Skip to main content
King County logo

ስለኮሮና ቫይረስ ክትባት ደህንነት ትክክል ያልሆነ መረጃን መስማት ቀላል ነው። አንዳንድ በድህረ-ገጽ እና በአፍ ቃላት እየተነሸራሸሩ ያሉ የተዛቡ መረጃዎች የሚረብሹ ናቸው። የትኛውን ማመን እንዳብን ማወቅ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፣ ስለዚህ እውነታዎቹን ለመረዳት እንዲችሉ ይህንን ገጽ ፈጥረናል።

እውነታ: በኮቪድ-19 ክትባት ውስጥ ምንም ዓይነት ማግኔቲክ (ብረትን የመሳብ ኃይል) ሊያደርግ የሚችል ምንም ነገር የለም።

የተዛባ መረጃ: በብዛት በተሰራጩ ቪዲዮዎች ክትባቶቹ ሰዎችን ማግኔቲክ (ብረትን የመሳብ ኃይል) ባህሪ እንዲኖራቸው ያደርጋሉ እያሉ በሃሰት ተናግረዋል።

ሐቅ: ኮቪድ-19 ክትባቶች በክትባቱ ቦታ ላይ (ክንድዎን ጨምሮ) ምንም ዓይነት የብረት የመሳብ ኃይል ወይም ማግኔቲክ ባህሪያትን ሊሰጥዎት አይችልም።

በክትባቶቹ ውስጥ ምንም ዓይነት የኤሌትሪክማግኔቲክስ ፊልድ እንዲያመነጭ የሚያስችል ንጥረ ነገር የለበትም። ሁሉም የኮቪ-19 ክትባቶች ምንም ዓይነት እንደ ብረት፣ ኒኬል፣ ኮባልት፣ ሊትየም እና ብርቅ የምድር ውህዶች ያሉ ብረቶች የሏቸውም። በተጨማሪ እንደ ማይክሮኤሌትሪክስ ፣ ኤሌክትሮድ ፣ ካርቦንናኖቲዩብ ፣ ወይም ናኖዋየር ሰሚኮንዳክተር ያሉ ምንም አይነት የፋብሪካ ምርቶች የሉባቸውም

የኮቪድ-19 ክትባቶች የመቀመሚያ ሙሉ ውህዶች ዝርዝር በእኛ በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች ገጽ ላይ ይመልከቱ፥ ስለ ኮቪድ-19 ክትባቶች በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች - ኪንግ ካውንቲ


እውነታ: የ COVID-19 ክትባቶች ዘረመሎትን ወይም DNA አይቀይሩም።

የተዛባ መረጃ: ክትባቱ የሰዎችን DNA ሊቀይር እንደሚችል እና ማንነታቸው ሊለውጥ ወይም የቤተሰቡን ቀጣይ ትውልድ ሊለዋውጥ ይችላል የሚል ፍራቻ አለ።

ሐቅ: ሁለቱም የ Moderna እና የ Pfizer ክተባቶች Messenger (የተላላኪ) RNA (ወይም mRNA) ይጠቀማሉ። mRNA ሰውነታችን ጸረ-ህዋሶችን እና ሌሎች በሽታን የሚከላከሉ ህዋሶች እንዲያመረቱ እና እኛን እንዲከላከሉ ያስተምራል።

በ COVID-19 ክትባት ውስጥ የሚገኘው mRNA መቼም ቢሆን የህዋሳችን የውስጠኛው ክፍል - DNA የሚቀመጥበት ቦታ ውስጥ ፈጽሞ አይገባም። ይህ ማለት mRNA፣ DNA ን በየትኛውም መንገድ ሊለውጠው አይችልም ማለት ነው። mRNA ህዋሶቻንን አስተምሮ ሲጨርስ፣ ሰውነታችን ውስጥ ያሉ ማብላያዎች mRNA ን እያብላሉ በማፈራረስ ከሰውነታችን እንዲወገድ ያደርጉታል።


እውነታ: የ COVID-19 ክትባቶች በኮሮና ቫይረስ እንዲያዙ አያደርግዎትም።

የተዛባ መረጃ: የ COVID-19 ክትባቶች በ COVID-19 ሊያስይዝዎት እንደሚችሉ የተዛባ መረጃ አለ።

ሐቅ: በየትኛዎቹም የ COVID-19 ክትባቶች ላይ የኮሮና ቫይረስ የለም። ክትባት በማግኘትዎ ምክኒያት ኮሮና ቫይረስ አይዝዎትም።

ክትባቶቹ የሰውነታችን ህዋሶች ልክ በ COVID-19 ቫይረስ ሽፋን ላይ ያለውን አይነት ፕሮቲን እንዲያመርቱ ያስትምራሉ። ይህንን መመሪያ ለማስተላለፍ፣ ተላላኪ RNA (mRNA) ወይም ጉዳት እንዳያስከትል ሆኖ የተሻሻለ በተለመደ የጉንፋን ቫይረስ ላይ የሚገኘውን ቫይረስ ክትባቶቹ ይጠቀማሉ። ሰውነታችን ይህንን ፕሮቲን መለየት ከተማረ በኋላ፣ የ COVID-19 ቫይረስ ሰውነታችን ውስጥ ቢገባ በቂ የሆነ በሽታን የመከላከል አቅም እንዲገነባ ያስችለዋል።


እውነታ: የ COVID-19 ክትባቶች መለስተኛ የሆኑ የጉንፋን አይነት ምልክቶችን ሊያመጡ ቢችሉም፣ እጅግ አሳሳቢ የሆኑ የጎንዮሽ ጉዳቶች ግን የማጋጠም እድላቸው በጣም አናሳ ነው።

የተዛባ መረጃ: ክትባቱ እጅግ ከባድ የሆኑ አላርጂክ የጎንዮሽ ጉዳቶችን ፣ አናፊላክሲስ በመባል የሚታወቀውን፣ ሰዎች ላይ በማድረስ እጅግ እንዲታመሙ ያደርጋል የሚል የተዛባ መረጃ አለ።

ሐቅ: እንደ የራስ ምታት፣ የሚያቃጥል እጅ፣ ድካም ወይም ትኩሳትን የመሰሉ የጎንዮሽ ጉዳቶችን ክትባቱን ባገኙ በመጀመሪያዎቹ አንድ ወይም ሁለት ቀናት ውስጥ ሊያጋጥምዎት ይችላል። ነገር ግን እነዚህ የጎንዮሽ ጉዳቶች ብዙም አይቆዩም እና ክትባቱ እየሰራ እንደሆነ ማሳያ ናቸው።

እጅግ የከፉ የአላርጂክ ምላሾች (አናፊላክሲስ) የማጋጠም እድላቸው በጣም አናሳ ነው፣ ሆኖም ግን ሊያጋጥሙ ይችላሉ፣ በተለይም እጅድ የከፋ የአላርጂክ ሁኔታ ቀድሞውኑ ባላቸው ሰዎች ላይ። ሁሉም መታከም የሚችሉ ናቸው።

ድንገት አደጋ ቢፈጠር፣ የአደጋ መከላከያ መንገዶች ተዘጋጅተዋል። ከተከተቡ በኋላ ለ15 ደቂቃዎች እንዲቆዩ ይጠየቃሉ፣ በዚህም ለክትባቱ እጅግ የከፋ የአላርጂክ ምላሽ እንደሌልዎት ማረጋገጥ ይቻላል።

ለመጀመሪያው ክትባት የአላርጂክ የጎንዮሽ ጉዳት ከነበርዎት፣ ሁለተኛውን ክትባት ማግኘት የለብዎትም። ስለክትባቱ ለተጨማሪ ሙያዊ ለሆነ ማብራሪያ፣ ይህንን የ CDC (ሲ.ዲ.ሲ.) መመሪያን (ደህረ-ገጹ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ብቻ ነው ያለው) ይመልከቱ።


እውነታ: የ COVID-19 ክትባቶች የመከታተያ መሳሪያ፣ የጽንስ ህዋስ፣ የአሳማ ውጤቶች፣ ጉዳት አምጪ ብረቶችን ወይም መርዛማ ንጥረ-ነገሮችን አይዙም።

የተዛባ መረጃ: ድህረ-ግጽ በክትባቱ ውስጥ ስላሉ ነገሮች በሚነገሩ የውሸት መረጃዎች ነው የተሞላው።

ሐቅ: በ Pfizer እና Moderna ክትባቶች ውስጥ ያለው ቁልፍ ንጥረ-ነገር mRNA የሚባል ዘረመል ነው። ክትባቱ በተጨማሪም ቅባቶች፣ ጨዎች፣ አሴቲክ አሲድ (የአቼቶ ዋና አካል) እና ስኳር ይይዛል። በ Johnson && Johnson (J&&J) ክትባት ውስጥ ያለው ዋና ንጥረ-ነገር ህመም እንዳያስከትል ሆኖ የተሻሻለ የተለመደ የጉንፋን ቫይረስ ነው። የ J&J ክትባት ማረጋጊያዎችን (ጨዎች፣ አልኮሎች፣ ፖሊሶርቤት 80፣ ሃይድሮክሎሪክ አሲድ) እና አሚኖ አሲዶችን ይይዛል።

እነዚህ ክትባቶች ከአማካይ የድንች ጥብስ ያነሰ ንጥረ-ነገሮችን ነው የያዙት!


እውነታ: ወረርሺኙን በፍጥነት በማስቆም፣ የ COVID-19 ክትባቶች ሁሉንም ሰው ይረዳሉ። ክትባቱን ማግኘት በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ ለሆኑ ቡድኖች ውስጥ ያሉ ሰዎችን በሆስፒታል አልጋ የመያዝ እና የመሞት እድልን ይቀንሳል።

የተዛባ መረጃ: በማህበረስብ ጤና እና በጤና ተቋማት ውስጥ በታሪክ የነበረውና አሁንም ያለው የተደራጀ ዘረኝነትን ታሳቢ በማድረግ፣ ሰዎች በክትባት አሰራር እና ክትባት አሰጣጥ ላይ ተገቢ የሆነ የፍትሃዊነት ጥያቄ ያነሳሉ፣ ይህም በክትባት ሙከራዎች ላይ ማን ተጠቃለሎ እንደነበር እና እነዳልነበር ጨምሮ ነው።

ሐቅ: የ COVID-19 ክትባቶች ከመዘጋጀታቸው በፊት፣ የህብረተሰብ አንቂዎች እና ተሰሚነት ያላቸው ሰዎች በታሪክ በነበረው እና አሁንም እየቀጠለ ስላለው፣ በጥቁሮች፣ ነባር ነዋሪዎች እና የተለየ የቆዳ ቀለም ባላቸው ሰዎች ላይ በህክምና ማህበረሰቡ እና በመንግስት ተቋማት ስለሚደርሰው ጉዳት ጥያቄያቸውን አንስተው ነበር። ለጥረታቸው ምስጋና ይግባና፣ በአስረ ሺዎች ከሚቆጠሩ የ COVID-19 ክትባት የሙከራ ተሳታፊዎች የህዝባችንን ብዝሃነት ያንጸባረቃል። ክትባቶቹ በተለያዩ የዘር እና የብሄር ቡድኖች ውስጥ ውጤታማነታቸው እና ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆኑ ታይቷል።

በተጨማሪም፣ የተለየ የቆዳ ቀለም ያላቸው ሰዎች በክትባት ዝግጅት ወቅት የአመራር ሚናን ተጫውተዋል። ለምሳሌ፣ Dr. Kizzmekia Corbett፣ ጥቁር ሳይንቲስት እና የብሄራዊ የጤና ተቋም የኮሮናቫይረስ ክትባት ምርምር ዋና መሪ ተካቶበታል።

በክንግ ካውንቲ ውስጥ የጥቁር፣ ነባር አሜሪካውያን፣ ላቲኖ እና የፓሲፊክ አይላንደር ማህበረሰቦች በ COVID-19 ምክኒያት በከፍተኛ መጠን በሆስፒታል ውስጥ አልጋ ይዘዋል እናም ሞተዋል። እነዚህ ማህበረሰቦች በክትባቱ ከፍተኛ ጥቅም ከሚያገኙት ውስጥ ይመደባሉ።