Skip to main content

የኮቪድ -19 ክትባት

COVID-19 ክትባት

ኤፕሪል 28, 2023 የተሻሻለው (ቢቫለንት) ክትባት እድሜያቸው 6 ወር እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ሰዎች ይመከራል።

ከኤፕሪል 19,2023 ጀምሮ የሲዲሲ COVID-19 ክትባት ምክሮች፡፡

ዕድሜው 6 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነ ማንኛውም ሰው 1 የተሻሻለውን የፒፋይዘር ወይም የሞደርና COVID-19 ክትባት ከወሰደ (እንግሊዝኛ ብቻ) ወቅታዊ ክትባት እንደወሰድ ይቆጠራል።

አንዳንድ ሰዎች ተጨማሪ የኮቪድ፡ COVID-19 የማጠናከሪያ ዙር ክትባቶች ሊያገኙ ይችላሉ፡፡

  • እድሜያቸው 65 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች 1 ተጨማሪ የትሻሻለ COVID-19 4ኛ ማጠናከሪያ ዙር ክትባት ወይንም መጀመሪያ ከተሻሻለው COVID-19 ክትባት ከውሰዱ ተጨማሪ ወራት በኋላ ሊያገኙ ይችላሉ።
  • መካከለኛ ወይም ከባድ የበሽታ መከላከያ ችግር ያለባቸው ሰዎች 1 ተጨማሪ የተሻሻለውን COVID-19 2ኛ ማጠናከሪያ ዙር ወይንም መጀመሪያ ከተሻሻለው COVID-19 ክትባት ከውሰዱ ተጨማሪ ወራት በኋላ ሊያገኙ ይችላሉ።

እድሜያቸው ከ6 ወር እስከ 5ዓመት የሆኑ ህጻናት ብዙ COVID-19 ክትባት ሊፈልጉ ይችላሉ፣ ቢያንስ 1 የተሻሻለ የፒፋይዘር ወይም ሞደርና ክትባት። ቀደም ሲል በተቀበሉት የክትባት መጠን እና በእድሜ ላይ የተመሰረተ ነው።

ምን ያህል መጠን እንደሚፈልጉ ጥያቄዎች ካለዎት እባክዎን የጤና እንክብካቤ አቅራቢዎን ያነጋግሩ።

የክትባት ቦታዎችን እና ቀጠሮዎችን ለማግኘት በኪንግ ካውንቲ ውስጥ እንዴት ክትባት ማግኘት እንደሚቻል የሚገልጸውን ድህረገፅ ይጎብኙ።

ክትባቱን እንዴት ማግኝት እንደሚቻል ያሉ መረጃዎች በተደጋጋሚ ይሻሻላሉ። እነዚህ ማሻሻያዎች በፍጥነት እንዲተረጎሙ እየሰራን ቢሆንም፣ ትርጉሙን ለመስራት እና ድህረ-ገጽ ላይ ለመለጠፍ በሚወሰደው ጊዜ ምክኒያት መጓተት ሊኖር ይችላል። ለትእግስትዎ እናመሰግናለን።

በእንግሊዘኛ ያሉ በጣም በቅርብ ጊዜ የተሻሻሉ መረጃዎችን ከ kingcounty.gov/vaccine (ድህረ-ገጹ በእንግሊዘኛ ብቻ ነው ያለው) ማግኘት ይችላሉ።

  በኪንግ ካውንቲ የኮቪድ-19 ክትባት እንዴት ማግኘት እችላለሁ?

እድሜው 6 ወር እና ከዚያ በላይ የሆነ ማንኛውም ልጅ በአሁኑ ጊዜ ለCOVID-19 ክትባት እና ማጠናከሪያ ክትባቶች ብቁ ነው።

ስለብቁነት የበለጠ ይወቁ እና ኪንግ ካዉንቲ ካዉንቲ ዉስጥ ክትባት ማግኘት

መርጃዎች:

የማጠናከሪያ ዙር ክትባት ማን ማግኘት እንደሚችል፣ መቼ እንደሚወሰዱት እና የትኛውን አይነት ማግኘት እንዳለቦት ወቅታዊ መመሪያ:

CDC እድሜያቸው 5 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ማናቸውም ግለሰቦች እናም መካከለኛ ወይም ከባድ የበሽታ መከላከያ ችግር ላለባቸው ግለሰቦች (immunocompromised) ሶስተኛውን ክትባት እንዲወስድ ይመክራል (ድህረ ገፁ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ብቻ ነው)። ሦስተኛው ክትባት የመጀመሪያው የክትባት ተከታታይ አካል እንጂ ማጠናከሪያ ዙር አይደለም።

የበሽታ መከላከል ችግር ያለባቸው ህጻናቶች እና ጎልማሳዎች ብቁ በሚሆኑበት ጊዜ የማጠናከሪያ ዙር ክትባት መውሰድ አለባቸው።

የክትባት ቦታዎችን እና ቀጠሮዎችን ለማግኘት በኪንግ ካውንቲ ውስጥ እንዴት ክትባት ማግኘት እንደሚቻል የሚገልጸውን ድህረገፅ ይጎብኙ (ድህረ ገፁ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ብቻ ነው)።

የፌደራል መንግስት እስከ 2023 ክረምት ድረስ እንደሚቆዩ የሚገመቱ ከፍተኛ መጠን ያላቸውን የ COVID-19 ክትባቶችን ገዛ። የ COVID-19 ክትባቶች መድህን ባይኖራቸውም እንኳን ለሁሉም ሰዎች ብሔራዊ የክትባት አቅርቦቱ እስቀሚያልቅ ድረስ ነፃ ሆነው ይቆያሉ።

የፌደራል ክትባት አቅርቦት ካለቀ በኋላ፦

  • የ COVID-19 ክትባቶች በዋሽንግተን ላሉ ህጻናት ነፃ ሆነው ይቀጥላሉ
  • የአዋቂዎች የ COVID-19 ክትባቶች በአብዛኛዎቹ በግል መድን፣ Medicare (“Apple Health”) እና Medicaid/CHIP  ይሸፈናሉ።
  • መድን የሌላቸው ሰዎች በተወሰኑ የአካባቢ ፋርማሲዎች እና የማህበረሰብ ጤና ጣቢያዎች የ COVID-19 ክትባቶችን ማግኘት ይችላሉ

አብዛኛዎቹ የግል የጤና መድን ዓይነቶች በሽተኛውን ሳያስከፍሉ በጤና አጠባበቅ አቅራቢው በኔትዎርካቸው ውስጥ ለሚሰጡ የ COVID-19 ክትባቶች መክፈላቸውን መቀጠል አለባቸው። የግል የጤና መድን ያላቸው ሰዎች ከኔትዎርካቸው ውጪ የሆነ አቅራቢ ቢከትባቸው ከፊል ወጪውን መክፈል ሊኖርባቸው ይችላል።

የህዝበ ጤና - ሲያትል እና ኪንግ ካውንቲ እና ሌሎች የነጻ የክትባት ክሊኒኮችን እያቀረቡ ነው። ለእነዚህ ክሊኒኮች ፍትሃዊ አቅርቦት ቅድሚያ የሚሰጡት ጉዳይ ነው። ተጨማሪ መረጃ በኪንግ ካውንቲ ክትባትን ማግኘት ገጽ ላይ ይገኛል።

ስለ የኮቪድ-19 ክትባት የበለጠ ለማዋቅ


በፌዴራል የሲቪል መብት ህግ መሰረት: የማህበረሰብ ጤና-ሲያትል እና ኪንግ ካውንቲ በማናቸውም ፕሮግራም ወይም ስራዎች ላይ ጥበቃ በሚደረግላቸው ግለሰቦች ምድብ: ሁሉንም ያካተተና በዘር ሳይገደብ : በመልክ: በመጡበት የትውልድ ስፍራ/አገር: ሃይማኖት: የጾታ ማንነት (የጾታ አገላለጽን አካቶ):የጾታ ኦሪየንቴሽን: የአካል ጉዳተኛነትን: እድሜ: እና የጋብቻ ሁኔታ ላይ መሰረት ያደረገ ማናቸውንም ልዩነቶች አያደርግም። ቅሬታ ካልዎትና ክስ መመስረት ከፈለጉ: ወይም አድሎአዊነትን በተመለከተ ጥያቄ ካልዎት እባክዎትን የኪንግ ካውንቲ የሲቪል መብቶች ፕሮግራምን በ civil-rights.OCR@kingcounty.gov206-263-2446(እባክዎትን ለትርጉም አገልግሎት ቋንቋዎትን ይግለጹ); TTY ሪሌይ 7-1-1; ወይም በፖስታ አድራሻ (401 5th Ave, Suite 800, Seattle, WA 98104) ያግኙ።


Link/share our site at kingcounty.gov/covid/vaccine/amharic

expand_less