Skip to main content
King County logo

የዋሺንግተን ግዛት የጤና ዲፓርትመንት የግዛታችንንየክትባትስርጭት (ድህረ-ገጹ በእንግሊዘኝ ብቻ ነው ያለው) እና በዙሮች የሚስጥ ክትባት ተገቢነትን ይወስናል።

የተሻሻለ፥ ኣዲሱ የብቃት መስፈርት ምድቦች፡ ዕድሜኣቸው 60 እና ከዛ በላይ የሆኑ፣ ሁለት ወይም ከዛ በላይ መሰረታዊ የጤና እክል ያላቸው፣ እንዲሁም የግምባታ፣ የማኑፋክቹሪን፣ የምግብ ቤቶችና የምግብ ኣቅርቦት ኣገልግሎት ሰራተኞችን ያጠቃልላል። ከታች “ማን ነው ኣሁን ክትባት መውሰድ የሚችለው?” የሚለውን ዝርዝር ይመልከቱ።

የኦበርን፣ ኬንት፣ ረድመንድና ስያትል ጣብያዎችን ጨምሮ ከኪንግ ካውንቲ በኣጋርነት ክትባት በሚሰጡ ቦታዎች ቀጠሮ ለማስያዝ የሚያስችል ኣማራጭ ለማየት “እንዴት ነው መከተብ የምችለው?” የሚለውን እዩ።

የስልክ ድጋፍ ይገኛል

የቋንቋ ትርጓሜ ከፈለጉ የሚከተሉት የስልክ መስመሮች ይገኛሉ:

 • የ WA State COVID-19 ድጋፍ መስመር: 1-800-525-0127 ወይም 1-888-856-5816 (ከዛም # ይጫኑ) ፣ ሰኞ 6am እስከ 10pm ፣ ማክሰኞ እስከ እሁድ 6am እስከ 6pm
 • ኪንግ ካውንቲ COVID-19 የጥሪ ማዕከል: 206-477-3977 ፣ 8am እስከ 7pm

ለቋንቋ ትርጓሜ ፣ ሲገናኙ የሚፈልጉት ቋንቋዎን ይናገሩ።

ክትባቱን እንዴት ማግኝት እንደሚቻል ያሉ መረጃዎች በተደጋጋሚ ይሻሻላሉ። እነዚህ ማሻሻያዎች በፍጥነት እንዲተረጎሙ እየሰራን ቢሆንም፣ ትርጉሙን ለመስራት እና ድህረ-ገጽ ላይ ለመለጠፍ በሚወሰደው ጊዜ ምክኒያት መጓተት ሊኖር ይችላል። ለትእግስትዎ እናመሰግናለን።

በእንግሊዘኛ ያሉ በጣም በቅርብ ጊዜ የተሻሻሉ መረጃዎችን ከ kingcounty.gov/vaccine (ድህረ-ገጹ በእንግሊዘኛ ብቻ ነው ያለው) ማግኘት ይችላሉ።

እንዴት መከተብ ይቻላል

ለሚከተሉት ቡድኖች ክትባቱ መድህንን፣ዝ ዜግነትን ወይም የስደት ሁኔታ ላይ መሰረት ሳያደርግ ክትባቱ ይቀርባል። ለክትባቱ ሂሳብ አይከፍሉም ወይም ደረሰኛ አይቆረጥብዎትም። የክትባቱ ወጪ በሜዲኬይር፣ በሜዲኬይድ እና በአብዛኛዎቹ የግል የመድህን ድርጅቶች ይሸፈናል፣ እናም መድህን ለሌላቸው ሰዎች የክትባቱ ወጪ ይሸፈንላቸዋል።

በአሁኑ ሰአት የክትባት አቅርቦቶች እና ቀጠሮዎች ውስን ናቸው፡፡ መርሃ-ግብር በማስያዝ ወቅት መራዘሞች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ አቅራቢዎች ተጨማሪ ክትባቶችን ሲያገኙ እና ከፍተኛ መጠን ክትባት የሚሰጡ ቦታዎች ሲከፈቱ ክትባትን ማግኘት ቀላል ይሆናል፡፡

በራሪ፡ የCOVID-19 ክትባት ቀጠሮ እንዴት ነው ማስያዝ የሚቻለው? (PDF)

በራሪ፡ በኪንግ ካውንቲ አጋር የክትባት ቦታዎች ያለ ተገኚነት (PDF)


ከመጋቢት (March) 31፣ 2021 ጀምሮ፣ የዋሺንግተን ግዛት የጤና ዲፓርትመንት የዙር 1b4 ክትባት ስርጭትን ጀመሯል።

ለሚከተሉት ቡድኖች ክትባቱ መድህንን፣ዝ ዜግነትን ወይም የስደት ሁኔታ ላይ መሰረት ሳያደርግ ክትባቱ ይቀርባል። ለክትባቱ ሂሳብ አይከፍሉም ወይም ደረሰኛ አይቆረጥብዎትም። የክትባቱ ወጪ በሜዲኬይር፣ በሜዲኬይድ እና በአብዛኛዎቹ የግል የመድህን ድርጅቶች ይሸፈናል፣ እናም መድህን ለሌላቸው ሰዎች የክትባቱ ወጪ ይሸፈንላቸዋል።

ኣዲስ የብቃት መስፈርት (ከ 3/31/21 ጀምሮ):

 • ዕድሜው ከ 60 እስከ 64 የሆነ ግለሰብ

 • ብቁ ለደረጃ 1b3: 16 ወይም ከዛ በላይ ዕድሜ ያላቸው ሆነው በሲዲሲ የጤና ዝርዝር ከኣንድ በላይ የጤና እክል ወይም መሰረታዊ የጤና ችግር ያለባቸው። (ድህረ-ገጽ በእንግሊዘኛ)

 • ብቁ ለደረጃ 1b4:
  • ለከፍተኛ ኣደጋነት የተጋለጡ በኣንዳንድ ተሰብስቦ የሚኖርበት/የሚሰራበት ቦታ ያሉ ግለሰቦች (ነዋሪዎች፣ ሰራተኞች፣ በጎ ፈቃደኞች)፥
   • ኣካለ ጉዳተኞች የሚኖሩበት የቡድን መኖርያ ቤቶች (ግሩፕ ሆም)፣ ከባድ የኣእምሮ ሕመም፣ የኣእምሮ ዕድገት እና ዕውቀትን ማዳበር የተሳናቸው እንዲሁም ኣካል ጉዳተኞች የሚኖሩባቸው ተቋማት፣ በተጨማሪም በደረጃ 1 ያልተካተቱ የኣደንዛዥ ዕፅ ሱሰኞች ማገገምያ የሆኑ የመኖርያ ቤት ተቋማትን ያጠቃልላል።
   • እስር ቤቶች፣ ወህኒ ቤቶች፡ የኣጭር ግዜ ማቆያ ወህኒ ቤቶች እና ተመሳሳይ ተቋማት
   • መኖርያ ቤት ለሌላቸው ግለሰቦች ኣገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት (እንደ ግዜያዊ መኖርያ፡ መጠለያ ቤት)
   • የቤት ውስጥ ዓመፅ ለሸሹ መጠላያ (ዶመስቲክ ቫዮለንስ)
  • ተሰብስቦ መስራት በሚጠይቁ፡ ለከፍተኛ እስከ መሃከለኛ ኣደጋ ተጋላጭነት ባላቸው የሚቀጥሉት ኢንዱስትሪዎች የሚሰሩ ሰራተኞች:
   • ምግብ ቤትና የምግብ ኣቅርቦት ኣገልግሎት
   • ማኑፋክቼሪን
   • ግምባታ (ኮንስትራክሽን)

   ማሳሰብያ: ተሰብስቦ መስራት ሲባል፡ ተራርቆ መስራት በማይቻልበት ዝግ በሆነ ህንፃ ውስጥ ከሌሎች ተደበላልቆ መስራት ማለት ነው። እንደዚህ ባሉ ተቋማት የሚሰሩ ግን ተራርቀው መስራት የሚችሉ፣ ከርቀት መስራት የሚችሉ ወይም ከተቋሙ እየወጡ (off-site) የሚሰሩ ሰራተኞች በዚህ ደረጃ ኣልተካተቱም።

ክትባት ቀጥለው ለተዘረዘሩት ግለሰቦችም ክፍት ነው፥

 • ለዙር 1a ተገቢ የሆኑ (ድህረ-ገጹ በእንግሊዘኝ ብቻ ነው ያለው): ማንኛውም በስራው ምክኒያት በጤና ተቋማት ውስጥ በ COVID-19 የመያዝ እድሉ ከፍተኛ የሆነ ሰው፣ የረጅም ጊዜ እንክብካቤ ማእከላት ሰራተኞች እና ነዋሪዎች፣ እና የጤና እና እንክብካቤ ረዳቶች።

 • ለዙር 1b1 ተገቢ የሆኑ፡
  • 65 አመት እና ከእዛ በላይ የሆናቸው
  • 50 አመት እና ከእዛ በላየ ሆነው በቤት ውስጥ ሁለት እና ከእዛ በላይ ትውልዶች የሚኖሩ ከሆነ፣ (ማለትም በእድሜ የገፋ ሰው እና የልጅ ልጁ)፣ እናም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ከሆነ፣
   • ለብቻ መኖር የማይችሉ እና ከዘመድ ወይም እርዳታ ሰጪ (ክፍያ የሚያገኝ ወይም የማያገኝ) ወይም ከቤት ውጪ የሚሰራ ሰው ካለ
   • ከትንሽ ልጅ ጋር የሚኖር ወይም ለልጁ እንክብካቤ የሚያደርግ፣ እንደ አያት እና የልጅ ልጅ።
  • የፕሪኬ (ፕሪስኩል) እስክ 12ኛ ደረጃመምህራን እና ሰራተኞች
  • የህጻናት እንክብካቤ ሰራተኞች የሚከተሉትን ያካትታል:
   • ፈቃድ ያላቸው የቤተሰብ የልጆች እንክብካቤ አቅራቢዎች እና በቤታቸው ውስጥ የሚኖሩት የቤተሰብ አባላት።
   • ፈቃድ አልባ የሆኑ ቤተሰቦች ፣ ጓደኞች እና የጎረቤት አቅራቢዎች የሥራ ግንኙነቶችን የሕፃናት እንክብካቤ ድጎማ የሚቀበሉ ናቸው። እነዚህ በቤት ውስጥ የሚሰጡ አገልግሎት ሰጭዎች እስከ 6 ልጆችን ሊያገለግሉ ይችላሉ።
   • ECEAP ፣ በዋሽንግተን የመንግስት የገንዘብ ድጋፍ የፕሪኬ (ፕሪስኩል) ትምህርት ቤት አቅራቢዎች። ይህ ከፌዴራል ሄድስታርት ፕሮግራም ጋር ተመሳሳይ ነው ፡፡
   • ወረርሽኙ ከተጀመረበትና ትምህርት ቤቶች ተዘግተው ወደ ኦንላይን ወይም ወደ ሃይብርድ ማስተማር ከተዛወሩበት ጊዜ አንስቶ ለትምህርት የደረሱ ሕፃናት እንክብካቤ ሲያደርጉ የነበሩ ከፈቃድ አልባ የትምህርት ዕድሜ እና ወጣቶች ልማት አቅራቢዎች ፡፡

 • ለዙር 1b2 ተገቢ የሆኑ፡
  • ብዛት ያለበት የሰዎች ስብስብ በሚጠይቁ በሚቀጥሉት ኢዱስትሪዎች የተሰማሩ ከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭነት ያላቸው ወሳኝ ሰራተኞች፡
   • እርሻ
   • የዓሳ ማጥመድ ጀልባ ሰራተኞች
   • የምግብ ዝግጅት
   • የሸቀጣሸቀጥ ሱቅ(Grocery Store) እና የምግብ ባንክ (Food Bank)
   • ማረምያ ቦታዎች (ወህኒ ቤት እስር ቤት እና የኣጭር ግዜ ማቆያ ጣብያዎች)
   • ፍርድ ቤቶች
   • ፈጣን እርዳታ ሰጪዎች፡ በመጀመርያው ደረጃ ያልተካተቱ (ኣስተዳዳሪዎችና ከርቀት-ሪሞት የሚሰሩትን ሳይጨምር)
   • የመዋዕለ ሕፃናት፡ የሕፃናት እንክብካቤ ፕሮግራም ሰራተኞች፡ የወጣቶች ዕድገት፡ የቀን መዋያ ካምፖች (ደይ ካምፕ) እና በ 1b1 ደረጃ ያልተካተቱ

   ብዛት ያለበት የሰዎች ስብስብ ሲባል፡ ከርስ በርስ መራራቅ በማይቻልበት ዝግ በሆነ ክፍል መሆን ማለት ነው።

  • ያረገዙ ሰዎች
  • ለ ከባድ የCOVID-19 ሕመም በከፍተኛ ደረጃ ስጋት ላይ የሚጥል የኣካል ጉዳት ያለባቸው።

ስለ ዋሺንግተን የዋሽንግተን የክትባት ቅደም ተከተል ደረጃ መመርያ (ድህረ-ገጹ በእንግሊዘኝ ብቻ ነው ያለው) ተጨማሪ ይወቁ።

እነዚህን ማምጣት ይገባዎታል፡

 • የልደት ቀን ያለው መታወቂያ፡የሠራተኛ መታወቂያ ወይም በግዛት፣ በጎሳ ወይም በፌዴራል-የተሰጠ መታወቂያ። ስምዎትን እና አድራሻዎትን የያዘ የክፍያ ወረቀት ወይም የባንክ ደብዳቤም መጠቀም ይችላሉ። ለዙር 1a የሰራተኛ መታወቂያን መጠቀም ይቻላል።

 • በላይኛው ክንድዎ ውስጥ መከተብ እንዲችሉ በቀላሉ ለመጠቅለል ቀላል የሆኑ አጭር እጀታዎችን ወይም የተለቀቁ እጀታዎችን ይልበሱ።

እንዴት መድረስ እንደሚቻል

የሚኖሩበት ቦታ ኪንግ ካውንቲ ከሆነና ወደ ክትባት ቦታ ለመድረስ ማጓጓዣ የሚያስፈልግዎ ከሆነ ብዙ ኣማራጮች ኣሉ።

 • መጓጓዣ ያግኙ፥ ለመጓጓዣ፣ የበጎ ፈቃደኞች ፕሮግራሞችና ጉዞዎን ለማቀድ www.findaride.org ይጎብኙ። ብቁ ስለመሆንዎ ጥያቄ ካለዎትና ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ www.findaride.org/covid ይጎብኙ። (ድህረ-ገጽ በእንግሊዘኛ)

 • የኣውቶቡስ ኣገልግሎት፡ ኪንግ ካውንቲ ሜትሮ የአውቶቡስ ትራንስፖርት፣ የአክሰስ ፓራትራንዚት እና የማህበረሰብ ቫን ሻትሎችን ጨምሮ ለክትባት ቀጠሮዎች ብዙ የመጓጓዣ አማራጮችን ይሰጣል፡፡ ከኪንግ ካውንቲ ሜትሮ ስለ ትራንዚት አማራጮች የበለጠ ይረዱ፡፡ ወይም 206-553-3000 ይደውሉ።

  ልብ ይበሉ ፣ በመንዳት በኩል በክትባት ጣቢያዎች የሚራመዱ ደንበኞችን መውሰድ እና መኪና ወይም ትራንሲት ሊፈልጉ አይችሉም ፣ ስለሆነም መጓጓዣ ለእነዚህ አካባቢዎች ጥሩ አማራጭ አይሆንም ፡፡ ከቀጠሮዎ በፊት የመዳረሻ ዝርዝሮችን ከክትባቱ አቅራቢ ጋር ያረጋግጡ ፡፡

 • የሜዲኬድ ወይም ኣፕል ሄልዝ ካርድ ካለዎት ሆፕ ሊንክ ሜዲኬድ 800-923-7433 በመደወል (ብቁነትዎን ያረጋግጡ)

 • በዕድሜ የገፉ ወይም የኣካል ጉዳተኛ ከሆኑ ሜትሮ ኣክሰስ 206-205-5000 ይደውሉ። (ብቁነትዎን ያረጋግጡ)

 • ለበርካታ ሰዎች መጓጓዣ ለማመቻቸት እየጣሩ ነው? ይህንን ቅጽ ይሙሉ ና የሆፕሊንክ ሞቢሊቲ (Hopelink Mobility Management team) ኣባል ሁኔታውን ለመከታተል ከርስዎ ይገናኛል።

በስልክ እርዳታ ወይም ኣስተርጓሚ ካስፈለገዎት፡ የክትባት መጓጓዣ እርዳታ ስልክ (Coordinated Vaccine Transportation Helpline) 425-943-6706 ከሰኞ – ዓርብ ከ8:30 AM – 4:00 PM ባለ ግዜ ይደውሉ። ለኣስተርጓሚ እርዳታ 5 ቁጥርን ይጫኑ።

በራሪ፡ የሕዝብ የጤና ጥበቃ ምክረ ሐሳቦች፦ ከኮቪድ-19 ክትባቶች በኋላ (PDF)


የሁለተኛ ክትባት ቀጠሮ ማስያዝ

ባለ ሁለት መጠን ክትባት የሚወስዱ ከሆነ በክትባቱ ቀጠሮዎ ጊዜ፣ የመጀመሪያ ክትባትዎን ከተቀበሉ በኋላ በክትባት ቀጠሮዎ ላይ ለሁለተኛው ክትባት ቀጠሮ ያስይዙ። ሁለተኛውን ክትባት ከመጀመሪያው ክትባት ከ21 ቀናት በኋላ (Pfizer-BioNTech) ወይም ከ28 ቀናት በኋላ (Moderna) ማግኘት አለበት። ሁለተኛው ክትባት ከቫይረሱ ሙሉ ጥበቃን ይሰጣል።

የጆንሰን እና ጆንሰን (Johnson & Johnson) COVID-19 ክትባት ሁለተኛ መጠን አያስፈልግዎትም፣ አንድ መጠን ሙሉ መከላከያ ይሰጣል ፡፡


ለV-Safe ይመዝገቡ

የበሽታ መከላከል እና መቆጣጠር (CDC) ማዕከል የክትባቱን ደህንነት ለመቆጣጠር V-Safe (ድህረ-ገጹ በእንግሊዘኝ ብቻ ነው ያለው) የተባለ መገልገያ አቅርቧል፡፡ V-Safe በስልኮች ላይ የተመሰረተ መገልገያ ሲሆን የጽሁፍ መልዕክትን እና የድህረ-ገጽ ዳሰሳ ጥናቶችን በመጠቀም ለየሰው የተመቻቸ ለCOVID-19 የጤና መከታተያ የሚያቀርብ ነው፡፡ የCOVID-19 ክትባትን ካገኙ በኋላ የጎንዮሽ ችግር ቢያጋጥሞት ለበሽታ መከላከል እና መቆጣጠጠር ማዕከል (CDC) በቶሎ ማሳወቅ ይችላሉ፡፡፡ የበሽታ መከላከልና መቆጣጠርማዕከል (CDC) ለተጨማሪ መረጃ ሊያናግሮት ይችላል፡፡ ካስፈለገ፣ V-Safe ሁለተኛውን ክትባቶን እንዲያገኙ ሊያስታውስዎት ይችላል፡፡


ያልተፈለጉ የጎንዮሽ (side effects) ምልክቶች ሲያጋጥም ምን መደረግ ኣለበት

ከባድ ኣለርጂ ከፈጠረብዎ፡ 9-1-1- ይደውሉ ወይም በኣቅራብያዎ ወዳለ ሆስፒታል ይሂዱ። ሌላ የሚያሳስብዎ ወይም ኣልለቅ ያለ የጎንዮሽ ስሜት (side effect) ከተሰማዎት ሓኪምዎ ጋ ይደውሉ።

ክትባቱ የፈጠረብዎ ማንኛውም የጎንዮሽ ምልክት ለምግብና መድኋኒት ኣስተዳደር (FDA) / የበሽታ ቁጥጥርና መከላከያ ማእከል (CDC) Vaccine Adverse Event Reporting System (VAERS) ያመልክቱ። የ VAERS ቁጥር 1-800-822-7967 በመደወል ወይም ኦንላይን https://vaers.hhs.gov/reportevent.html በመሄድ ያመልክቱ። በመጀመርያው መስመር 18ቁጥር ሳጥን ላይ የወሰዱትን ክትባት ይጨምሩ።


የCOVID-19 መከላከያ መንገዶችን መከተል ይቀጥሉ

ክትባቶቹ በ COVID-19 ከኢንፌክሽን ፣ ሆስፒታል መተኛት እና ሞት ከፍተኛ መከላከያ ይሰጣሉ ፡፡ ስለዚህ ለምን አሁንም ፊት ሽፋን ማድረግ እና ከሌሎች ጋር መራቅ ያስፈልገናል?

በአሁኑ ጊዜ ብዙ ሰዎች ገና ክትባት አልወሰዱም ፣ ውስን አቅርቦት በመያዝ የክትባት ስርጭት በጣም የመጀመሪያ ደረጃዎች ላይ ነን ፡፡ ክትባቱ የተከተቡ ሰዎችን COVID-19 ን ወደ ሌሎች እንዳያሰራጩ ለመከላከል ክትባቱ ምን ያህል እንደሚሰራ እንዲሁም በኪንግ ካውንቲ ውስጥ እየተሰራጨ በሚታወቀው የኮሮና ቫይረስ ተለዋጮች አይነቶች ላይ እንዴት እንደሚሰራ እየተማርን ነው ፡፡

ከክትባት በኋላም ቢሆን ሌሎችን መከላከል አስፈላጊ ነው ፡፡ ፊት ሽፋን መልበስዎን ይቀጥሉ ፣ ከቤት ውጭ ያሉ የቤት ውስጥ እንቅስቃሴዎችን ይገድቡ ፣ የተጨናነቁ የቤት ውስጥ ቦታዎችን ያስወግዱ ፣ ከሌሎች ጋር አጭር እና ርቀትን ያኑሩ ፣ በቤት ውስጥ የአየር ማናፈሻ ያሻሽሉ እና እጅዎን ብዙ ጊዜ ይታጠቡ ፡፡

በጎነቱ፡ የሚጠበቅብዎ የክትባት መጠን በሙሉ ወስደው እንደጨረሱ በዓለም ኣቀፍ ወረርሽኙ ምክንያት ማድረግ የተሳኑዋቸውን ነገሮች እንደገና ተመልሰው ማድረግ መጀመር ይችላሉ።

ግለሰቦች ክትባቱን ወስደው ጨርሰዋል የሚባሉት፡

 • ሁለቴ የሚወሰዱት እንደ ሞደርና እና ፋይዘር - ክትባቱ ከወሰዱ ከ2 ሳምንታት በኋላ ወይም
 • ኣንዴ የሚወሰዱት እንደ ጆንሶን ኤንድ ጆንሶን - ክትባቱ ከወሰዱ ከ2 ሳምንታት በኋላ

ክትባቱ ከወሰዱ ገና 2 ሳምንት ያልሞላ ከሆነ ወይም ሁለተኛውን መጠን (ዶዝ) ለመውሰድ እየተጠባበቁ ከሆነ ሰውነትዎ ሙሉ በሙሉ ኣልተጠበቀም ያለው። ሰውነትዎ ሙሉ በሙሉ እስኪጠበቅ ድረስ ኣስፈላጊ የመከላከያ እርምጃዎች መከተል ይቀጥሉ።

ክትባቱን ሙሉ በሙሉ ወስደው ከጨረሱ: የሚከተሉትን እንቅስቃሴዎች ማድረግ ይችላሉ፡

 • ቤት ውስጥ፡ ከሌሎች ክትባቱን ወስደው ከጨረሱ ጋር ማስክ ሳይለብሱ መሰባሰብ
 • ቤት ውስጥ፡ ክትባቱ ካልወሰዱ ኣንድ ቤተሰብ (ብቻ) ማስክ ሳይለብሱ መሰባሰብ። ከሰዎቹ መካከል ለከባድ የ COVID-19 ሕመም ተጋላጭ ከሆኑት ምድቦች ከተገኙ (የሰውነት የመከላከያ ዓቅማቸው የተዳከሙ፡ 65 እና ከዛ በላይ ዕድሜ ያላቸው) ኣለ ማስክ ቤት ውስጥ መሰባሰብን ያቁሙ።
 • COVID-19 ካለበት ሰው ጋር የቅርብ ግንኙነት ካደረጉ እና ለሕመሙ ከተጋለጡ፡ ለብቻ መለየት ኣያስፈልግዎት ይሆናል። ምልክቶች ካላሳዩ በስተቀር። እርግጠኛ ለመሆነ ስለ የኳራንቲን መመርያ እዚህ ይመልከቱ።

ክትባቱን ሙሉ በሙሉ ወስደው የጨረሱ ሰዎች የሚቀጥሉትን ጥንቃቄዎች መውሰድ ይቀጥሉ:

 • በህዝባዊ ቦታዎች ማስክ ይልበሱ ተፈላጊውን ርቀት ይጠብቁ
 • መካከለኛና ትልቅ ስብስብ ከመሳተፍ ይቆጠቡ
 • የኣገር ውስጥና ውጭ ጉዞ ዕቅድዎ ያዘግዩ። ከተጓዙ ግን የCDC መስፈርቶችን ይከተሉ
 • የ COVID-19 ምልክቶችን ያስተውሉ፡ በተለይ ከታመመ ሰው የቅርብ ግንኙነት ካደረጉ የ COVID-19 በሽታ ምልክቶች ከታየብዎት ይመርመሩ፡ ከቤት ሳይወጡ ከሌሎች ራቅ ብለው ይቆዩ።
 • የስራ ቦታ መመርያዎችን ይከተሉ።

ኣሁንም ገና ክትባቱ ምን ያህል የ COVID-19 በሽታ ስርጭት የመከላከል ውጤታማነት እንዳለው በመማር ላይ ነን ያለነው፡ ማሻሻያዎች በየወቅቱ እየወጡ ነው።  ስለ ክትባቱን ሙሉ በሙሉ ወስደው የጨረሱ ወቅታዊ መመርያ ይህንን የ CDC ድሕረ ገጽ ይጎብኙ

ተገቢነት ያለው ማነው?

በዋሺንግተን ግዛት ውስጥ ያሉ እድሜያቸው ከ65 አመት በላይ የሆኑ በእድሜ የገፉ አዋቂዎች የ COVID-19 ክትባትን ማግኘት ይችላሉ። እድሜያቸው 50 አመት እና ከዚያ በላይ የሆኑ እና በአንድ ቤት ውስጥ በብዙ ትውልድ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች የተወሰኑ ቅድመ-ሁኔታዎችን እስካሟሉ ድረስ ክትባቱን ለማግኘት ተገቢነት አላቸው። ባለው የክትባት አቅርቦት እጥረት ምክኒያት፣ ሁሉም ሰው በፍጥነት ክትባቱን ማግኘት አይችልም። በኪንግ ካውንቲ ያሉ አቅራቢዎች ተጨማሪ ክትባቶችን እያገኙ እና ይበልጥ ክትባቶች እየተመረቱ በሄዱ ቁጥር የክትባቱ ተገኚነት እየጨመረ ይሄዳል።


ክትባቶች አሁን ላይ የት የት ነው የሚገኙት?

 • የረጅም ጊዜ የእንክብካቤ ማእከላት፣ የነርሲንግ ቤቶች ነዋሪዎች፣ የተረጂ ነዋሪዎች እና ሌሎች የረጅም ጊዜ እንክብካቤ ማእከላት፣ ከፋርማሲዎች ጋር ብሄራዊ ትብብር በመፍጠር ክትባቱን ያሉበት ቦታ ላይ ሆነው እያገኙ ነው።

 • የጤና ተቋማት ስርአቶች፣ ሃኪሞችን፣ ሆስፒታሎችን፣ እና የማህበረስብ ክሊኒኮችን ጨምሮ በኪንግ ካውንቲ ያሉ በእድሜ የገፉ አዋቂዎች ክትባታቸውን የሚያግኙበት መንገድ ነው።

 • ተንቀሳቃሽ የክትባት ቡድኖች፣ በማህበረስብ ጤና እና አካባቢያዊ የእሳት አደጋ ቡድኖች በማስትባበር፣ ከፍተኛ አደጋ ላይ ያሉ በእድሜ የገፉ አዋቂዎችን፣ በአዋቂ ቤተሰብ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ የሚኖሩትን ጨምሮ፣ እየከተቡ ይገኛሉ እና ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው አዛውንት የኑሮ ተቋማት ።

 • ከፍተኛ መጠን ያለው የክትባት ጣቢያዎች በሕዝብ ጤና አስተባባሪነት በደቡብ ኪንግ ካውንቲ ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የሆስፒታሎች እና የሞት መጠን ከ COVID-19 ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የክትትል ጣቢያዎች ፣ ራሳቸውን ችለው መኖር የማይችሉ ግለሰቦችን እና ተንከባካቢዎቻቸውን ጨምሮ።

 • ፋርማሲዎች፡ ልክ በአካባቢያችሁ ፋርማሲ እንደምታገኙት የጉንፋን ክትባት፣ ትልልቅ ፋርማሲዎች - የምግብ መሸጫ መደብሮችን ጨምሮ - የ COVID-19 ክትባትን ቀጠሮ መያዝ።

 • ማህበረሰብ ወይም እምነት ላይ የተመሰረቱ ክሊኒኮች፡ ልክ ክትባቶች በሚገኙበት ጊዜ ለማዳረስ እንደ መመገቢያ ቦታዎች፣ የአዛውንቶች መኖሪያዎች እና እምነትን መሰረት ባደረጉ ድርጅቶች ላይ እነዚህን አይነት ክሊኒኮች ለመክፈት እየታቀደ ነው።

 • ከቤት መውጣት ለሚከብዳቸው ኣረጋውያን ከመኖርያ ቤትዎ ሳይወጡ መከተብ ሌላ ኣማራጭ ነው። ተንቀሳቃሽ የክትባት ቡድንና ከቤት ቤት እየሄዱ የጤና ኣገልግሎት ለማቅረብ ፈቃድ ያላቸው ተቋማት ናቸው እቤትዎ ድረስ መጥተው ክትባቱን የሚሰጡ።