Skip to main content
King County logo

ከ መስከረም 6 ጀምሮ በኪንግ ካውንቲ ውስጥ ከ 500 ወይም ከዚያ በላይ ሰዎች ጋር ከቤት ውጭ ዝግጅቶች ላይ ለሁሉም ሰዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስኮች ያስፈልጋሉ፣ እና በሕዝባዊ የቤት ውስጥ ቦታዎች ማስፈለጋቸውን ይቀጥላሉ።

ከጥቅምት 25 ጀምሮ ደንበኞች እንደነዚህ ያሉ ቦታዎች ላይ ለመግባት የ COVID-19 ክትባት ማረጋገጫ ሰነድ ወይም አሉታዊ ምርመራ እንዲያሳዩ ይጠየቃሉ፡

 • የውጪ ዝግጅት ቦታ ላይ: 500 ወይም ከ500 በላይ ሰዎች በሚገኙበት የውጪ ዝግጅት ቦታ ላይ (የሙያዊ እና የኮሌጅ ስፖርት መስጫ ቦታዎችን እና የመዝናኛ ቦታዎችን ጨምሮ)
 • የቤት ውስጥ የመዝናኛ ዝግጅት ቦታዎች ወይም ተቋማት ላይ (የሙያዊ ስፖርት መስጫ ቦታዎችን ፣ መዝናኛዎችን ፣ የስነጥበብ ሥራ ቦታዎችን ፣ የቲያትር ቤቶችን ፣ ሙዚቃ ሥፍራዎችን ፣ ጂም እና ኮንፈረንስ መስጫ ቦታዎችን ጨምሮ)
 • ምግብ ቤቶች እና ቡና ቤቶች ላይ (የቤት ውስጥ መመገቢያ ቦታዎችንም ጨምሮ)። ይህ ከቤት ውጭ ያሉ የመመገቢያ ቦታዎችን ፣ ቴክአዌ ደንበኞችን እና በዋናነት እንደ ምግብ ቤት የማያገለግሉ ቦታዎችን ለምሳሌ እንደ የምግብ መደብሮችን አይመለከትም።

ይህ ከ 12 ዓመት በታች ላሉ ሕፃናት አይመለከትም

ለበለጠ መረጃ የኪንግ ካውንቲን ትዕዛዝ እና የእኛን የማስክ መመሪያ ገፅ ይመልከቱ።

የክትባት ማረጋገጫ ፖስተር

በክትባት ማረጋገጫ መስፈርቶች ውስጥ የተካተቱ የንግድ እና የዝግጅት ቦታዎች ይህንን ምልክት/ፖስተር በሁሉም የህዝብ መግቢያዎች ላይ ማሳየት አለባቸው።

የስልክ ጥሪ ማዕከል፡ እንዴት አስተርጓሚ ማግኘት እንደሚቻል

ስለ COVID-19 ጥያቄ አለዎት? የኪንግ ካውንቲ የኮሮና ቫይረስ የስልክ ጥሪ ማእከል አስተርጓሚዎች አዘጋጅተዋል።

አስተርጓሚ ካስፈለገዎት፡

 1. 206‑477‑3977 ይደውሉ
 2. አስቀድሞ የተቀረጸ መልዕክት ከሰሙ ሰው እስኪያናግርዎ ይጠብቁ።
 3. የፈለጉትን ቋንቋ በእንግሊዘኛ አጠራሩ ይንገሩ። ለምሳሌ “አማርኛ” ከማለት ፈንታ “አማሐርክ” ይበሉ።
 4. የስልክ ጥሪዎ የተቀበለ ሰው፡ አስተርጓሚ ወዳለበት ስልክ ይደውላል። ስልኩን ሳይዘጉ ይጠብቁ። አስተርጓሚ እስኪቀርብ መስመር ላይ ይጠብቁ።
 5. ያለዎት ጥያቄ አስተርጓሚውን ይጠይቁ።

እኛ ስለ ስደተኝነት ሁነታ አንጠይቅም፤ማንኛውም ሰው ሁነታዉ ከግምት ውስጥ ሳይገባ እርዳታ ያገኛል።


የ COVID-19 መምራዎች

ከርስዎ በተለይ ደግሞ ለCOVID-19 በከፍተኛ ተጋላጭ ለሆኑት ስጋት ለመቀነስ፤

 • ቤት ይቆዩ በተጨማሪም ሲታመሙ ህዝብ ወዳለበት እንዳይወጡ።
 • አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር ህክምና አካባቢ መሆንን ማስወገድ። ሆኖም ከታመሙ ወደ ዶክተርዎ ቢሮ ከመሄድዎ በፊት ይደዉሉ።
 • ባይታመሙም እንኳን በተቻለ መጠን ሆስፒታሎችን፣ የረጅም ግዜ መንከባከቢያ ቦታዎችን ወይንም ነርሲንግ ቤቶችን መጎብኘትን ያስወግዱ። ከነዚህ ቦታዎች አንዱ ጋ መሄድ ካለብዎት፣ ከዚያ የሚቆዩበትን ግዜ ይገድቡ በተጨማሪም 6 ጫማ ከታማሚዎች ይራቁ።
 • አስፈላጊ ካልሆነ በቀር ድንገተኛ ክፍሎች እንዳይሄዱ። የድንገተኛ ህክምና አገልግሎቶች ቅድምያ በጣም ለተጎዱት ነዉ ማገለገል ያለባቸዉ። ሳል፣ ትኩሳት ወይንም ሌላ ምልክት ካለብዎ መጀመሪያ መደበኛ ዶክተርዎ ይደዉሉ።
 • እጅዎን በሳሙናና ዉሃ በየጊዜዉ መታጠብ፣ በሶፍት ወይንም ክንድዎ ላይ ማሰል፣ ና ዐይኖን፣አፍንጫ፣ ወይንም አፎን መንካት ማስወገድን ጭምር ያሉትን ምርጥ የግል ንጽህና ልማዶችን ያድርጉ።
 • በተለይ ለኮሮናቫይረስ በከፍተኛ ተጋላጭነት ስጋት ያለብዎት ከሆኑ ከታመሙ ሰዎች ይራቁ።
 • በየጊዜው የሚነኩ እቃዎችንና ላያቸዉን ያጽዱ (እንደ በር እጀታዎችና መብራት ማብሪያ/ማጥፊያዎች)። መደበኛ የቤት ማጽጃዎች ዉጤታማ ናቸዉ።
 • ብዙ እረፍት ያግኙ፤ ብዙ ፈሳሽ መጠጣት፤ ጤናማ ምግቦችን መብላት ና ጫናዎትን መቆጣጠር የሰዉነትዎን በሽታ የመከላከል ችሎታን ጠንካራ እንደሆነ ለመጠበቅ።

ኢንፎግራፊክ


ቨድዮ


ፖስተሮች

የ COVID-19 አደጋ ለመቀነስ ሠራተኞቹ ምልክቶቹን በማተምና በመለጠፍ ከ ደንበኛ ጋር በመግባባት ይተባበራሉ።

እርስበርስ ለመረዳዳት ዝግጁ ሁኑ። ጠንካራ የመተሳሰብ ስሜት ከዚህ ከባድ ወቅት እንድናልፍ ይረዳናል።


Link/share our site at kingcounty.gov/covid/amharic