Skip to main content

COVID-19 ምርመራ

COVID-19 ምርመራ

ይመርመሩ

የህመም ስሜት ከተሰማዎት ወይም የ COVID ምልክቶች ካጋጠሙዎት፣ ክትባቱን ቢወስዱም እንኳን ወዲያውኑ ምርመራ ያድርጉ። አዎንታዊ ምርመራ ካደረጉ፣ አብዛኛዎቹን የ COVID መዳኒቶች ህመሙ በተሰማዎት በ5 ቀናት ውስጥ መጀመር አለብዎት።

መዝገበ ቃላት

 የቃላቶቹን ትርጉም ለማግኘት ከዚህ በታች ያሉትን መግቢያዎች ይምረጡ

አንቲጂን ራስን መመርመሪያዎች አንዳንድ ጊዜ “ፈጣን መመርመሪያ” ወይም “የቤት ውስጥ መመርመሪያ” በመባል ይጠራሉ፤ በሰውነት ውስጥ የቫይረስ ፕሮቲኖችን ለይተው ያውቃሉ። አንቲጂን የራስ-ምርመራዎች ከምራቅ እና ከአፍንጫ ቀዳዳዎች የሚገኙ ናሙናዎችን ይጠቀማሉ። ውጤቶቹን ለማወቅ ከ15-30 ደቂቃዎች ይወስዳል።

የተወሰኑ የሰዎች ቡድኖች ለCOVID-19 ከፍተኛ ተጋላጮች እንደሆኑ ተደርገው ይወሰዳሉ፣ በጠና የመታመም ዕድላቸው ሰፊ ስለሆነ። እነሱም ከ60 ዓመት በላይ የሆኑ፣ ያልተከተቡ፣ የጤና ችግር ያለባቸው ሰዎች እና ነፍሰጡሮች ከፍተኛ ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ።

ከፍተኛ ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች ህክምናው ቀደም ብሎ ሲጀመር በጣም ውጤታማ ስለሆነ ቫይረሱ እንዳለባቸው በምርመራ ካረጋገጡ ወዲያውኑ ከጤና አቅራቢዎቻቸው ጋር መነጋገር አለባቸው።

ከሌሎች ተነጥሎ መቆየት ማለት COVID-19 ከሌላቸው ሰዎች ሁሉ ተነጥለው መቆየት ማለት ነው፣ እቤት ውስጥ ቢሆንም።

የሞለኪውላር ምርመራዎች የ COVID-19 ዘረመል መጠን (ጄኔቲክ ቁስ) በሰውነት ውስጥ መኖሩን ይለያሉ። እነዚህ ምርመራዎች የሚከናወኑት ከአፍንጫ ቀዳዳዎች በተሰበሰቡ ናሙናዎች ላይ ነው. እነዚህ ምርመራዎች “PCR” እና “TMA” ን ያካትታሉ።

ከሌሎች ተገልለው መቆየት ማለት ከቤትዎ ውጭ ካሉ ሰዎች ርቀው ያለ ምንም እንግዳ ወይም ጠያቂ በቤት ውስጥ መቆየት ማለት ነው። ወደ ሥራ፣ ትምህርት ቤት ወይም የሕዝብ ቦታዎች አይሂዱ። በተቻለ መጠን እቤትዎ ውስጥ ከሚኖሩት ለCOVID-19 ከፍተኛ ተጋላጭ ከሆኑ ሰዎች (ለምሳሌ ካልተከተቡ፣ አረጋውያን ወይም የጤና ችግር ካለባቸው ሰዎች) ይራቁ።

በተለያየ ጊዜ እየተደጋገመ የሚደረግ ምርመራ ተከታታይ ምርመራ ይባላል። አንዳንድ በራስ የሚደረጉ ምርመራዎች በ24 እስከ 48 ሰአታት ልዩነት ውስጥ በተከታታይ ተደጋግመው ጥቅም ላይ እንዲውሉ ተደርገው የተሰሩ ናቸው። በአንድ ጊዜ ከሚደረግ ምርመራ ይልቅ በተከታታይ የሚደረግ ምርመራ በCOVID-19 የቅርብ ግንኙነት ምክንያት የሚመጡትን ኢንፌክሽኖችን የማወቅ ዕድሉ ከፍተኛ ሊሆን ይችላል።


መመሪያ

 • የCOVID-19 ምልክቶች ካለብዎ የክትባት ሁኔታዎ ምንም ይሁን ምን በተቻለ ፍጥነት ይመርመሩ። ለመመርመር ወደ ሆስፒታል ድንገተኛ ክፍል ወይም አስቸኳይ እንክብካቤ ማእከል አይሂዱ።
 • ለበሽታው ከተጋለጡ ማለትም COVID-19 ካለው ሰው ጋር የቅርብ ግንኙነት ካደረጉ (በሽታው ከያዘው ግለሰብ ጋር በ24 ሰአት ውስጥ ለ 15 ደቂቃ ወይም ከዚያ በላይ በ 6 ጫማ ርቀት ውስጥ አብረው ከቆዩ) ለበሽታው ከተጋለጡ ከ5 ቀናት በኋላ የክትባት ሁኔታዎ ምንም ይሁን ምን ምርመራ ያድርጉ። የሕመሙን ምልክቶች ካዩ 5ቱን ቀናት አይጠብቁ፣ ከሱይ ይልቅ ወዲያውኑ ይመርመሩ። ቀደም ብለው ተመርምረው ከሆነ እንደገና ለመመርመር ያስቡ።
 • በትምህርት ቤትዎ፣ በስራ ቦታዎ፣ በጤና እንክብካቤ አቅራቢዎ፣ በስቴትዎ ወይም በአካባቢዎ የጤና ክፍል እንዲመረመሩ ከተጠየቁ
 • ሁሉም ተጓዦች የክትባት ሁኔታቸው ምንም ይሁን ምን ምርመራ ሊደረግላቸው ይገባል። የበለጠ ለቫይረሱ የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ በሆነ ሁኔታ ለምሳሌ በተጨናነቁ ቦታዎች ላይ በመሆን እና በደንብ የሚከላከል ጭንብል ሳይለብሱ ከተጓዙ።

COVID-19 እንዳለቦት ለማወቅ የሚረዳዎት ሁለት ዋና ዋና የምርመራ ዓይነቶች አሉ:

 • አንቲጂን (በራስ የሚደረግ ምርመራ)
 • ሞለኪውላር (የPCR ወይም NAAT ምርመራ)
 1. ከጤና እንክብካቤ አቅራቢዎ፣ ከክሊኒክ፣ ከምርመራ ቦታ ወይም ከላብራቶሪ በኩል የአንቲጂን እና የPCR/NAAT ምርመራዎችን ማግኘት ይችላሉ።
 2. በኪንግ ካውንቲ ውስጥ ነፃ ወይም ዝቅተኛ ዋጋ ያለውን የምርመራ ጣቢያ፣ ክሊኒክ ወይም ላብራቶሪ ያግኙ። መታወቂያዎን እና (ኢንሹራንስ ካለዎት) የኢንሹራንስ ካርድዎን እንዲያቀርቡ ይጠየቃሉ፣ ነገር ግን ለመመርመር የግድ እነዚህን ማሟላት አያስፈልጎትም።

 3. በቤት ውስጥም አንቲጂን ምርመራ ማድረግ ይችላሉ። እነዚህ የቤት ውስጥ፣ ያለ ሓኪም ማዘዣ ወይም ፈጣን ራስን መመርመሪያ በመባል ይጠራሉ። አንቲጂን መመርመርያዎች በፋርማሲ፣ በሱቆች ወይም ኦን ላይን/በይነመረብ ላይ ሊገዙ ይችላሉ። የጤና መድህን ካለዎት በየወሩ 8 የቤት ውስጥ መመርመርያዎችን ወጪ ይሸፍናል (ኢንሹራንስዎን በቀጥታ ያነጋግሩ)።

በ COVID-19 ምክንያት ሆስፒታል የመተኛት ከፍተኛ ስጋት ካለዎት ቶሎ ምርመራ ማድረግ እና ቶሎ መታከም አስፈላጊ ነው። በአፍ የሚወሰዱ የፀረ-ቫይረስ ክኒኖች ወይም ሌሎች የሕክምና አማራጮችን ምልክቶች በታዩ በ 5 ቀናት ውስጥ ከወሰዱ የበሽታዎ መባባስ እድል ይቀንሳል። ኢንሹራንስ ወይም የኢሚግሬሽን ሁኔታ ምንም ይሁን ምን ለሕክምና ምንም ወጪ የለዉም።

ህክምና ለማግኘት፦

 1. በመጀመሪያ የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎን ያነጋግሩ። አገልግሎት አቅራቢዎ ጋር አብረው ከሚሰሩ ፋርማሲዎች ወይም ፀረ-ቫይረስ መድሓኒት ከሚገኝበት በማንኛውም ቦታ ሊሞላ የሚችል የሐኪም ማዘዣ ሊሰጡዎት ይችላሉ።
 2. በአንድ ጊዜ ምርመራ እና ህክምና ለማግኘት ምርመራም ህክምናም የሚያገኙበትን ክሊኒክ ይጎብኙ። ምርመራ እና ህክምና የሚያገኙበትን ክሊኒክ ለማግኘት ዚፕ ኮድዎን ወደ ክሊኒክ አመልካች ያስገቡ ፣ ወይም ወደ 1-800-232-0233 (TTY 888-720-7489) ይደውሉና በእንግሊዝኛ፣ በስፓኒሽ እና በሌሎች ከ150 በላይ ቋንቋዎች በመጠቀም እርዳታ ያግኙ።

የ COVID-19 ህክምና (PDF)

ምርመራዎት አዎንታዊ ከሆነ

 • ምንም አይነት የሕመም ምልክቶች ባይኖርቦትም እንኳን የ COVID-19 በሽታ ሊኖርቦት ይችላል።
 • ፈጣን እቤት ውስጥ የሚደረግ ምርመራ ካደረጉ፣ ወደ ላብራቶሪ፣ ክሊኒክ ወይም የምርመራ ቦታ ሄደው ውጤቱን ማረጋገጥ አይጠበቅብዎትም።
 • ሕክምና ለማግኘት ሌላ ምርመራ ማድረግ አያስፈልግዎትም።

ምን ማድረግ አለቦት:

 • ለ 5 ቀናት ከሌሎች እራስዎን ያግልሉ። ከሌሎች የሚገለሉበትን ቀናት ከጨረሱ በኋላ ለተጨማሪ ለአምስት ቀናት ከሌሎች ግለሰቦች ጋር አብረው በሚያሳልፉበት ጊዜ ጭምብል ማድረግዎን ይቀጥሉ።
 • ለበሽታው የበለጠ ተጋላጭ ከሆኑ የቅድሚያ ሕክምና አማራጮትን ለማወቅ የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎትን ይጠይቁ ወይም ለመታከም ምርመራ የሚያደርጉ ክሊኒኮችን ይጎብኙ
 • አዎንታዊ ምርመራ ውጤት እንዳገኙ በቅርብ የቅርብ ግንኙነት ላሎት ግለሰቦች እና ለቤተሰብ አባላቶች ይንገሩ።
 • ሰለ ሠራተኞች ድጋፍ የበለጠ ለመረዳት ይመልከቱ።
 • ከሚከተሉት ሁለት አማራጮች አንዱን በመጠቀም የፈጣን የምርመራ ውጤቶትን ለዋሽንግተን ስቴት የጤና ዲፓርትመንት ሪፖርት ያድርጉ
  • በኦንላይን መስመር ላይ ውጤቶን ያሳውቁ። ወደ safercovid.org/mytest ድህረገጽ ይሂዱና፣ የሚኖሩበትን ስቴት ይምረጡ፣ ከዚያም የኦንላይን ቅጹን ተጠቅመው የምርመራዎትን ውጤት ይሙሉ።
  • በስልክ ደውለው ያሳውቁ። 1-800-525-0127 ይደውሉና # ን ይጫኑ (ለስፓኒሽ ቋንቋ ድጋፍ ቁጥር 7 ን ይጫኑ ወይም ስልኮት ሲነሳ የሚፈልጉትን ቋንቋ ይናገሩ)።
 • ከሌሎች ተነጥለው ወይም ተገልለው በሚቆዩበት ጊዜ ምግብ ወይም ሌላ እርዳታ ከፈለጉ፣ Care Connect Washington ን ይጎብኙ ወይም ወደ ፕሮግራሙ የስልክ መስመር 1-833-453-0336 ይደውሉ ወይም በስልኩ የጽሁፍ መልዕክት ይላኩ።
 • የቅርብ ግንኙነት የነበራቸውን ሰዎች ከሚከታተሉ ቡድኖች የሚመጣ የስልክ ጥሪን ወይም የጽሑፍ መልዕክት ይመልሱ። ስልክዎ ደዋዩን "WA Health" ብሎ ለይቶ ይጽፈዋል።

የCOVID-19 የምርመራ ጣቢያዎች በኪንግ ካውንቲ ውስጥ ባሉ ቦታዎች

በኪንግ ካውንቲ ውስጥ በነጻ ወይም በዝቅተኛ ወጪ የCOVID-19 ምርመራ የሚያደርጉ ጣቢዎችን ለማግኘት ከዚህ በታች ያለውን ዝርዝር ይመልከቱ።

መታወቂያዎን እና (ኢንሹራንስ ካለዎት) የኢንሹራንስ ካርድዎን እንዲያቀርቡ ይጠየቃሉ፣ ነገር ግን ለመመርመር የግድ እነዚህን ማሟላት አያስፈልግዎትም።

እነዚህ ጣቢያዎች በኪንግ ካውንቲ አይተዳደሩም ስለዚህም ለምርመራ አገልግሎታቸው ክፍያ ሊያስከፍሉ ይችላሉ። ለበለጠ መረጃ እባክዎን ድህረገጻቸውን ይመልከቱ።

በአቅራቢያዎ የሚገኝ የምርመራ ጣቢያ ለማግኘት ከዚህ በታች ካሉት ከተማ ውስጥ የሚፈልጉትን ይምረጡ።

ማሳሰቢያ፡ የኮከብ ምልክት (*) የተደረገባቸው ጣቢያዎች ኢንሹራንስ ለሌላቸው ግለሰቦች የነፃ ምርመራ ይሰጣሉ። እባክዎን ሌላ ቦታ ያሉ ጣቢያዎችን የሚጎበኙ ከሆነ ስለምርመራ ክፍያዎች የሚሔዱበት ጣቢያ በቀጥታ ይጠይቁ።

በራሪ ወረቀት: የCOVID-19 ምርመራ አማራጭ (PDF)

ሲማር (SeaMar) የማህበረሰብ ጤና ማዕከላት (በርካታ ቦታዎች)

ዩደብሊው ሜድስን (UW Medicine)* – አንዳንድ የሙከራ ጣቢያዎች እየተዘጉ ነው። መረጃ ለማግኘት ድረገጹን ይጎብኙ።


ወጪ የሌለው የ COVID-19 ምርመራ ይፈልጉ external link (በርካታ ቦታዎች)

Test to Treat (ምርመራ ለህክምና) ክሊኒክ ይፈልጉ external link (በርካታ ቦታዎች)


በፌዴራል የሲቪል መብት ህግ መሰረት: የማህበረሰብ ጤና-ሲያትል እና ኪንግ ካውንቲ በማናቸውም ፕሮግራም ወይም ስራዎች ላይ ጥበቃ በሚደረግላቸው ግለሰቦች ምድብ: ሁሉንም ያካተተና በዘር ሳይገደብ : በመልክ: በመጡበት የትውልድ ስፍራ/አገር: ሃይማኖት: የጾታ ማንነት (የጾታ አገላለጽን አካቶ):የጾታ ኦሪየንቴሽን: የአካል ጉዳተኛነትን: እድሜ: እና የጋብቻ ሁኔታ ላይ መሰረት ያደረገ ማናቸውንም ልዩነቶች አያደርግም። ቅሬታ ካልዎትና ክስ መመስረት ከፈለጉ: ወይም አድሎአዊነትን በተመለከተ ጥያቄ ካልዎት እባክዎትን የኪንግ ካውንቲ የሲቪል መብቶች ፕሮግራምን በ civil-rights.OCR@kingcounty.gov206-263-2446(እባክዎትን ለትርጉም አገልግሎት ቋንቋዎትን ይግለጹ); TTY ሪሌይ 7-1-1; ወይም በፖስታ አድራሻ (401 5th Ave, Suite 800, Seattle, WA 98104) ያግኙ።


kingcounty.gov/covid/testing/amharic ላይ ጣቢያችንን ያግኙ/ያጋሩ።

expand_less