Skip to main content
King County logo

ሙሉ በሙሉ ክትባቱን ያልወሰደ ማንኛውም ሰው የስቴትቱን የጤና መምሪያ (State Department of Health ) ትእዛዝ ማክበር አለበት። መመሪያው ሙሉ በሙሉ ላልተከተበ ሰው እንደዚህ ይላል፥ በማንኛውም ዝግ የሆነ የህዝብ ቦታዎች ላይ ወይም ክፍት ቦታዎች ላይ ከ6 ሜትር በላይ የአካል ርቀት መጠበቅ በማይቻልበት ቦት ላይ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ (ማስክ) የማድረግ ግዴታ አለበቸው።

ጭምብል ማድረግና አካላዊ ርቀት መጠበቅ የሚኖርብን ቦታዎች:
ቦታ ሙሉ በሙሉ የተከተበ (የክትባት ተከታታይን ካጠናቀቁ ከሁለት ሳምንት በኋላ) በከፊል የተከተበ ወይም ምንም ያልተከተበ
በሰው የተጨናነቁ ህዝባዊ ቦታዎች (ከቤት ውጭ ዝግጅቶች፣ የተጨናነቁ ጎዳናዎች ወይም ዱካዎች)  
(ስድስት ጫማ ርቀት መቆየት ባልተቻለበት ጊዜ)
የቤት ውስጥ ህዝባዊ ቦታዎች  
የቤት ውስጥ ህዝባዊ ቦታዎች የንግድ ባለቤቶች ለሁሉም ሰው ጭምብል እንዲደረግ የሚያዙበት
ሆስፒታሎች፣ የእንክብካቤ ማዕከሎች፣ የዶክተሮች ቢሮ፣ ማረሚያ ቤቶች፣ ትምህርት ቤቶች፣ የህዝብ ትራንስፖርቶች ላይ

ሙሉ በሙሉ የተከተቡ ሰዎች እንደፍላጎታቸው ጭምብል ማድረጉን ሊቀጥሉ ይችላሉ፣ በተለይም ያልተከተቡ ሰዎች፣ ተጓዳኝ በሽታ ያለባቸው፣ ህፃናት እና እድሜያቸው ለክትባት ያልደረሰ አከባቢ ማስክ ሊያረጉ ይችላሉ። 300,000 የሚጠጉ ልጆች ጨምሮ ሁሉም ሰው አይደለም የተከተበው ስለዚህም ማንኛውም ሰው የማስክ መመሪያ እንዲሁም የሲዲሲ የጉዞ መመሪያንም መከተል ይኖርበታል።

ይሕ መመሪያ ዕድሜአቸው ከ16 ዓመት እና ከዚያ በላይ ለሆኑ የኪንግ ካውንቲ ነዋሪዎች እስከ 70% ወይም ሙሉ በሙሉ ክትባት እስኪወስዱ በሥራ ላይ ይውላል።

የዩኤስ የበሽታ ማእከል (ሲዲሲ) ማዕከላት በቅርቡ መመሪያውን አሻሽሎ ሙሉ በሙሉ ክትባት ያገኙ ሰዎችን በብዙ ቦታዎች ላይ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ (ማስክ) ማድረግ እንደሌለባቸው በቅርቡ አሳውቇል፡፡ በቀጣይ የሲዲሲ ዳይሬክተር ሮችሀል ዋለንስኪ እና የዋሽንግተን ግዛት የጤና ጥበቃ መምሪያ ክፍል ግን በማንኛውም ዝግ የሆኑ የህዝብ ቦታዎች ላይ የአፍና የአፍንጫን መሸፈኛ (ማስክ) የመጠቀምን ትዕዛዝ ለመከልከል የአከባቢው የኮቪድ፡ 19 መጠን እና የህዝብ ክትባት መጠኖች መታየት እንዳለበት አብራርቷል፡፡

በኪንግ ካውንቲ ውስጥ ስለሚሆኑት ነገሮች ጥያቄ ካሎት፣ እባክዎ በኪንግ ካውንቲ የኮቪድ፡ 19 የጥሪ ማዕከል ከጥዎቱ 8 ሰዓት እስከ ምሽቱ 7 ሰዓት ድረስ ይደውሉልን። ከሰኞ እስከ አርብ በ 206-477-3977 ይደውሉልን፡፡ የቋንቋ ድጋፍ አለን፡፡