Skip to main content
King County logo

COVID-19 የክትባት ልማት እና ደህንነት

የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር (FDA) የመጀመሪያው የCOVID-19 ክትባቶችን ለድንገተኛ ግዜ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ፈቅዷል ፡፡ በርካታ ሌሎት ክትባቶች በመሰራት ላይ ሲሆኑ በርካታዎቹ ደሞ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ፍቃደኞች መሰረት ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ውጤታማ መሆናቸውን ለማረጋገጥ በትላልቅ ክሊኒካዊ ሙከራዎች ውስጥ ናቸው፡፡ አቅርቦቶቹ ቀስ በቀስ እንደሚጨምሩ ይጠበቃል፤ የCOVID-19 ክትባቶች መከተብ ለፈለገዉ ሰዉ ሁሉ በ2021 ጸዳይ ወይም በጋ በሰፊዉ መቅረብ አለበት።

አስቸኳይ የጤና ፍላጎትን ለመቅረፍ አንድ ምርት እንዲገኝ ለማድረግ ብሔራዊ የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ሲከሰት የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር (FDA) በብሔራዊ ድንገተኛ አደጋዎች ወቅት EUAs በመባል የሚታወቁ የአስቸኳይ ጊዜ አጠቃቀም ፍቃዶችን ይጠቀማል ፡፡ EUA አንድ ምርት ሙሉ ፈቃድ ከመስጠቱ በፊት ጥቅም ላይ እንዲውል ይፈቅዳል ፡፡

አንድ EUA ለፈተናዎች ፣ ለመሣሪያዎች ወይም ለሕክምናዎች ሊያገለግል ይችላል ፡፡ ቀደም ሲል አንትራክስ ፣ ኢቦላ ፣ H1N1 እና ሌሎች የጤና እክሎችን ለመቅረፍ FDA አውጥቷል ፡፡

የCOVID-19 ክትባት ለ EUA እንዲታሰብ የFDA መመሪያዎች መሟላት አለባቸው ፣ እነሱም ደህንነት እና ውጤታማነት ደረጃዎችን እና ገለልተኛ የህክምና ባለሙያዎች ግምገማን መሟላት ይጠይቃል።

FDA ለEUA ክትባት የሚያፀድቅ ከሆነ ሁለተኛው ገለልተኛ አማካሪ ኮሚቴ የደህንነት እና ውጤታማነት መረጃን ይገመግማል። ይህ ኮሚቴ ፣ የክትባት ልምዶች አማካሪ ኮሚቴ (ACIP) ፣ ከዚያ ክትባቱ ጥቅም ላይ መዋል አለበት የሚል አስተያየት ይሰጣል ፡፡ እነሱ ብቁ መሆኑን ከመሰከሩ ACIP ለጤና እንክብካቤ አቅራቢዎች መመሪያ ያወጣል ፡፡

FDA እና CDC ክትባቱ ከተፈቀደም በኋላ የክትባቱን ደህንነት እና ውጤታማነት መከታተላቸውን ይቀጥላሉ ፡፡

የክትባት ድኅንት ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው።ሁሉም የ COVID-19 ክትባቶች ጥቅም ላይ ከመዋላቸው በፊት በአሜሪካ ውስጥ ጠንከር ያለና ባለብዙ ደረጃ የሙከራ እና የግምገማ ሂደት ውስጥ ማለፍ አለባቸው ፡፡ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተደረጉ ጥናቶችን እና ገለልተኛ የደህንነት ቁጥጥር ቦርዶችን የመረጃ ዳሰሳ ያካትታሉ ፡፡ ክትባቶቹ የሚፀድቁት ወይም ጥቅም ላይ የሚውሉት የደህንነትና የውጤታማነት ደረጃዎችን ካለፉ ብቻ ነው ፡፡ ክትባቶች ከተሰጡ በኋላም ለደህንነት ሲባል ቁጥጥር ይደረግባቸዋል ፡፡


ይህ አጭር ቪዲዮ ከዋሽንግተን ጤና ቢሮ COVID-19 ክትባቶች እንዴት እንደተሠሩ የበለጠ ያብራራል ፡፡

ብዙ ጊዜ የክትባት ምርመራና ምርት በበርካታ፣ ግዜ ጨራሽ፣ ተናጠል ደረጃዎች ለበርካታት ዓመታት ይከናወናሉ። በወረርሽኙ ምክንያት የፌደራል መንግስት ለክትባት ተመራማሪዎችና አምራቾች ማልማት፣ መሞከር እና ማምረት ባንድ ግዜ እንድቻል የተለየ የገንዘብ ድጋፍ አቅርቧል። ምንም ደረጃዎች አልታለፉም ነገር ግን ለልማት የጊዜ ሰሌዳው በፍጥነት ሊሄድ ይችላል።

ከPfizer እና Moderna ፈቃድ ያገኙት ክትባቶች የmRNA (ይህ ድህረ-ገጽ በእንግሊዘኛ ብቻ ነው ያለው) ክትባቶች ናቸው። የmRNA ክትባት ቴክኖሎጂ ለአስርት አመታት የተጠና እና የተሰራበት ነው። በእነዚህ ክትባቶች ላይ ያለ ፍላጎት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተፈላጊነታቸው እየጨመረ ነው፤ ምክኒያቱም በቀላሉ በሚገኙ ግብአቶች መሰራት የሚችሉ ናቸው። ይህም ማለት ይህ ሂደት ደረጃውን እንዲጠብቅ እና እንዲያድግ ማድረግ ያስቸላል፣ ማለትም ይህ የክትባት ማምረት ሂደት ከድሮው የማምረት ሂደት በእጅጉ እንዲፈጥን ያደርገዋል።

የ Johnson & Johnson ክትባት የቫይረስ ተላላኪ ክትባት (ድህረ-ገጹ በእንግሊዘኛ ብቻ ነው ያለው) ነው፣ ይህ ቴክኖሎጂ በመጀመሪያ የተፈጠረው በ1970ዎቹ ነው። ለአስርት አመታት፣ በአለም ዙሪያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሳይንሳዊ ጥናቶች ስለተላላኪ የቫይረስ ክትባቶች ተደርገዋል። እነርሱም ኢቦላ፣ ጉንፋን እና ኤች.አይ.ቪ. እና በሌሎች ተላላፊ የሆኑ በሽታዎች ላይ ጥቅም ላይ ውለዋል።

ክትባቱ በEUA ሲጸድቅ በፈቃደኝነት የ COVID-19 ክትባቱን የሚወስዱ ከተለመደ ክትባት ማፅደቅ ሂደት ጋር ሲነፃፀር ለአጭር ጊዜ ክትትል ይደረግባቸዋል። የ COVID-19 ክትባት ምርመራ በሺዎች የሚቆጠሩ ፈቃደኞች ያካተተ ሲሆን ግማሽ የሚሆኑት ፈቃደኞች የመጨረሻውን የክትባት መጠን ከወሰዱ በኋላ ቢያንስ ለ 2 ወራት ይከተላሉ (ከተለመደው ሂደት ውስጥ ከ 6 ወይም ከዚያ በላይ ወሮች ይልቅ)። ሆኖም በሁለት ወር ውስጥ ከክትባቶች የሚመጡ አብዛኛዎቹ የጎንዮሽ ጉዳቶች እንደሚታዩ ይጠበቃል።

ያልተለመዱ የጎንዮሽ ጉዳቶች ሊታዩ የሚችሉት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ከተከተቡ በኋላ ብቻ ነው። ለዚህ ምክንያት የ COVID-19 ክትባቶች ከተሰጡም በኋላ ደህንነታቸውን መከታተል ይቀጥላል።

አዎ፡፡ ከሚያዝያ 24,2021 ጀምሮ ዕድሜያቸው 18 እና ከዚያ በላይ የሆኑ አዋቂዎች ሲዲሲ እና ኤፍዲኤ የክትባቱን አጠቃላይ የተሟላ ደህንነት ግምገማ ካጠናቀቁ በኋላ የጆንሰን እና ጆንሰን COVID-19 ክትባትን ማግኘት ይችላሉ [በእንግሊዝኛ ብቻ]፡፡

የጆንሰን እና ጆንሰን (ጄ እና ጄ / ጃንሰን ተብሎም ይጠራል) ክትባት መጠቀሙ በሚያዝያ 13 ቀን ቆሟል ሲዲሲ (CDC) በጣም ያልተለመደ ሁኔታ አነስተኛ ቁጥር ያላቸውን ሪፖርቶችን ገምግሟል [በእንግሊዝኛ ብቻ] ብዙውን ጊዜ ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 49 ዓመት በሆኑ ሴቶች ውስጥ የሚገኙትን የደም መርጋት እና ዝቅተኛ የፕሌትሌት ቆጠራን ያካትታል፡፡ መረጃውን በጥልቀት ከመረመረ በኋላ ሲዲሲ የዚህ ሁኔታ ስጋት እጅግ በጣም ዝቅተኛ መሆኑን ወስኗል ፡፡ በአንፃሩ የጄ ኤን ጄ ክትባት ከ COVID-19 ሆስፒታል መተኛት እና ሞት ከሚያስከትለው ከፍተኛ አደጋ ይከላከላል፡፡

ዕድሜያቸው ከ50 ዓመት በታች የሆኑ ሴቶች ይህ በጣም ያልተለመደ ነገር ግን ከባድ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል ማወቅ አለባቸው፡፡ ሌሎች የ COVID-19 ክትባቶች (ፋይዘር እና ሞደርና) ከዚህ አደጋ ነፃ ናቸው፡፡

የጄ እና ጄ ክትባት ከተከተቡ በኋላ ለሦስት ሳምንታት እነዚህን ምልክቶችን ይከታተሉ

 • ከባድ ወይም የማያቋርጥ ራስ ምታት ወይም የደበዘዘ እይታ
 • የደረት ህመም
 • የትንፋሽ እጥረት
 • የእግር እብጠት
 • የማያቋርጥ የሆድ ህመም
 • ቀላል ጉዳት ወይም ከቆዳ በታች ጥቃቅን የደም ጠብታዎች

ከእነዚህ ምልክቶች አንዱ ወይም ከዚያ በላይ ከታዩ ወዲያውኑ የሕክምና እንክብካቤ ይፈልጉ፡፡

ማሳሰቢያ-ክትባቱን ከአንድ ወር በፊት ከወሰዱ አደጋዎ በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡ ማንኛውንም COVID-19 ክትባት ከወሰዱ በኋላ በመጀመሪያው ሳምንት ውስጥ ትኩሳትን ፣ ራስ ምታትን ፣ ድካምን እና የመገጣጠሚያ / የጡንቻ ህመምን ጨምሮ መለስተኛ እና መካከለኛ ምልክቶች መኖራቸው የተለመደ ነው፡፡

ማንኛውም ጥያቄ ወይም ጭንቀት ካለዎት ወደ ሐኪምዎ ፣ ነርስዎ ወይም ክሊኒክዎን ይደውሉ ፡፡ ሲዲሲ እና ኤፍዲኤ የሁሉንም የ COVID-19 ክትባቶች ደህንነት መከታተላቸውን የሚቀጥሉ ሲሆን ተጨማሪ መረጃዎች ሊገኙ ሲችሉ የህብረተሰብ ጤና መረጃዎችን ያቀርባል፡፡

ይህ በዋሺንግተን የጤና ዲፓርትመንት የተዘጋጀ ቪዲዮ፣ (ይህ ድህረ-ገጽ በእንግሊዘኛ ብቻ ነው ያለው) አዲስ መረጃ ሲያዩ የተጻፈበትን እሳቤ፣ ጸሃፊውን እና ምንጮችን እንዲያዩ እናም የሚያውቁትን ሰው ጠይቀው እንዲያረጋግጡ ምክር ይሰጣል። የህዝብ ጤና “Is it True?” (እውነት ነው?) የሚል ግብአትን በማዘጋጀት ስለ COVID-19 ክትባት በብዛት የሚነገሩ የተዛቡ መረጃዎች ላይ ውይይት ለማድረግ እየሰራ ነው።

የ COVID-19 ክትባት እንዴት ነው የሚሰራው

COVID-19 ክትባቶች ሰውነታችን በሽታውን ሳንይዝ COVID-19ን ለሚያስከትለው ቫይረስ የበሽታ መከላከያ እንዲዳብር ይረዱታል ፡፡ ክትባቱን ሲወስዱ በሽታ የመከላከል ስርዓትዎ በደምዎ ውስጥ የሚቆዩ እና በቫይረሱ ከተያዙ እርስዎን የሚከላከሉ ፀረ እንግዳ አካላትንና ሌሎች በሽታ ተዋጊ ሴሎችን ይሠራል ፡፡


በዚህ የ 60 ሰከንድ ቪዲዮ ውስጥ COVID-19 ክትባቶች በሰውነት ውስጥ እንዴት እንደሚሠሩ የበለጠ ይወቁ ፡፡

የ COVID-19 ክትባት በ COVID-19 እንዳይያዙና በደንብ እንዳይታመሙ ይረዳዎታል።

 • የሰዉነትዎን በሽታ የመከላከል ስርዓትዎን በ COVID-19 ሳይያዙ ቫይረሱን እንድዋጉ በማስተማር እርስዎን ለመከላከል ይረዳል።
 • በክሊኒክ ሙከራዎች በኡኑ ወቅት የቀረቡ ክትባቶች ሰዎችን ከ COVID-19 በመከላከል በጣም ዉጤታማ ሆኖ ተገኝቷል።

የ COVID-19 ክትባት ወረርሽኙን ለማቆም ለመርዳት ጠቃሚ መሣሪያ ይሆናል።

 • ክትባቱን ማግኘት ራሶን፣ ጓደኞቾትን እና ቤተሰብን እና በማህበረሰብ ውስጥ ያሉ ሰዎች በCOVID-19 እንዳያዙ ይረዳል፡፡ በዚህ ወቅት ክትባቱን ማግኘት እና የማህበረሰብ ጤና ምክሮችን መከተል ከ COVID-19 ራስን ለመከላከል ምርጡን አማራጭ ይሰጣሉ፡፡
 • ለቫይራሱ የመጋለጥ ወይንም ለሌሎች የማስተላልፍ ዕድሎን ለመቀነስ ማስኮችን ይልበሱ ማህበራዊ ርቀትንም ይጠብቁ፤ ኝ እነዚህ እርምጃዎች ብቻ በቂ አይደሉም። ክትባቶች ከሰዉነትዎ በሽታ የመከላከል ስርዓት ጋር ይሰራሉ ከተጋለጡ ቫይረሱን ለመዋጋት ዝግጁ እንድሆኑ።
 • ከግዜ በኋላ ብዙ ሰዎች እየተከተቡ ሲሄዱ በአሁን ሰዓት አስፈላጊ የሆኑ የCOVID-19 መከላከያ እርምጃዎችን ላንፈልጋቸዉ እንችላለን።

የለም ፣ COVID-19 ክትባቶች የ COVID-19 በሽታ ሊያስከትሉ አይችሉም ፡፡ የ COVID-19 ክትባቶች ፀረ እንግዳ አካላትንና ሌሎች በሽታ ተዋጊ ሴሎችን በመስራት ሰውነታችንን እንድከላከልን ያስተምራሉ ፡፡ ክትባቶቹ በCOVID-19 ቫይረስ ሽፋን ላይ ያሉትን ፕሮቲኖች የሚመስሉ ፕሮቲኖችን የሰውነታችን ህዋሶች እንዲያመርቱ ያስተምራሉ፡፡ ይህንን ትእዛዝ ለማስተላለፍ፣ ክትባቶቹ ተላላኪ RNA (mRNA) ወይም ሌላ አይነት፣ ጉዳት የማያደርስ እና የተሻሻለ ቫይረስን ይጠቀማሉ፡፡ ሰውነታችን ያንን ፕሮቲንን መለየት በመማር የ COVID-19 ሰውነታችን ውስጥ ሲገባ የበሽታን የመከላከል ምላሽ እንዲሰጥ ያስችሉታል፡፡

ክትባቱን ከወሰዱ በኋላ በአንድ ወይም በሁለት ቀን ውስጥ ራስ ምታት ፣ የክንድ ቁስለት ፣ ድካም ወይም ትኩሳት ያሉ የጎንዮሽ ጉዳቶችን ማግኘት ይቻላል ፡፡ ነገር ግን እነዚህ የጎንዮሽ ጉዳቶች ለአጭር ጊዜ የሚቆዩ እና ክትባቱ በሰውነት ውስጥ የበሽታ መከላከያ እየገነባ መሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶች ናቸው ፡፡ አንዳንድ እነዚህ የጉንዮሽ ጉዳቶች ከCOVID-19 ምልክቶች ጋር ሊመሳሰሉ ይችላሉ፤ ሆኖም ግን በበሽታ መጠቃት ጋር አንድ አይደለም። ክትባቱ ቫይረስ ወይም የትኛዉንም የቫይረስ ክፍል አልያዘም COVID-19ንም አያስከትልም።

ከPfizer እና Moderna ፈቃድ ያገኙት ክትባቶች የmRNA (ይህ ድህረ-ገጽ በእንግሊዘኛ ብቻ ነው ያለው) ክትባቶች ናቸው፡፡ የmRNA ክትባት ቴክኖሎጂ ለአስርት አመታት የተጠና እና የተሰራበት ነው፡፡

በmRNA ክትባት ውስጥ ቫይረስ የለም፡፡ ስለዚህ በክትባቱ ምክኒያት የ COVID-19 በሽታ አይዞትም፡፡ ይልቁንም የmRNA ክትባቶች ለህዋሶቻችን ትእዛዝ በመስጠት ጉዳት የሌለው ፕሮቲን እንዲመረት ያደርጋሉ - ልክ የ COVID-19 ቫይረስ ላይ ያለውን ወሳኝ ፕሮቲን የሚመስል ማለት ነው፡፡ ህዋሶቾት ያንን ፕሮቲን ሲያመርቱ፣ ሰውነቶ ጠንካራ በሽታን የመከላከል አቅም ይፈጥራል እናም ከ COVID-19 የሚከላከሉ አንቲ-ቦዲዎችን እንዲመረቱ ይደረጋሉ፡፡ ሰውነቶም ለቫይረሱ ገና ሳይጋለጡ እርሶን እንዴት ከበሽታ መከላከል እንደሚችል ይማራል፡፡

የmRNA ሰውነታችን ራሱን ከ COVID-19 መከላከል እንዳለበት ካስተማረው በሁዋላ፣ ሰውነታችን ውስጥ ያሉ ኢንዛይሞች እንዲሰባበር እና እንዲወገድ ይደረጋል፡፡ የmRNA ወደ ህዋሰቻችን ውስጠኛ ክፍል፣ ወደ DNA ወይም የዘረ-መል ክፍል ውስጥ አይገባም፡፡

እነዚህ የ mRNA ክትባቶች ለአገልግሎት ፈቃድ ያገኙት የመጀመሪያዎቹ ቢሆኑም፣ የmRNA ቴክኖሎጂ ከ30 አመታት በላይ ሲጠና ቆይቷል፡፡ የmRNA እንዴት እንደሚሰሩ (ይህ ድህረ-ገጽ በእንግሊዘኛ ብቻ ነው ያለው) ተጨማሪ መረጃ በ CDC (የበሽታ መከላከል ማእከል) ድህረ-ገጽ ላይ ይገኛል፡፡

አዎ፣ የ Moderna ወይም Pfizer ሁለተኛ ክትባቶች ማግኘታችሁን እርግጠኛ ይሁኑ። ሁለተኛውን ክትባት ካላገኙ፣ ሙሉ ለሙሉ እንደተከተቡ አይቆጠረም።

አንዳንድ ሰዎች ሊያጋጥሙ የሚችሉ የጎንዮሽ ጉዳቶችን በመፍራት ሁለተኛውን ክትባት መዝለል እያሰብ እንደሆነ ሰምተናል። ሆኖም፣ ሙሉ ከበሽታ የመከላከል አቅምን ለመስጠት ሁለተኛው ክትባት አስፈላጊ ነው- የመጀመሪያው ክትባት በሽታ የመከላከል አቅምዎን መገንባት ይጀምራል፣ ሁለተኛው ክትባት ደግሞ ያጠናክረዋል።

ሁሉም ሰው ከሁለተኛው ክትባት በኋላ የጎንዮሽ ጉዳት አያጋጥመውም፣ እና አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ከሌሎች ሰዎች አንጻር ቀለል ያለ የጎንዮሽ ጉዳት ብቻ ያጋጥማቸዋል። የጎንዮሽ ጉዳቶች ካጋጠመዎትም፣ ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ይጀምራሉ። እነዚህ በሙሉ ክትባቱ እየሰራ መሆኑ እና ሰውነትዎ በሽታ የመከላከል አቅምዎን እየገነባ መሆኑን ማሳያ ናቸው። ህዋሶችዎ ያንን ፕሮቲን ሲሰሩ፣ ሰውነትዎ ጠንካራ የሆነ  COVID-19 በሽታን የመከላከል አቅም ይገነባል። ሰውነትዎ ለእወነተኛው የኮሮና ቫይረስ ሳይጋለጥ እርስዎ በ COVID-19 እንዳይያዙ መከላከልን ይማራል።  

እንደዚህ አይነት ክትባት በ COVID-19 ሊያስይዝዎት አይችልም ወይም ጉዳት በማያደርሱ የተለመደ ጉንፋን ቫይረስ እንዳይይዙ ትእዛዝ ያስተላልፋሉ። ክትባቱ ወደህዋሶችዎ፣ DNA ወይም ዘረ-መል  ውስጥ አይገባም ወይም አይለውጣቸውም።

ሳይንቲስቶች የተላላኪ ቫይረስን መፍጠር የጀመሩት በ1970ዎቹ ነው። ለአስርት አመታት፣ በአለም ዙሪያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሳይንሳዊ ጥናቶች ስለተላላኪ የቫይረስ ክትባቶች ተደርገዋል። እነርሱም ኢቦላ፣ ጉንፋን እና ኤች.አይ.ቪ. እና በሌሎች ተላላፊ የሆኑ በሽታዎች ላይ ጥቅም ላይ ውለዋል።

የ Johnson & Johnson COVID-19 ክትባት ጉዳት እንዳያደርስ እና ህመም እንዳያስከትል ሆኖ የተሻሻለ የተለመደ ጉንፋን ቫይረስን (የኮሮና ቫይረስ አይደለም) ይጠቀማል። ይህ ጉዳት የማያደርስ ቫይረስ ለህዋሶቻችን ትእዛዝ በማስተላለፍ ህዋሶቻችን በኮሮና ቫይረስ ሽፋን ላይ የሚገኘውን አይነት ፕሮቲን እንዲያመርቱ ያደርጋቸዋል። ህዋሶችዎ ያንን ፕሮቲን ሲሰሩ፣ ሰውነትዎ ጠንካራ የሆነ  COVID-19 በሽታን የመከላከል አቅም ይገነባል። ሰውነትዎ ለእወነተኛው የኮሮና ቫይረስ ሳይጋለጥ እርስዎ በ COVID-19 እንዳይያዙ መከላከልን ይማራል።  

እንደዚህ አይነት ክትባት በ COVID-19 ሊያስይዝዎት አይችልም ወይም ጉዳት በማያደርሱ የተለመደ ጉንፋን ቫይረስ እንዳይይዙ ትእዛዝ ያስተላልፋሉ። ክትባቱ ወደህዋሶችዎ፣ DNA ወይም ዘረ-መል ውስጥ አይገባም ወይም አይለውጣቸውም።

ሳይንቲስቶች የተላላኪ ቫይረስን መፍጠር የጀመሩት በ1970ዎቹ ነው። ለአስርት አመታት፣ በአለም ዙሪያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሳይንሳዊ ጥናቶች ስለተላላኪ የቫይረስ ክትባቶች ተደርገዋል። እነርሱም ኢቦላ፣ ጉንፋን እና ኤች.አይ.ቪ. እና በሌሎች ተላላፊ የሆኑ በሽታዎች ላይ ጥቅም ላይ ውለዋል።

ዕድሜያቸው ከ 50 ዓመት በታች የሆኑ ሴቶች የደም መርጋት እና ዝቅተኛ የፕሌትሌት ቆጠራን የሚያካትት በጣም ያልተለመደ ነገር ግን ከባድ ሁኔታ አደጋን ሊያስከትል እንደሚችል ማወቅ አለባቸው። ሌሎች የ COVID-19 ክትባቶች (ፋይዘር እና ሞደርና) ይህንን አደጋ የማያገኙ ናቸው። እባክዎን ጥያቄውን ይመልከቱ “የጆንሰን እና ጆንሰን ክትባት ጥቅም ላይ ይውላል? ለበለጠ መረጃ ከላይ ይመልከቱ።

በ Pfizer እና Moderna ክትባቶች ውስጥ ያለው ዋናው ንጥረ-ነገር mRNA ሲሆን፣ ህዋሶቾት ከ ኮሮና ቫይረስ እንዴት ፕሮቲን መስራት እንዴት እንደሚቸሉ በማሳወቅ ከ COVID-19 በሽታ እንዴት እርሶን እንደሚጠብቅ ያስተምሩታል፡፡ በተጨማሪም ክትባቶቹ በውስጣቸው ቅባቶች፣ ጨዎች እና ስኳር ይይዛል፡፡

በ Johnson & Johnson ክትባት ውስጥ ያለው ዋናው ንጥረ-ነገር አዴኖ ቫይረስ 26 ሲሆን፣ ይህም በኮሮና ቫይረስ መሸፈኛ ላይ ያለውን የሾለ ፕሮቲን ለህዋሶቻችን የሚያደርስ ጉዳት የማሳስከትል ቫይረስ ነው፡፡ ከዛም ህዋሶቻችን COVID-19 ን በማወቅ ከበሽታው ለመከላከል ይረዱናል፡፡ የ J&J ክትባት በተጨማሪነት ሲትሪክ አሲድን እና ኤታኖልን ይይዛል፡፡

ክትባቶች በውስጣቸው እነዚህን አይዙም፡ የአሳማ ስጋ ውጤቶች፣ እንቁላል፣ ላቴክስ፣ የደም ውጤቶች፣ የ COVID-19 ቫይረስ ህዋሶች፣ ሜርኩሪ፣ ጥቃቅን የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች፡፡ ክትባቶች በውስጣቸው የጽንስ ህዋስ አይዙም፡፡

በ Pfizer ክትባት ውስጥ ያሉ ንጥረ-ነገሮች ሙሉ ዝርዝር፣ ከምግብና መድሀኒት አስተዳደር የተገኘ (ይህ ድህረ-ገጽ በእንግሊዘኛ ብቻ ነው ያለው):

ዋና ንጥረ-ነገሮች

 • nucleoside-modified messenger RNA (modRNA) የቫየረሱን spike glycoprotein (S) of SARS-CoV-2 መልእክት የሚያስተላልፉ

ቅባቶች

 • (4-hydroxybutyl)azanediyl)bis(hexane-6,1-diyl)bis(2- hexyldecanoate)
 • 2-[(polyethylene glycol)-2000]-N,N-ditetradecylacetamide
 • 1,2-distearoylsnglycero-3-phosphocholine
 • ኮሌስትሮል (cholesterol)

ተጨማሪ ንጥረ-ነገሮች (ጨዎች፣ ስኳሮች፣ መበረዣዎች)

 • ፖታሺየም ክሎራይድ (potassium chloride)
 • ሞኖቤዚክ ፖታሺየም ፎስፌት (monobasic potassium phosphate)
 • ሶዲየም ክሎራይድ (sodium chloride)
 • ዳይቤዚክ ሶዲየም ፎስፌት ዲሃይድሬት (dibasic sodium phosphate dehydrate)
 • ሲክሮሰስ (sucrose)

በ Moderna ክትባት ውስጥ ያሉ ንጥረ-ነገሮች ሙሉ ዝርዝር፣ ከምግብና መድሀኒት አስተዳደር የተገኘ (ይህ ድህረ-ገጽ በእንግሊዘኛ ብቻ ነው ያለው):

ዋና ንጥረ-ነገሮች

 • nucleoside-modified messenger RNA (modRNA) የቫየረሱን spike glycoprotein (S) of SARS-CoV-2 መልእክት የሚያስተላልፉ

ቅባቶች

 • polyethylene glycol (PEG) 2000 dimyristoyl glycerol (DMG)
 • SM-102
 • 1,2-distearoyl-snglycero-3-phosphocholine
 • ኮሌስትሮል (cholesterol)

ተጨማሪ ንጥረ-ነገሮች (ጨዎች፣ ስኳሮች፣ መበረዣዎች)

 • ትሮሜታሚን (tromethamine)
 • ትሮሜታሚን ሃይድሮክሎራይድ (tromethamine hydrochloride)
 • አሴቲክ አሰድ (acetic acid)
 • ሶዲየም አሲቴት (sodium acetate)
 • ሲክሮሰስ (sucrose)

በ Johnson & Johnson (Janssen) ክትባት ውስጥ ያሉ ንጥረ-ነገሮች ሙሉ ዝርዝር፣ ከምግብና መድሀኒት አስተዳደር የተገኘ፡ (ይህ ድህረ-ገጽ በእንግሊዘኛ ብቻ ነው ያለው)

ዋና ንጥረ-ነገሮች

 • ተቀያሪ፣ የመራባት አቅም የሌለው አዴኖ ቫይረስ አይነት 26 የ SARS-CoV-2 ሹል ፕሮቲንን የሚያሳይ

ዋና ያልሆኑ ንጥረ-ነገሮች

 • ሲትሪክ አሲድ ሞኖሃይድሬት
 • ትራይሶዲየም ሲትሬት ዳይሃይድሬት
 • ኤታኖል
 • 2-hydroxypropyl-β-cyclodextrin (HBCD)
 • polysorbate-80
 • ሶዲየም ክሎራይድ

የ Moderna እና Pfizer ክትባቶች ከፍተኛ የሆነ የ COVID-19 በሽታን የመከላከል አቅምን ማሳየታቸውን ቀጥለዋል እናም የ COVID-19 ህመም እንዳይስፋፋ ለማድረግ አሁንም ቢሆን በጣም አስፈላጊ ናቸው። የበሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ማእከል (CDC)፣ የ Moderna እና Pfizer ክትባቶች የ B.1.1.7 ልውጥ፣ የዩናይትድ ኪንግደም ልውጥ ተብሎ የሚጠራው፣ እና በዋሺንግተን ግዛት ውስጥ የተገኘውን የልውጥ አይነትም ላይ ውጤታማ ይመስላሉ። በክትባቱ የሚመረቱ ጸረ-ህዋሶች፣ የ B.1.351 (ደቡብ አፍሪካ) እና የ P.1 (ብራዚል) ልውጦችን እንደሚለዩዋቸው ጥናቶች ያመላክታሉ። የጤና ባለሙያዎች ክትባቶቹ እንዚህ ልውጦች ላይ ምን ይህል ውጤታማ እንደሆኑ መከታተላቸውን እና ማጥናታቸውን ይቀጥላሉ።

የ Johnson & Johnson ክትባት ክሊኒካዊ ሙከራ አዳዲስ እና ይበልጥ ተዛማጅ የሆኑ የቫይረስ አይነቶች እየተዘዋወሩ ባሉበት በአሁኑ ሰአት ነው የተጠናቀቀው፣ እናም በክፍተኛ ሁኔታ ውጤታማ መሆኑን ታውቋል፡፡ የ Johnson & Johnson ክትባት በ COVID-19 ምክኒያት ከሚመጣ የከፋ ህመም፣ በሆስፒታል አልጋ ከመያዝ፣ ሞት፣ የ B.1..351 (ደቡብ አፍሪካ) እና P.1 (ብራዚል) ልውጦች ከፍተኛ የሆነ የመከላከል አቅም አለው፡፡ የጤና ባለሙያዎች ክትባቱ ልውጦች ላይ ያለውን ውጤታማነት ላይ ክትትል እና ምርምር ማድረግ ይቀጥላሉ፡፡

ክትባቱን በመከተብ እና ሌሎች የ COVID-19 መከላከያ መንገዶችን፣ ማስክ ማድረግ፣ ከቤት ውጪ በምንሆንበት ሰአት አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ እና እጆቻችንን በመታጠብ፣ ቫይረሱ እንዳይንሰራፋ እንከላከላለን እና ተጨማሪ ልውጦች የመፈጠር እድላቸውን እንቀንሳለን።

የክትባት መኖር

ዕድሜያቸው 12 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነ ሁሉ አሁን ለኮቪድ-19 (COVID-19 )ክትባት ብቁ ናቸው።

እንዴት ክትባት መውሰድ እንደሚችሉ የበለጠ በዚህ ይወቁ

ስለ ዋሽንግተን ግዛት የCOVID-19 ክትባት ስርጭት እዚህ የበለጠ ይወቁ (ይህ ድህረ-ገጽ በእንግሊዘኛ ብቻ ነው ያለው)።

የ COVID-19 ክትባቶች በሆስፒታሎች፣ በፋርማሲዎች፣ በከፍተኛ መጠን ቦታዎች፣ በማህበረሰብ ጤና ማእከላት እና በሌሎች አቅራቢዎች በኩል እየተሰራጩ ይገኛሉ። በኪንግ ካውንቲ ውስጥ ክትባቱን የት መከተብ እንደሚችሉ እዚህ ጋር ይጎብኙ። (ይህ ድህረ-ገጽ በእንግሊዘኛ ብቻ ነው ያለው)

አንዳንድ የክትባት አቅራቢዎች ያሉዋቸውን ይክትባት አይነቶች ዝርዝር በመመዝገቢያ ድህረ-ግጾቻቸው ላይ ያስቀምጣሉ ወይም ይህንን መረጃ በስልክ ይሰጣሉ። ሁሉም ለአገልግሎት ፈቅድ የተሰጣቸው ክትባቶች በ COVID-19 በሆስፒታል አልጋ መያዝን እና ሞትን ይከላከላሉ። ሁሉም ክትባቶች ደህንነታቸ የተጠበቀ እና በጣም ውጤታ ናቸው። ሆኖም ግን፣ አንዳንድ ወሳኝ ልዩነቶች አሉዋቸው፣

 • የእድሜ ተገቢነት፡ የ Pfizer ክትባት በአሁኑ ጊዜ 16 አመት እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ሰዎች ይሰጣል። የ Moderna እና Johnson & Johnson ክትባቶች 18 አመት እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ሰዎች መሰጠት ይችላሉ።
 • የክትባት መጠኖች፡ የ Johnson & Johnson ክትባት አንድ ጊዜ መከተብን ብቻ ነው የሚጠይቀው። ለ Pfizer ክትባት (ቢያንስ በ3 ሳምንት ልዩነት) እና ለ Moderna ክትባት (ቢያንስ በ4 ሳምንት ልዩነት) ሁለት ክትባቶች ያስፈልጋሉ።

የተለያዩ አቅራቢ ቦታዎች እንዳላቸው ክትባት መሰረት የተለያዩ ክትባቶች ሊኖሯቸው ይችላል። የክትባት አቅርቦት ሊለዋወ ይችላል፣ ስለዚህ አንድ አቅራቢ የሚያገኘው የክትባት አይነት ሊቀየር ይችላል።

ዕድሜያቸው 12 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ወጣቶች የኮቪድ-19(COVID-19)ክትባትን አሁን መውሰድ ይችላሉ፡፡ የፋይዘር(Pfizer)ክትባት ዕድሜያቸው 12 እና ከዚያ በላይ ለሆኑት የተፈቀደ ሲሆን የሞዴና ጆንሰን እና ጆንሰን(Moderna and Johnson & Johnson ክትባቶች ዕድሜያቸው 18 እና ከዚያ በላይ ለሆኑት እንዲፈቀድ ተደርጓል፡፡

ለታዳጊ ሕፃናት የክትባት ክሊኒካዊ ሙከራዎች በአሁኑ ወቅት በመጀመርያው ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን ክትባቶቹም ለታዳጊ ሕፃናት ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ውጤታማ መሆናቸውን የጥናት መረጃዎች እስከሚያሳዩ ድረስ ለኮቪድ-19(COVID-19)ክትባት አይኖርም፡፡

ለወጣቶች ክትባት በተመለከተ የበለጠ በዚህ ገጽ ይመልከቱ kingcounty.gov/youthvaccine/amharic

መከተብ የግል ምርጫ ነው። አሁን ላይ ፈቃድ ያገኙት ሁሉም የ COVID-19 ክትባቶችእርጉዝ ለሆኑ ወይም ለሚያጠቡ ሰዎች መሰጠት ይችላሉ። ስለመከተብ ጥያቄ ካልዎት፣ ከጤና እርዳታ አቅራቢዎ ጋር ማውራት ሊረዳዎት ይችላል፣ ነገር ግን አስገዳጅ አይደለም።

ከሲ.ዲ.ሲ. ተጨማሪ መረጃዎችን ያግኙ (ድህረ-ገጹ በእንግሊዘኛ ብቻ ነው ያለው)።

ምን እንደሚጠበቅ

የ COVID-19 ክትባት ለማግነት ክፍያ የለውም፣ ይህም በስደተኝነት ወይም የጤና ኢንሹራንስ ላይ አይመሰረትም። ክትባቱ በሜዲኬይር (Medicare)፣ ሜዲኬይድ (Medicaid) እና በአብዛኛዎቹ የግል ኢንሹራንሶች ይሸፈናሉ፣ እና ኢንሹራንስ ለሌላቸው ሰዎች የክትባት ወጪው ይሸፈናል።

የ COVID-19 ክትባት አቅራቢዎች የሚከተሉትን ማድረግ አይችሉም፡

 • ለክትባቱ ማስከፈል
 • ለተደራቢ ኢንሹራንስ፣ ተደራቢ ክፍያ ወይም የአስተዳደር ወጪዎች እርስዎ እንዲከፍሉ መጠየቅ
 • የጤና ኢንሹራንስ ሽፋን ለሌለው፣ አንስተኛ የሆነ ኢንሹራንስ ብቻ ላለው ወይም ግንኙነት ለሌለው ለማንኛውም ሰው ክትባት መከልከል
 • የተሰጠው አገልግሎት የ COVID-19 ክትባት ብቻ ሆኖ እያለ ለቢሮ ጉብኝት ወይም ለሌላ ምክኒያት ክፍያ መጠየቅ
 • የ COVID-19 ክትባትን ለመሰጠት ሌሎች አገልግሎቶችንም እንዲያገኙ መጠየቅ፣ ሆኖም ግን፣ ተጨማሪ የጤና እርዳታ አገልግሎቶች በተመሳሳይ ሰአት መቅረብ ይችላሉ እናም ተገቢው ክፍያ ሊፈጸም ይችላል

የ COVID-19 ክትባት አቅራቢዎች የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ፡

 • ክትባቱን ካገኘው ሰው ፕላን ወይም ፕሮግራም (ለምሳሌ፣ የግል የጤና ኢንሹራንስ፣ ሜዲኬይር (Medicare)፣ ሜዲኬይድ (Medicaid)) ክትባት የሰጡበትን ተገቢ ክፍያ መጠየቅ ይችላሉ። ሆኖም ግን፣ ክትባቱን ያገኘው ሰው ያንን ክፍያ እንዲፈጽም መጠየቅ አይችሉም
 • ኢንሹራንስ ለሌላቸው ተከታቢዎች ከጤና ግበቶች እና አገልግሎቶች አስተዳደር የ COVID-19 ኢንሹራንስ የሌላቸው ሰዎች ፕሮግራም (Health Resources and Services Administration's COVID-19 Uninsured Program) ክፍያን መጠየቅ ይችላሉ።

የህዝበ ጤና - ሲያትል እና ኪንግ ካውንቲ እና ሌሎች የነጻ የክትባት ክሊኒኮችን እያቀረቡ ነው። ለእነዚህ ክሊኒኮች ፍትሃዊ አቅርቦት ቅድሚያ የሚሰጡት ጉዳይ ነው። ተጨማሪ መረጃ በኪንግ ካውንቲ ክትባትን ማግኘት ገጽ ላይ ይገኛል።

ይህ የትኛው ክትባትን እንደሚያገኙ ላይ ይወሰናል፡፡ የ Johnson & Johnson የ COVID-19 ክትባት ሙሉ የሆነ የበሽታ መከላከልን ለማግኘት አንድ ክትባት ብቻ ይበቃዋል፡፡ የ Pfizer እና Moderna ክትባቶች ሁለት ክትባቶችን መውሰድ ይጠይቃሉ ፣ አንደኛው መከላከያ ግንባታን ለመጀመር እና ሁለተኛው መከላከያውን ከፍ ለማድረግ እና ለማጠናቀቅ ነው፡፡

እንደ ክትባቱ ዓይነት ሁለተኛዉ ክትባት አንደኛዉ ከተሰጠ 21 ወይም 28 ቀናት በኋላ መሰጠት አለበት። ሁለቱንም ግዜ ተመሳሳይ ክትባት ማግኘት አለብዎት። የመጀመሪያዉ ሲከተቡ የክትባት አቅራቢዎ ሁለተኛዉን ክትባት ማግኘት ካስፈለግዎት እና የት መቼ እንሚያገኙ መረጃ ይሰጥዎታል።

ሁለተኛውን ክትባት ማግኘት የሚመከረው፣ ለ Pfizer ክትባት ከመጀመሪያው ክትባት ከ 21 ቀናት በኋላ ሲሆን ለ Moderna ክትባት ደግሞ ከ 28 ቀናት በኋላ ነው፡፡ በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ክትባቶችን ማግኘት በጣም ውጤታማው መንገድ ሆኖ እንዳለ፣ በሁለቱ ክትባቶች መካከል ያለው ጊዜ ልዩነት ቢሰፋም ክትባቱ ውጤታማ መሆኑን ይቀጥላል፡፡ የሚመከረው ቀን ቢያልፍም፣ ሁለተኛውን ክትባት ማግኘት ይመከራል፡፡

አንዳንድ ሰዎች ክትባቱን ከተከተቡ በኋላ እንደ ራስ ምታት ፣ እንደ ክንድ ቁስለት፣ ድካም ፣ ወይም ትኩሳት ለጥቂት ቀናት ምልክቶች ሊኖራቸው ይችላል ፡፡ እነዚህ ምልክቶች ከሁለተኛው የክትባት መጠን በኋላ በጣም የተለመዱ ናቸው ፡፡ እነዚህ ሁሉም የሰውነት በሽታ የመከላከል ስርዓት መከላከያ እየገነባ መሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶች ናቸው ፡፡ ይህ የተለመደ እና ሌሎች አብዛኛዉን ግዜ ጥቅም ላይ የሚዉሉ ክትባቶችም በኋላ ሊታይ ይችላል።

አናፊላክሲስ - ከባድ የሆነ የአላርጂክ የሰውነት ምላሽ - ከ COVID-19 ክትባት በኋላ የማጋጠም እድሉ እጅግ አናሳ ነው፡፡ አሁን ባለው መረጃ መሰረት ከ COVID-19 ክትባት በኋላ አናፊላክሲስ ያጋጠው ሁሉም ሰው አገግሟል፣ እናም ምንም ሞት አላገጠመም፡፡ በጸና የ COVID-19 ህመም የመታመም ወይም የመሞት አደጋ ከክትባት በኋላ በአናፊላክሲስ ወይም በሌላ በባሰ የሰውነት ምላሽ ከማጋጠም እድል አንጻር ሲታይ እጅግ ይበልጣል።

ከክባቶቹ ጋር ስለሚኖሩ አናፊላክሲስ እና ሌሎች የሰውነት የአላርጂክ ምላሾች ላይ ሲዲሲ ተጨማሪ መረጃዎችን የያዙ ሪፖርቶችን አውጠቷል፡

የበሽታን የመከላከል እና መቆጣጠር ማእከል (CDC) በቅርቡ ተመሳሳይ የሆነ ሪፖርት ለ Johnson & Johnson ክትባት ያወጣል፡፡ በክሊኒካዊ ሙከራዎች ጊዜ፣ የ Johnson & Johnson ክትባትን ከማግኘት በኋላ የሚመጡ አናፊላክቲክ የሰውነት ምላሾች እጅግ አናሳ ናቸው፡፡

አናፊላክሲስ ያጋጠማቸው አብዛኛዎቹ ሰዎች ምልክቱ ያጋጠማቸው ክትባቱን ባገኙ በ 15 ደቂቃዎች ውስጥ ነው፡፡ እነዚህ ሁሉም ታካሚዎች ምልክቶቹ ሲታዩባቸው ወዲያውኑ በኢፒነፍሪን ታክመዋል፡፡

ሁሉም የክታብት ቦታዎች አናፊላክሲስ ሲያጋጥም ማወቅ እና ማከም የሚችሉ የህክምና ባለሙያዎች አሏቸው፡፡ የ COVID-19 ክትባት የሚሰጠውን ሰው በሙሉ ከክትባት በኋላ ለ 15 ደቂቃዎች ክትትል በማድረግ እርዳታ ማድረግ ካስፈለገ ያደርጋሉ፡፡

የሚከተሉትን ሁኔታዎች የሚያሟሉ ከሆነ፣ ክትባቱን ካገኙ በኋላ ባሉት ጥቂት ቀናት ራስዎን ሳያገልሉ ወደ ስራ መመለስ ይችላሉ፡

 • በ COVID-19 ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ካልነበርዎት እና
 • ጤንነት የሚሰማዎት ከሆነ እና ስራን የመሳሰሉ የተለመዱ የእለት-ተእለት ተግባራትን መከወን የሚችሉ ከሆነ እና
 • ትኩሳት ከሌለዎት እና
 • ያለዎት የህመም ምልክቶች ከ COVID-19 ክትባት ጋር ብቻ የተወሰኑ ከሆነ (እዚህ ጋር ተጠቅሰዋል) (ይህ ድህረ-ገጽ በእንግሊዘኛ ብቻ ነው ያለው) ህመም፣ እብጠት፣ ድካም፣ ብርድ ብርድ ማለት፣ ትኩሳትን ጨምሮ እና
 • እንደ ሳል፣ ትንፋሽ ማጠር፣ የጉሮሮ መድረቅ ወይም የሽታ እና ጣእም መቀየርን የመሳሰሉ ሌሎች የ COVID-19 ምልክቶች ከሌልዎት

ተጨማሪ ግብአቶች፡

ሲዲሲ፡ ከክትባት በኋላ የሚኖሩ እሳቤዎች ለጤና ባለሙያዎች (ይህ ድህረ-ገጽ በእንግሊዘኛ ብቻ ነው ያለው)
ሲዲሲ፡ ከክትባት በኋላ የሚኖሩ እሳቤዎች ለረጅም ጊዜ እንክብካቤ መስጫ ነዋሪዎች (ይህ ድህረ-ገጽ በእንግሊዘኛ ብቻ ነው ያለው)

ነጻ፣ በስማርት ስልክ ላይ የተመሠረተ የCOVID-19 ክትባት ከወሰዱ በኋላ የግል ጤና መከታታዎችን ለማቅረብ የቴክስት መልዕክትና የበየነ መረብ ዳሳሳዎችን የሚጠቀም CDC V-safe የተሰኘ መሣሪያ ፈጥሯል። V-safe ሁለተኛ ክትባትዎን እንድያገኙም ያስታዉስዎታል። በ V-safe እንድሳታፉ እናበረታታዎታለን። ከዚህ www.cdc.gov/vsafe የበለጠ ይወቁ።

አዎ። በ2-መጠን ክትባት ተከታታይ ውስጥ (እንደ ፋይዘር እና ሞደርና) ወይም ከአንድ መጠን- ክትባት (እንደ ጄ እና ጄ) እስከ 2 ሳምንታት ድረስ ሙሉ ለሙሉ ጥበቃ አልተደረገላችሁም። ክትባቱን ያገኙ ሰዎች COVID-19 ን ለሌሎች ሰዎች እንዳያስተላልፉ ምን ያህል እንደሚከላከል እና ለሌሎች የኮሮና ቫይረስ ልውጦች፣ በኪንግ ካውንቲ ውስጥ እየተሰራጩ እንደሆኑ የሚታወቁ፣ ላይ እንዴት እንደሚሰራ ገና እያየን ነው፡፡

ከክትባት በኋላም ቢሆን፣ ሌሎችን ሰዎች መከላከል ተገቢ ነው፡፡ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ማድረግን፣ ከቤትዎ ውጪ ያሉ የቤት ውስጥ እንቅስቃሴዎችን መቀነስ፣ በቤት ውስጥ ስብስብ ብሎ መቀመጥን፣ ከሌሎች ጋር የሚኖር ግንኙነትን ርቀቱን በጠበቀ እና አጭር በሆነ መንገድ እንዲቀጥል ማድረግ፣ በቤት ውስጥ አየር በደምብ እንዲንሸራሸር ማድረግን እና እጅን አዘውትሮ መታጠብን ይቀጥሉ፡፡

ጥሩው ዜና አንዴ ሙሉ ለሙሉ ከተከተቡ በኋላ፣ በወረርሺኙ ምክኒያት ቆመው የነበሩ አንዳንደ ነገሮችን መልሰው ማድረግ መጀመር ይችላሉ። በኪንግ ካውንቲ ክትባትን ማግኘት ገጽ ላይ ተጨማሪ ያንብቡ።

በራሪ፡ የህዝብ ጤና ምክሮች፡ ከ COVID-19 ክትባት በኋላ

የCOVID-19 ክትባቶች የአሁኑ በሽታን ለመለየት በምንጠቀመዉ የቫይራል ምርመራዎች አዎንታዊ የምርመራ ዉጤት እንድኖሮት ምክንያት አይሆንም።

የጸረ ህዋስ ምርመራዎች አንድ ሰዉ በቫይረስ ወይም ባክቴሪያ ተጠቅቶ እንደሆነ የሚያመላክቱ ጸረ ህዋሳትን ደም ዉስጥ ይፈልጋል። ጸረ ህዋሳት የሚመረቱት አንድ ሰዉ ዉጤታማ ክትባት ሲያገኝ ነዉ። ሰዉነትዎ ለCOVID-19 ክትባት በሽታን የመከላከል ምላሽ ካዳበረ በአንዳንድ ለCOVID-19 ጸረ ህዋስ ምርመራዎች አዎንታዊ የምርመራ ዉጤት ልኖሮት ይችላል።

አዎ ፣ ቀድሞውንም COVID-19 ያለዎት ቢሆንም ክትባት መውሰድ ይኖርብዎታል። ከ COVID-19 ካገገሙ በኋላ እንደገና ከመታመም ምን ያህል ጊዜ እንደሚጠበቁ ባለሙያዎች እስካሁን ድረስ አያውቁም። ምንም እንኳን ቀድሞውኑ ከ COVID-19 ካገገሙ እንኳን COVID-19 ን እንደገና በሚያስከትለው ቫይረስ ሊጠቁ ይችላሉ።

ክትባት ለማግኘት ለ COVID-19 አዎንታዊ ምርመራ ካደረጉ ሦስት ሳምንት መጠበቅ አለብዎት። ለ COVID-19 በሞኖክሎናል ፀረ እንግዳ አካላት ወይም በተሳሳተ የፕላዝማ ሕክምና ከተወሰዱ የ COVID-19 ክትባት ከመውሰዳቸው በፊት 90 ቀናት መጠበቅ አለብዎት ፡፡ ምን ዓይነት ሕክምና እንደደተደረገልዎት እርግጠኛ ካልሆኑ ወይም የ COVID-19 ክትባት ስለመያዝ ተጨማሪ ጥያቄዎች ካሉዎት ዶክተርዎን ያነጋግሩ።

የ COVID-19 ክትባትን ማግኘት የእርሶ ምርጫ ነዉ። የዋሺንግተን ግዛት በአሁኑ ሰአት ክትባቱን አስገዳጅ ማድረግ እያሰበ አይደለም፤ ነገር ግን ስራ ቀጣሪዎች የግድ ሊፈልጉት ይችላሉ፡፡ የማህበረሰብ ጤና COVID-19ን ለመከላከል፣ በ COVID-19 ምክንያት ህመሞችን፣ ሆስፒታል መግባትን፣ ና ሞቶችን ለመቀነስ፣ እና የአሁኑ ወረርሽኝና ለማቆም የCOVID-19 ክትባት ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ዉጤታማ እና ጠቃሚ መንገድ መሆኑን ይጠቁማል።

በአሁኑ ሰአት የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ከሌሎች ሃገሮች ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ለሚመጡ ሰዎች እና የዩናይትድ ስቴትስ ዜጋ ሆነው ወደ ሌላ ሃገራት ተጉዘው መልሰው ወደ የዩናይትድ ስቴትስ ለሚመለሱ ሰዎች፣ የ COVID-19 ክትባት እንዲኖራቸው አይጠይቅም፡፡ ሆኖም ግን፣ የየግል አየር መንገዶች፣ ተሳፋሪዎች በእነርሱ አየር መንገድ ሲጓዙ ክትባት እንዳገኙ የሚያሳይ ማስረጃ እንዲያሳዩ ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡ ጉዞዎትን ከማስተካከልዎት በፊት፣ እባክዎ የአየር መንገድዎን ሁሉንም የጉዞ ደህንነት መስፈርቶች ይፈትሹ፡፡

የክትባት ስርጭት በቀጠለ ቁጥር፣ ሌሎች ሃገሮችም ወደፊት ተጓዦች እንዲገቡ ከመፍቀዳቸው በፊት ክትባት እንዳገኙ የሚያሳይ ማስረጃ ሊጠይቁ ይችላሉ፣ ሆኖም ግን በአሁኑ ሰአት ይህንን የክትባት መስፈርት የጀመረ ሃገር የለም፡፡

ሲዲሲ ሁሉም ወሳኝ ያልሆኑ ጉዞዎችን ተጓዦች እንዳይጓዙ ይመክራል፣ እናም በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ መኖር ስላለበት የውስጥ ጉዞ መመሪያ (ይህ ድህረ-ገጽ በእንግሊዘኛ ብቻ ነው ያለው) አውጥቷል፡፡ ስለጉዞ በብዛት ለሚጠየቁ ጥያቄች (ይህ ድህረ-ገጽ በእንግሊዘኛ ብቻ ነው ያለው) ከሲዲሲ የተሰጡ ምላሾችን እዚህ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡

ክትባት ከተገኘ በኋላም ቢሆን የበሽታውን ወረርሽኝ ለማቆም ሁሉም ሰው(የተከተበም ቢሆን) እራሳቸውን እና ሌሎችን ለመጠበቅ ሲባል የአሁኑን መመሪያ መከተል መቀጠል ይጠይቃል ፡፡ ለበርካታ ወራቶች ጭምብል ማድረጋችንን መቀጠል ያስፈልገናል ፣ ቢያንስ ከ 6 ሜትር ርቀት ላይ ከሌሎች ርቀን ፣ ከቤት ውጭ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በመቀነስ እና በህዝብ ከተጨናነቁ ቦታውች መራቅ፣ ብዙ ጊዜ እጆችን በመታጠብ ፣ የሲዲሲን(CDC) የጉዞ መመሪያ በመከተል እና COVID-19 ያለበት ሰው ጋር ከተጋለጡ በኋላ የኳራንቲን መመሪያን መከተል ያስፈልገናል፡፡