Skip to main content
King County logo

መቼ ነዉ ለብቻ መቆየት ያለብኝ?

COVID-19 ካለዉ ሰዉ ጋር በቅርበት የተገናኙ ሰዎች በ CDC እና የማህበረሰብ ጤና መመሪያ መሠረት ምርመራ ማድረግ እና የለይቶ ማቆያ ቦታ (ካለዎት ቤትዎ ዉስጥ ወይንም በመንግስት የሚመራ ወይም ከተገኘ ለህዝብ ጥቅም የቀረበ ቦታ ዉስጥ) መሆን አለባቸዉ።

የምርመራ ዉጤትዎ አዎንታዊ ከሆነ ተለይቶ መቆየት አለብዎት።

COVID-19 ካለዉ ሰዉ ጋር በቅርበት ከተገናኙ እና ምልክቶች ከሌለዎት፡

 • ግንኙነቱ ካለቀበት ግዜ ጀምሮ ለ 14 ቀናት ለይቶ ማቆያ ዉስጥ ይቆዩ። ይህ በጣሙን ደህና አማራጭ ነዉ።
 • ይህ ካልተቻለ ሌላ ምርመራ ሳያደርጉ ግንኙነቱ ካለቀበት ግዜ ኣንስቶ ለ 10 ቀናት ለይቶ ማቆያ ዉስጥ ይቆዩ።

የመጀመሪዎቹ ሁለቱ አማራጮች ካልተቻሉ እና የምርመራ ዉጤትዎ አሉታዊ ከሆነ፡ ግንኙነቱ ካለቀበት ግዜ ኣንስቶ ለ 7 ቀናት ለይቶ ማቆያ ዉስጥ ይቆዩ (ግንኙነቱ ካቆመበት ግዜ ቢያንስ 5 ቀናት ጠብቀው ይመርመሩ)። ይህ አማራጭ በምርመራ ኣቅርቦት መኖርና ኣለምኖር ይመረኮዛል። በአንዳንድ ሁኔታዎች ደግሞ እንዲወሰድ ላይመከርም ይችላል።


የ COVID-19 ክትባት ሙሉ በሙሉ ወስጄ ከሆነስ?

ሙሉ ክትባት ወስደዉ ከሆነ COVID-19 አለዉ ተብሎ ከሚጠረጠር ወይም ከተረጋገጠ ሰዉ ከተጋለጡ በኋላ ተለይቶ መቆየት አያስፈልግዎትም፡ ምልክቶች ካላሳዩ በቀር።

ከተጋለጡ በኋላ በ 14 ቀናት ዉስጥ ምልክቶች ካሳዩ ራስዎን ከሌሎች ያግልሉ እና ለኮቪድ-19 ለመታየት ከሃኪምዎ ጋር ይነጋገሩ። ሃኪምዎ ስለወሰዱት ክትባት እና/ወይም ቀድሞ በበሽታው ስለመያዝዎ ሁኔታ ይጠይቅዎታል። ለ SARS-CoV-2 ስለመመርመር ወይም መገለልን ቀደም ብሎ ስለማቆም ጨምሮ ስለ ቀጣይ እርምጃዎች ያነጋግርዎታል።

ከተጋለጡ በኋላ ምልክቶች ካላሳዩ፡ ምልክቶች እንዳይታይብዎ ለ 14 ቀናት ይከታተሉ ግን ለይቶ ማቆያ መግባት ወይም መመርመር አይኖርብዎትም።

*ከተጋለጡ በኋላ ምልክቶች ካላሳዩ፡

 • ሁለቴ መወሰድ ላለባቸው እንደ Pfizer ወይም Moderna፡ ሁለተኛው ክትባት ከወሰዱ ከ2 ሳምንታት በኋላ ወይም
 • ኣንዴ መወሰድ ላለባቸው እንደ የጆንሶን ኤንድ ጆንሶን ጃንሰን (Janssen) ኣንዱን ክትባት ከወሰዱ ከ2 ሳምንታት በኋላ።

ክትባት ከወሰዱ ገና 2 ሳምንት ያልሞላ ከሆነ ወይም ሁለተኛውን መጠን (ዶዝ) ለመውሰድ እየተጠባበቁ ከሆነ ሰውነትዎ ገና ሙሉ ለሙሉ ኣልተጠበቀም ያለው። ሙሉ በሙሉ ክትባት ወስደው እስኪጨርሱ ድረስ ከላይ ያለዉን የለይቶ ማቆያ መመሪያዎችን ጨምሮ ሁሉንም የመከላከያ እርምጃዎችን መዉሰድ ይቀጥሉ።

የተረጋገጠ ወይም ኮቪድ-19 እንዳለዉ ከተጠረጠረ ሰዉ በመቅረብ ከተጋለጡበት ቀን በኋላ ለ14 ቀናት ተለይቶ መቆየት እና ለኮቪድ-19 መመርመር ያስፈልግዎታል። ለዚህ ምክንያት የሆነው፡ ብዙ ሰው ኣንድ ቦታ የሚቀመጡባቸው ቦታዎች፡ ከፍተኛ የነዋሪዎች መቀያየር ስላለ፣ ከፍተኛ የህመሙ ተላላፊነት ስለሚኖር እና ነዋሪዎች የሚፈለገውን መራራቅ እንዲኖራቸው ለማስከበር በጣም ኣስቸጋሪ ስለሆነ ነው።

ምልክቶች ካላሳዩ በቀር የተረጋገጠ ወይም ኮቪድ-19 እንዳለዉ ከተጠረጠረ ሰዉ በመቅረብ ከተጋለጡ በኋላ ተለይቶ መቆየት አያስፈልግዎትም። በእንዲህ ዓይነት ሁኔታዎች ምርመራ እንዲያደርጉ ይመከራል።

የጤና እንክብካቤ የሚሰጥበት ቦታ የሚኖሩ ከሆነ፥ ሙሉ በሙሉ ክትባት የወሰዱ ቢሆንም ለ 14 ቀናት ተለይተዉ መቆየት ይኖርብዎታል።

የጤና እንክብካቤ የሚሰጥበት ቦታ የሚሰሩ ከሆነ፥ ሙሉ በሙሉ ክትባት የወሰዱ ሰራተኞች እና ምልክት የማያሳይ ከሆኑ፡ ስራ ከመሄድ መገደብ የለብዎትም። እዚህ በ ሲ ዲ ሲ መግለጫ የተሰጠባቸው ልዩ ሁኔታዎች (ኤክሰፕሽን) ሊኖሩ ይችላሉ።

ለተጨማሪ መምርያ የ ሲ ዲ ሲ ክትባት ለወሰዱ የጤና እንክብካቤ ሰራተኞች መመርያ ይጎብኙ። (ድሕረ-ገጽ በእንግሊዝኛ)

ሙሉ በሙሉ ክትባት ቢወስዱም፡ በ ሲ ዲ ሲ መመርያ መሰረት የተሟላ የሰውነት የመከላከል ኣቅም ላይሰጥዎ ይችላል። ሓኪምዎን ያነጋግሩ። ክትባት ከወሰዱ በኋላም ኣስፈላጊ የሚባሉ ቅድመ-ጥንቃቄዎች መውሰዱን መቀጠል ይኖርብዎታል።

ከጉዞ በኃላ ለብቻ መለየት (ኳራንቲን ማድረግ) ይኖርብኛል? ክትባት ወስጄ ከሆነስ?

ክትባት ወስደው ቢሆኑም፡ የኮቪድ-19 ስርጭት ለመቀነስ እንዲረዳ ኣስፈላጊ ያልሆኑ ጉዞዎችን ከመውሰድ እንዲቆጠቡ እንመክራለን።

ለጉዞ ዝግጁ ከሆኑ፡ የያንዳንዱ የጉዞ ቦታና የክትባት ሁኔታ መሰረት ያደረጉ የ ሲ ዲ ሲ ምክሮች ቀጥለው ተዘርዝረዋል። ክትባት ቢወስዱም ባይወስዱም፡ የጉዞ ቦታዎ የትም ይሁን የት፡ በጉዞ ወቅት እያንዳንዱ ግለሰብ ለ 14 ቀናት ምልክቶቹን መከታተል እና ማስክ መልበስ ይኖርበታል።

የኣገር ውስጥ ጉዞ:

የኣገር ውስጥ ጉዞ ምክሮች እና ግዴታዎች ክትባት ያልወሰዱ ሙሉ በሙሉ ለተከተቡ*
ከመጓዝዎ ከ 1-3 ቀናት ኣስቀድመው ይመርመሩ።  
ከጉዞ 3-5 ቀናት በኋላ ይመርመሩና ለ 7 ቀናት ለብቻ ይቆዩ። ካልተመረመሩ ለ 10 ቀናት ለብቻ ይቆዩ።  
ምልክቶችዎን ራስዎ ይከታተሉ።
በጉዞ ወቅት ማስክ ይልበሱ፡ እንዲሁም ሌላ ኣስፈላጊ ቅድመ-ጥንቃቄ ይውሰዱ።

ከኣገር ውጭ ጉዞ፥

ከኣገር ውጭ ጉዞ ምክሮች እና ግዴታዎች ክትባት ያልወሰዱ ሙሉ በሙሉ ለተከተቡ*
ለጉዞ ከ ዩ ኤስ ከመውጣትዎ ከ 1-3 ቀናት ኣስቀድመው ይመርመሩ።  
ወደ ዩ ኤስ ከመብረርዎ ግዴታ መመርመር ኣለብዎት።
ከጉዞ ከ 3-5 ቀናት በኋላ ይመርመሩ።
ከጉዞ በኋላ ምርመራ ወስደው ኔጋቲቭ ከሆነ ለ 7 ቀናት፡ ምርመራ ካላደረጉ ደግሞ ለ 10 ቀናት ለብቻ ይቆዩ።  
ምልክቶችዎን ራስዎ ይከታተሉ።
በጉዞ ወቅት ማስክ ይልበሱ፡ እንዲሁም ሌላ ኣስፈላጊ ቅድመ-ጥንቃቄ ይውሰዱ።

*ግለሰቦች ሙሉ በሙሉ ክትባት ወስደዋል የሚባሉት፥

 • 2ኛው መጠን(ዶሴ) ክትባት ከወሰዱ ከ2 ሳምንታት በኋላ - እንደ ፋይዘርና ሞዴርና ሁለቴ ለሚወሰዱ ክትባቶች፡ ወይም
 • ነጠላውን መጠን ክትባት ከወሰዱ ከ2 ሳምንታት በኋላ - እንደ ጆንሶን ኤንድ ጆንሶን ያሉ ኣንዴ ብቻ የሚወሰዱ ክትባቶች።

እነዚህ መስፈርቶች ካላሟሉ ሙሉ በሙሉ ክትባቱን ወስደዋል ሊባል ኣይቻልም።

በቅርብ ከኮቪድ-19 ድኜ ከሆነስ?

በላቦራቶሪ ከተረጋገጠ የኮቪድ-19 ህመም በቅርብ ድነዉ ከሆነ ለአዲስ ኮቪድ-19 ከተጋለጡ በኋላ ተለይተዉ እንዲቆዩ አይጠየቁም - የሚከተሉት ከሆነ፡

 • ለመጀመሪያዉ በላቦራቶሪ ለተረጋገጠው የኮቪድ-19 ሕመም የመገለል ግዜዎን ጨርሰዉ ከሆነ እና
 • ከመጀመሪያዉ አዎንታዊ የምርመራ ዉጤትዎ (ምልክት የማይታይብዎት ከሆነ) ወይም ምልክቶች መታየት ከጀመሩ 90 ቀናት ያልሞላ ከሆነ እና
 • ከአሁኑ የኮቪድ-19 መጋለጥ በኋላ ምንም ምልክቶች ከሌለብዎት

ከአዲስ መጋለጥ በኋላ በ 14 ቀናት ዉስጥ አዲስ የኮቪድ-19 ምልክቶች ካሳዩ እና ከላይ ያሉትን የመጀመሪያዎቹን ሁለት መስፈርቶች ብቻ የሚያሟሉ ከሆነ ከሌሎች መገለል እና ለኮቪድ-19 ለመታየት ሃኪምዎን ማነጋገር አለብዎት። ሃኪምዎ ክትባቱን ወስደው እንደሆነ ወይም ቀድሞ በኮቪድ-19 በሽታ ተይዘው እንደሆነ መጠየቅ አለበት። ምርመራ ስለማድረግ ወይም ቀደም ብሎ መገለልን ስለማቆም ጨምሮ ስለ ቀጣዩ እርምጃዎች ከርስዎ ጋር ይነጋገራሉ።

ከዚህ ቀደም ኮቪድ ይዞኛል ብለው የሚጠረጥሩ ከሆነ ሆኖም ግን በላቦራቶሪ የተረጋገጠ ዉጤት ከሌለዎት ተለይቶ መቆየት አለብዎት (ከላይ ያለዉ “መቼ ነው ለብቻ መቆየት ያለብኝ?” ክፍል ይመልከቱ) እና ኮቪድ-19 አለዉ ተብሎ ከሚጠረጠር ወይም ከተረጋገጠ ሰዉ እንደ አዲስ ከተጋለጡ በኋላ ምልክቶች ባያሳዩም ይመርመሩ።


መገለል የሚያስፈልገኝ መቼ ነዉ?

የኮቪድ-19 ምርመራ ዉጤታቸዉ አዎንታዊ የሆኑ ሰዎች ሁሉ መገለል እና ተለይተው መቆየት አለባቸዉ፡ ክትባቱ ወስደውም ቢሆን።

ህክምና ለማግኘት ካልሆነ በቀር ከቤትዎ ወይም ማገገሚያ ቦታ ኣይውጡ። ምልክቶች ላለባቸዉ ግለሰቦች መገለልን ማቋረጥ ያላባቸዉ የሚከተሉት ከተሟሉ ብቻ ነው፡

 • ያለ ትኩሳት ቢያንስ 24 ሰዓታት ካለፉ (ያለምንም የትኩሳት ማስታገሻ መድኃኒት) እና
 • ምልክቶቹ ለመጀመሪያ ጊዜ ከታዩ ቢያንስ 10 ቀናት ካለፉ እና
 • ሌሎች ምልክቶች ከተሻለብዎ

የምርመራ ዉጤት አዎንታዊ ሆኖ ምንም ምልክቶች ላልነበራቸዉ ግለሰቦች የመጀመሪያ አዎንታዊ የኮቪድ ምርመራ ዉጤት ካገኙበት ቢያንስ 10 ቀናት ካለፈ እና ምንም ቀጣይ ሕመም ካላሳዩ መገለልን ያቋርጡ።


ለመገለል ወይንም ተለይቶ መቆያ ቦታ ለማግኘት እርዳታ ካስፈለገኝስ?

በራሳቸዉ፡ ዋስትና በተሞላበት እቤታቸው ውስጥ ተገልለው ወይም ተለይተዉ መቆየት ላልቻሉ ወይም ቤት ለሌላቸዉ፡ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ንጹህ፣ እና ምቹ ቦታ ለማቅረብ የመገለያ እና ተለይቶ መቆያ ማዕከላት አሉ። እነዚህ ቦታዎች ነጻ እና ለሁሉም ምስጥራዊነታቸዉ የተጠበቀ ሆኖ ቆይታችሁን ከማህበረሰብ ጤና ዉጪ ለማንም ርፖርት አይደረግም።

አገልግሎቶችን ለማግኘት የኪንግ ካዉንቲ ኮቪድ-19 ጥሪ ማዕከል 206-477-3977 በየቀኑ ከ 8AM እስከ 10 PM በመደወል የመገለል እና ተለይቶ መቆየት አገልግሎቶች ለርስዎ ትክክለኛ መፍትሔ መሆኑን ይጠይቁ። የትርጉም ኣገልግሎት አለ።

ስለ ኪንግ ካዉንቲ መገለል እና ተለይቶ መቆየት ድጋፍ አገልግሎቶች ከዚህ የበለጠ ይወቁ


የአከባቢ ጤና ኦፊሰር መመሪያ እና ትዕዛዝ

ከማርች 28 2020 ጀምሮ የኮቪድ-19 ምርመራ ዉጤታቸዉ አዎንታዊ የሆነ ወይም የኮቪድ-19 ምልክቶች የታየባቸው ግለሰቦች እና የምርመራ ዉጤታቸዉ በመጠባበቅ ላይ ያሉ ከላይ እንደተገለጸዉ ተጨማሪ ስርጭትን ለመቀነስ ተለይተዉ መቆየት ወይም መገለል ኣለባቸው። ተገዥ ያልሆኑ ግለሰቦች በ RCW 70.05.070 (2)-(3) እና WAC 246-100-036 (3) (የህግ መረጃ በእንግልዝኛ ብቻ) ሥር ባለዉ የማህበረሰብ ጤና ስልጣን መሠረት ያለዉዴታ ሊታሰሩ ይችላሉ ።


የተለይቶ መቆየት ወይም መገለል መስፈርቶችን ጨምሮ ለበለጠ መረጃ ለተጨማሪ ዝርዝር የትዕዛዙን ማጠቃለያ ይመልከቱ