Skip to main content
King County logo

ማን ነው ብቁ ?

ማንኛውም ቢያንስ 5 ዓመት ዕድሜ ያለው በወቅቱ የ COVID-19 ክትባት ለመውሰድ ብቁ ነው። ክትባቱ፡ በወቅቱ 5 ዓመት ዕድሜ ላልሞሉ ግለሰቦች እንዲሰጥ ኣልተፈቀደም ያለው። የትናንሽ ልጆች የክሊኒክ ሙከራዎች እየተካሄዱ ይገኛል።

የ COVID-19 ክትባት ምርጫ ለወጣቶች (teens)

 • ፋይዘር: ቢያንስ 5 ዓመት ዕድሜ ላላቸው
 • ጆንሶን ኤንድ ጆንሶን፡ ቢያንስ 18 ዓመት ዕድሜ ላላቸው
 • ሞዴርና: ቢያንስ 18 ዓመት ዕድሜ ላላቸው

የጆንሰን እና ጆንሰን (J&J) ክትባት ከ50 አመት ዕድሜ በታች ለሆኑ ሴቶች የደም መርጋት ችግር የማስከተል አነስተኛ ስጋት አለዉ። የፋይዘር (Pfizer) ወይም የሞደርና (Moderna) ክትባቶች የህን አይነት ስጋት የለባቸውም። በዚህም ምክንያት የተነሳ ለመጀመሪያውም ሆነ ለማጠናከሪያው ዙር ክትባት ከJ&J ክትባት ይልቅ የፋይዘር (Pfizer) ወይም የሞደርና (Moderna) ክትባቶች ብትወስዱ ይመከራል (ድህረገጹ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ብቻ ነው)።

ለክትባት ቀጠሮ ስታስይዝ፡ ለዕድሜ ክልልህ ብቁ ተብሎ የተፈቀደለት ክትባት እየሰጡ መሆኑን ኣረጋግጥ።

young girl receiving vaccination

ወደ ክትባት ጣብያ ምን ይዘህ መምጣት እንደሚኖርብህ

 • ዕድሜህን የሚያረጋግጥ ሰነድ፥ የስተይት፡ ጎሳ ወይም በፈደራል መንግስት የተሰጠ መታወቅያ ወረቀት፣ የትውልድ ሰነድ (birth certificate)፣ የት/ቤት መታወቅያ ወረቀት ወይም ስምና የትውልድ ቀን የሚያሳይ የሕክምና ወረቀት ይዞ መምጣት ይቻላል።

 • ኣጭር ኣጅጌ ልበስ፥ ወይም በቀላሉ ወደላይ የሚሰበሰብ እጅጌ፡ ክትባቱ በላይኛው የክንድ ክፍል ለመውሰድ እንዲያመች።

 • ስልጣን ባለው አዋቂ ሰው የተሰጠ ፈቃድ: ዕድሜዎ ከ18 ዓመት በታች ከሆነ: ክትባት ለማግኘት ስልጣን ካለው አዋቂ ሰው ፈቃድ ማግኘት ያስፈልግዎታል። ከቤተሰብ ነጻ ሆነው የሚኖሩ ከሆነ : አዋቂ ሰው አግብተው ከሆነ: ወይም የክትባት ጣቢያው የበሰሉ/አዋቂ ልጅ (mature minor) መሆንዎትን ከወሰነ ለራስዎ ፈቃድ መስጠት ይችላሉ። ሁሉም የክትባት ጣቢያዎች የበሰለ/አዋቂ ልጅ ውሳኔዎችን ሊሰጡ አይችሉም።

 • ለልጆች ፈቃድ ለመስጠት የሚችሉ ስልጣን ያላቸው አዋቂዎች የሚከተሉትን ያካትታል:

  • የጤና እንክብካቤ ውሳኔዎችን ለእርስዎ መስጠት እንዲችሉ ከፍርድ ቤት ፈቃድ የተሰጣቸው አዋቂዎች (ህጋዊ ሞግዚት: አሳዳጊ: ከቤት ውጭ እንዲሆኑ የታዘዘበት)
  • ወላጅ
  • የጤና እንክብካቤዎትን አስመልክቶ ውሳኔ እንዲሰጥ ከቤተሰብ በጽሁፍ ፈቃድ የተሰጠው አዋቂ ሰው
  • ለጤና እንክብካቤዎት ሃላፊነት ያለበት የቅርብ ዘመድ የሆነ አዋቂ ሰው
  • በአንዳንድ ሁኔታዎች: የት/ቤት ነርስ: የት/ቤት አማካሪ: ወይም መኖርያ ቤት የሌለው ተማሪ ጉዳይ አስፈጻሚ

  ስልጣን ያለው አዋቂ ሰው በክትባት ቀጠሮው ላይ ከርስዎ ጋር የማይገኝ ከሆነ ስልጣን ያለውን አዋቂ ሰው ማረጋገጫ ወይም በህግ ነጻ መሆንዎትን የሚያረጋግጡ ማስረጃዎችን ለማሳየት የሚያስፈልጉ ነገሮችን በተመለከተ ክትባቱን ከሚስጥዎት ድርጅት ያጣሩ።

የህብረተሰብ ጤና - የሲያትልና ኪንግ ካውንቲ ለልጆች የCOVID-19 ክትባት ፈቃድ መስጫ ፎርም (PDF)

ይህ ቅጽ በህብረተሰብ ጤና የሲያትል እና ኪንግ ካውንቲ የክትባት መስጫ ጣቢያዎች እንዲሁም በኦበርን እና ኬንት የጋራ የክትባት ጣቢያዎች እና የህብረተስብ ጤና ክሊኒኮች ስራ ላይ ይውላል። ስልጣን ያለው አዋቂ ሰው በክትባት ቀጠሮው ላይ ከርስዎ ጋር የማይገኝ ከሆነ ይህ ቅጽ እንደ ጽሁፍ ማረጋገጫ ሊያገለግል ይችላል። እንዲሁም የህብረተሰብ ጤና ሰራተኛ ስልጣን ካለው አዋቂ ሰው በስልክ የቃል ማረጋገጫ ወይም የጽሁፍ ማስታወሻ ሊቀበል ይችላል። የክትባት ቀጠሮዎት በህብረተሰብ ጤና ጣቢያ ካልሆነ ስልጣን ያለውን አዋቂ ሰው ማረጋገጫ ወይም በህግ ነጻ መሆንዎትን የሚያረጋግጡ ማስረጃዎችን ለማሳየት የሚያስፈልጉ ነገሮችን በተመለከተ ክትባቱን ከሚስጥዎት ድርጅት ያጣሩ።


በፌዴራል የሲቪል መብት ህግ መሰረት: የማህበረሰብ ጤና-ሲያትል እና ኪንግ ካውንቲ በማናቸውም ፕሮግራም ወይም ስራዎች ላይ ጥበቃ በሚደረግላቸው ግለሰቦች ምድብ: ሁሉንም ያካተተና በዘር ሳይገደብ : በመልክ: በመጡበት የትውልድ ስፍራ/አገር: ሃይማኖት: የጾታ ማንነት (የጾታ አገላለጽን አካቶ):የጾታ ኦሪየንቴሽን: የአካል ጉዳተኛነትን: እድሜ: እና የጋብቻ ሁኔታ ላይ መሰረት ያደረገ ማናቸውንም ልዩነቶች አያደርግም። ቅሬታ ካልዎትና ክስ መመስረት ከፈለጉ: ወይም አድሎአዊነትን በተመለከተ ጥያቄ ካልዎት እባክዎትን የኪንግ ካውንቲ የሲቪል መብቶች ፕሮግራምን በ civil-rights.OCR@kingcounty.gov206-263-2446(እባክዎትን ለትርጉም አገልግሎት ቋንቋዎትን ይግለጹ); TTY ሪሌይ 7-1-1; ወይም በፖስታ አድራሻ (401 5th Ave, Suite 800, Seattle, WA 98104) ያግኙ።


Link/share our site at kingcounty.gov/youthvaccine/amharic