እስከ ሌሊት 12 ሰዓት

የMetro Flex የበዓል ቀናት መርሃግብር

Metro Flex በአዲስ ዓመት ቀን፣ በመታሰቢያ ቀን፣ በነፃነት ቀን፣ በሠራተኞች ቀን፣ በምስጋና ቀን እና በገና ቀን በእሁድ የአገልግሎት መርሃ ግብር ይሠራል።

ተጨማሪ ዝርዝሮችን ለማግኘት የ Metro የበዓል ቀናት አገልግሎት ይመልከቱ።

እንዴት እንደሚጓጓዙ

ጉዞዎን በMetro Flex መተግበሪያ ሲያስይዙ፣ በጣም የተሟላ የጉዞ መረጃ ያገኛሉ። ይህ የቀጥታ ተሽከርካሪ ክትትልን እና ሌሎች የመጓጓዣ አማራጮችን ዝርዝር ያካትታል።

በመተግበሪያው ውስጥ

  • መተግበሪያውን ያውርዱ እና መገለጫዎን ያዋቅሩ። ማንኛውንም የመንቀሳቀስ ፍላጎቶችን ወይም ልዩ ክፍያዎችን ለማመልከት የእርስዎን “የክፍያ ዓይነት”(payment type) እና በመቀጠል “ታሪፍ/አገልግሎት ዓይነት” (fare/service type) የሚለውን ይምረጡ።
  • ለእርስዎ እና እስከ 4 ለሚደርሱ ሌሎች መንገደኞች መጓዣ ለመጠየቅ መተግበሪያውን ይክፈቱ።
  • የመድረሻ ሰዓት እና በአቅራቢያዎ የሚገኝ መነሻ ቦታ ያገኛሉ - በመነሻና መዉረጃ ቦታዎችአጭር የእግር ጉዞ ሊያስፈልግ ይችላል።

በዊል ቼር/ተሽከርካሪ ወንበር የሚደረስ ተሽከርካሪ የሚጠይቁ የመንቀሳቀስ ፍላጎቶች ካሎት፣ ይህንን መረጃ በMetro Flex መገለጫዎ ውስጥ ያካትቱ። ከዚያ በኋላ ለሁሉም ጉዞዎችዎ ተደራሽ የሆነ ተሽከርካሪ በቀጥታ ይመደብልዎታል እና ምንም የእግር ጉዞ አያስፈልግዎትም።

በስልክ

  • ለደንበኛ አገልግሎት በ206-258-7739 ይደውሉ እና የት እንዳሉ እና የት መሄድ እንደሚፈልጉ ያሳውቋቸው።
  • ስላሎት ማንኛውም የመንቀሳቀስ ፍላጎት እና ክፍያዎን እንዴት እንደሚከፍሉ መረጃ ያቅርቡ።
  • የመድረሻ ሰዓቱን እና ሹፌርዎን የት እንደሚያገኙ ወኪልዎ የጉዞዎን ዝርዝሮች ያቀርባል።

መስመር ላይ

  • መለያዎን ለመፍጠር እና/ወይም ወደ መለያዎ ለመግባት ወደ metroflex.app.ridewithvia.com tይሂዱ።
  • መነሻ እና መድረሻ ቦታዎን ያስገቡ፣ ቦታዎችን ያረጋግጡ (ወይም ካርታውን ሁለቴ ነካ ያድርጉ)።
  • ማንኛውም የመንቀሳቀስ ፍላጎት እና/ወይም ተጨማሪ ተሳፋሪዎችን በ“1 ተሳፋሪ”(1 Passenger) ተቆልቋይ ስር ያመልክቱ።
  • የጉዞ አማራጮችን ይገምግሙ እና “የጉዞዬን ቦታ ያስይዙ”(book my ride) የሚለውን ይምረጡ።
  • የመድረሻ ሰዓቱን እና ሹፌርዎን የት እንደሚያገኙ ጨምሮ የጉዞ ዝርዝሮችዎ ይደርሰዎታል።

ታሪፍ እና ክፍያ

Metro Flex የጉዞ ወጪ ከMetro አውቶቡስ ጉዞ ጋር ተመሳሳይ ነው። በሚሳፈሩበት ጊዜ ይክፈሉ ወይም ለአሽከርካሪዎ የክፍያ ማረጋገጫ ያሳዩ።

የአሁኑን Metro ታሪፎችን እና ክፍያን ይመልከቱ

ORCA ካርድ

ORCA ካርድ መጠቀም በMetro Flex እና አውቶቡሶች፣ Sound Transit Link ቀላል ባቡር ወይም Sounder መካከል ለመሸጋገር ያስችልዎታል። በORCA ካርድ የቦርድ ካርድ አንባቢን (በአሽከርካሪዎ ራስ መቀመጫ ጀርባ ላይ የሚገኘውን) ነካ ያድርጉ።

ስለ ORCA ካርዶች የበለጠ ይወቁ

Transit GO Ticket

በስልክዎ ላይ Transit GO Ticketን መጠቀም በMetro Flex እና በሌሎች Metro አውቶቡሶች መካከል ለመሸጋገር ያስችልዎታል። ወደ Link ቀላል ባቡር እና Sounder ባቡር የሚደረጉ ሽግግሮችአይሸፈኑም። የእርስዎን Transit GO Ticket (በስልክ መተግበሪያዎ ላይ) ለሹፌሩ ያሳዩ።

Transit GO Ticket የበለጠ ይወቁ

ክሬዲት ካርዶች፣ ዴቢት ካርዶች እና የቅድመ ክፍያ ካርዶች

ክፍያው ተቀባይነት የሚያገኘው በስልክ ከደንበኛ አገልግሎት ወኪል ጋር ወይም በMetro Flex መተግበሪያ በኩል ብቻ ነው። የመለያ መረጃን ወደ Metro Flex መተግበሪያ በማስገባት በክሬዲት ወይም በዴቢት ካርድ ይክፈሉ።

ይህ ዘዴ በሚከፈልበት Metro Flex ታሪፍ ወደ አውቶቡሶች፣ Link ቀላል ባቡር ወይም Sounder ለማስተላለፍ አይፈቅድልዎትም። በሌላ አገላለጽ፣ በሌሎች የመጓጓዣ ተሽከርካሪዎች ለመጓዝ እንደገና መክፈል ያስፈልግዎታል።

የተቀነሱ ታሪፎች

ሁሉም ነባር የ የኪንግ ካውንቲ ሜትሮ የተቀነሱ ዋጋ ፕሮግራሞች፣ ORCA LIFTን ጨምሮ፣ ተቀባይነት አላቸው።

ስለተቀነሱ ዋጋዎች የበለጠ ይወቁ

ማስተባበያ፦ መደበኛ የMetro ዋጋዎች ተፈጻሚ ናቸው። የገንዘብ ታሪፎች እና የወረቀት ዝውውሮች/ትኬቶች በMetro Flex ተሽከርካሪዎች ላይ ተቀባይነት የላቸውም። 18 እና ከዚያ በታች ያሉ ተጓዦች ሁልጊዜ በMetro Flex እና በክልሉ ውስጥ ባሉ ሌሎች መጓጓዣዎች ላይ በነጻ ይጓዛሉ።

ተደራሽነት

ለዊል ቼር/ተሽከርካሪ ወንበር የሚመች ተሽከርካሪ ከፈለጉ፣ ሌላ የመንቀሳቀስ ድጋፍ ከፈለጉ ወይም በአጭር ርቀት ለመራመድ ከተቸገሩ፣ እባክዎ ሁሉንም ፍላጎቶች በMetro Flex መገለጫዎ ውስጥ ያመልክቱ። ጉዞዎችን በስልክ ካስያዙ ስለግል ጉዞ ድጋፍ ፍላጎቶችዎ ለደንበኛ አገልግሎት ወኪልዎ ይንገሯቸው።

እባክዎ ያስተውሉ፣ ለእያንዳንዱ Metro Flex ተሽከርካሪ አንድ የዊል ቼር/የተሽከርካሪ ወንበር መንገደኛ ብቻ ነው የሚቀመጠው። በተሽከርካሪው የኋላ ክፍል ውስጥ የሚገኘው የዊል ቼር/ተሽከርካሪ ወንበር መወጣጫ እስከ 800 ፓውንድ እና እስከ 36 ኢንች ስፋት ያለው የዊል ቼር/ተሽከርካሪ ወንበሮችን ለማስተናገድ የተነደፈ ነው።

በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች

አይችሉም፣ ጉዞዎች በትዕዛዝ ሊጠየቁ የሚችሉት በመተግበሪያው ወይም በስልክ ብቻ ነው። ጉዞዎን ለማስያዝ ሲፈልጉ አስቀድመው ያቅዱ እና የሚገመተውን የመድረሻ ጊዜ (Estimated Time of Arrival, ETA) ያረጋግጡ። Metro Flex ተሽከርካሪዎች ከፍተኛ ተፈላጊነት ሲኖራቸው፣ ወደ እርስዎ እና ወደ እርስዎ አካባቢ ለመድረስ ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልጋቸዋል። ለትዕግስትዎ እናመሰግናለን።

Metro Flex በጣም ከፍተኛ ፍላጎት ካጋጠመው ወይም ሌላ መጓጓዣ ለዚህ ጉዞ የሚያገለግል ከሆነ የመጀመሪያ የጉዞ ጥያቄዎ ተቀባይነት ላይኖረው ይችላል። ግን እባክዎ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ እንደገና ይሞክሩ። አንዴ ሌሎች ተጓዦች ጉዟቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ጥያቄዎ ተቀባይነት ሊኖረው ይችላል።

ከአገልግሎት ክልል ውጭ ከሆኑ፣ Metro Flex አገልግሎት ስራ በዝቶበታል ወይም መተግበሪያው Metro Flex መድረሻዎ ላይ ለመድረስ ምርጡ መንገድ እንዳልሆነ ይወስናል፣ ሌሎች የጉዞ አማራጮች ይዘረዘራሉ፣ ለምሳሌ የአውቶቡስ እና የLink የቀላል ባቡር አገልግሎት።

Metro Flexን በተቻለ መጠን ቀልጣፋ ለማድረግ፣ መተግበሪያው ለሚነሱበትና ለሚወርዱበት ቦታ ቅርብ የሆኑ የማቆሚያ ቦታዎችን ይፈልጋል። አጭር ርቀት በእግር በመጓዝ እርስዎ እና ሌሎች ተጓዦች በMetro Flex ተሸከርካሪዎች ላይ የሚያጠፉትን ጊዜ ይቀንሳሉ - ያነሰ ጊዜ ማለት ተጨማሪ አገልግሎት ማለት ነው!

ማስታወሻ፦ የእንቅስቃሴ እክል ላላቸው—እና ለዘረዘሩ—እና ከ10 ፒ.ኤም እስከ 6 ኤ.ኤም ለሚጓዙ ማናቸውም መንገደኞች በእግር መጓዝ አያስፈልጋቸውም ። የእንቅስቃሴ ፍላጎቶችዎን በመተግበሪያዎ መገለጫ ወይም በስልክ ሲናገሩ ማመላከትዎን ያረጋግጡ።

የጉዞ ጥያቄዎን ለመላክ በስክሪን ገጹ ግርጌ ያለውን የ“መውረጃ ቦታ አዘጋጅ”(Set drop-off) ቁልፍን ነካ ያድርጉ። መተግበሪያው አቅራቦቶችን በመነሻ ቦታ እና በጉዞዎ ላይ ETA (የሚገመተው የመድረሻ ጊዜን) ይዘረዝራል። የተሰጠዎት የጉዞ ጊዜ ከ30 ሰከንዶች በኋላ ያበቃል:: ጉዞን ለመቀበል፣ የመረጡትን አማራጭ ይምረጡና “ይህን ጉዞ ያዝ”(Book this ride) የሚለውን ቁልፍ ነካ ያድርጉ።

Metro Flex ለዊል ቼር/ተሽከርካሪ ወንበር ተደራሽ የሆኑ ተሽከርካሪዎች አሉት። ለዊል ቼር/ተሽከርካሪ ወንበር ተደራሽ ተሽከርካሪ የሚፈልጉ ተሳፋሪ ከሆኑ፣ እባክዎ ይህንን ምርጫ በMetro Flex መተግበሪያዎ ውስጥ ባለው “ታሪፍ/አገልግሎት ዓይነት”(fare/service type) ክፍል ወይም በስልክ ጉዞ ሲጠይቁ ያስቀምጡ።

አዎ! ጉዞዎን ከማስያዝዎ በፊት፣ ከ“ለብቻዎት ነው የሚጓዙት?”(Traveling alone?) ጥያቄ በኋላ “+” የሚለውን ቁልፍ ነካ ያድርጉ። “ብስክሌት ለማከል” (Add a bike) ወደ የአማራጮች ዝርዝር ወደ ታች ያሸብልሉ። የብስክሌት መደርደሪያ የያዙ ተሽከርካሪዎቻችን እንዲላኩልዎ ለማድረግ ይህን አማራጭ ይንኩ።

የእርስዎን Metro Flex ጉዞ ስለሰረዙ ምንም ቅጣት የለም። ነገር ግን፣ የጉዞ ስረዛ ለሌሎች ተሳፋሪዎች አላስፈላጊ መዘግየቶችን ያስከትላል—እባክዎ አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር ከመሰረዝ ይቆጠቡ።

አዎ፣ ለልጆች ይፈቀዳል! እና ያስታውሱ፣ 18 አመት ወጣቶች እና ከዚያ በታች በMetro Flex እና በክልሉ ውስጥ ባሉ ሌሎች መጓጓዣዎች ላይ በነጻ መጓዝ ይችላሉ። እባክዎ ለትንንሽ ልጆች የሚያስፈልጋቸውን የመኪና ውስጥ የልጆች መቀመጫ/car seat/booster ይዘው ይምጡ—እነዚህ የደህንነት ገደቦች ይመከራሉ ነገር ግን አስፈላጊ አይደሉም። ሁሉም ልጆች፣ እድሜያቸው ምንም ይሁን ምን፣ ጉዞዎን በሚያስይዙበት ጊዜ እንደ “ተጨማሪ ተሳፋሪ”(additional passenger) መገለጽ አለባቸው። እና እያንዳንዱ ተሳፋሪ ብቻውን ለመጓዝ ቢያንስ 13 አመት መሆን አለበት።

የአገልግሎት እንስሳት በMetro Flex ተሽከርካሪዎች ውስጥ ያለ ገደብ እንዲጓዙ ይፈቀዳል። ሌሎች ውሾች እና ድመቶች ለመሳፈር ለአየር መንገድ በተፈቀደው መያዣ ውስጥ መሆን አለባቸው።

Metro Flex ጉዞዎች የጋራ እንደመሆናቸው መጠን ፣ እያንዳንዱ ተሳፋሪ የግል ዕቃዎችን በአንድ ሻንጣ ወይም በተመጣጣኝ መጠን እንዲገድብ ይጠየቃል። እቃዎ ቦታ የማይበቃው ከሆነ Metro Flex ለጉዞዎ ዋስትና ሊሰጥ አይችልም።

ምንም እንኳን የMetro Flex aመተግበሪያ የመክፈያ ዘዴዎን ቢጠይቅም፣ የORCA ካርድዎ ከተሽከርካሪው የቦርድ አንባቢ ጋር እስካልተነካካ ድረስ ክፍያ አይሰበሰብም።

አይጨነቁ—አሁንም በMetro Flex መተግበሪያ ውስጥ የመገለጫ ቅንጅቶችን በማዘመን በቅናሽ ዋጋ መጓዝ ይችላሉ። የታሪፍ አይነትዎን ለመምረጥ ከላይ በግራ በኩል ያለውን “ምናሌ”(Menu) የሚለውን ቁልፍ ይንኩ እና “ታሪፍ/የአገልግሎት ዓይነት”(Fare/Service Type) የሚለውን ይምረጡ። ከተቆልቋይ ምናሌው ትክክለኛውን የታሪፍ አይነት ይምረጡ። ክፍያ የሚከናወነው በቦርድ ላይ ስለሆነ፣ የእኛ ORCA ካርድ አንባቢዎች የተቀነሰ የታሪፍ ORCA ካርድ እንዳለዎት ወዲያውኑ ያውቃሉ እና ደረሰኙ የሚናገረው ምንም ይሁን ምን ትክክለኛውን የተቀነሰ ዋጋ ያስከፍልዎታል።

Metro Flex Access On-Demand ቅድመ ብቃት ላላቸው የAccess ደንበኞች የሙከራ ፕሮግራም ነው። በMetro Flex ቫኖች ውስጥ በተጠቀሰው የአገልግሎት ክልል ውስጥ በተመሳሳይ ቀን በፍላጎት ተደራሽ ጉዞዎችን ያቀርባል። ተሳፋሪዎች ለመጓጓዣ ቦታ ከያዙ በ30 ደቂቃዎች ውስጥ ይወሰዳሉ፣ እና ጉዞዎች ሊጋሩ ይችላሉ። በሙከራው ደረጃ ላይ፣ Metro የተወሰኑ Access ደንበኞችን Metro Flex Access On-Demandን እንዲሞክሩ ይጋብዛል ።

የበለጠ ለመረዳት

expand_less