Skip to main content
Our website is changing! Starting March 31, 2023 our website will look different, but we're working hard to make sure you can still find what you need.  
King County logo

ወደ King County Metro እንኳን በደህና መጡ! ይህ መመሪያ እርስዎ መጓጓዣ እንዴት ደረጃ በደረጃ መጠቀም እንደሚችሉ ያሳይዎታል። በእኛ ስለተጓዙ እናመሰግንዎታለን!

ደረጃ 1: ጉዞዎን ያቅዱ

ተመራጭ የአውቶቡስ መስመሮችዎን፣ እና የት አውቶቡሱ ላይ እንደሚሳፈሩና የት እንደሚወርዱ ይፈልጉ።

ወደtripplanner.kingcounty.gov, ይግቡና ከዚያም የመነሻ አድራሻዎን እና ወዴት እንደሚሄዱ ይጻፉ። ሰዓት እና ቀን ይምረጡ፣ እና የመጓጓዣ አማራጮችዎ ይመጡልዎታል።

ወይም ለMetro የደንበኞች አገልግሎት ከሰኞ እስከ አርብ ከ6 a.m.–6 p.m. ሰዓት በስልክ ቁጥር206-553-3000ይደውሉ።

አስተርጓሚ ከፈለጉ ልንረዳዎ እንችላለን! የእርስዎን ቋንቋ ከሚናገር ከአንድ ሰው ጋር ለመገናኘት 1ን ይጫኑ። የመስማት ችግር ያለባቸው ተጓዦች በWA Relay በ711 መደወል ይችላሉ።

ደረጃ 2: አውቶቡስዎን ያግኙ

ሁሉም አውቶቡሶች የመስመር ቁጥር ወይም ፊደል አላቸው። የአውቶቡስ ማቆሚያዎች በቋሚ ላይ የተደረገ ምልክት አላቸው። ይህ ምልክት እዛ ቦታ ላይ የሚቆሙ ሁሉንም የአውቶቡስ መስመሮች ይዘረዝራል። ለመጓዝ የሚፈልጉበት መስመር መዘርዘሩን ያረጋግጡ።

አንዳንድ የአውቶቡስ ማቆሚያዎች በሚጠባበቁበት ወቅት የሚጠቀሙባቸው መጠለያዎችና ወንበሮች አሏቸው።

አንድ አውቶቡስ ማቆሚያዎ ላይ መጥቶ በሚቆምበት ወቅት መስመርዎን ከአውቶቡሱ ፊት ለፊት ወይም የጎን ክፍል ላይ ይመልከቱ።

ማንኛውም ጥያቄዎች ካሉዎ ሹፌርዎ ሊረዳዎት ይችላል።

አስፈላጊ ከሆነ ጓደኛ ወይም የቤተሰብ አባል የመስመር ቁጥርዎን እና የጉዞ አቅጣጫዎን በቁራጭ ወረቀት ላይ እንዲጽፍልዎ ያድርጉ። ይህን ለሹፌሩ ወደ አውቶቡሱ በሚገቡበት ወይም በሚወርዱበት ወቅት ሊያሳዩት ይችላሉ።

ደረጃ 3: ወደ አውቶቡሱ ይግቡና ይክፈሉ

የጉዞ ክፍያዎን ለመክፈል ከእነዚህ ዘዴዎች መካከል አንዱን ይምረጡ።

ORCA ካርድ ያስነኩ – ቀላሉና ተመራጩ ዋጋ።

በታሪፍ ሳጥኑ ውስጥ የአውቶቡስ ቲኬት ያስገቡ።

Transit GO ቲኬት በስልክዎ መተግበሪያ ይግዙና ለሹፌሩ ያሳዩት።

ትክክለኛውን የገንዘብ ወይም ሳንቲሞች መጠን ያስገቡ። ሹፌሮች መልስ ሊሰጡዎት አይችሉም። በጥሬ ገንዘብ ወይም በ አውቶቡስ ቲኬት በሚከፍሉበት ወቅት በሁለት ሰዓት ውስጥ ሌላ አውቶቡስ ላይ በሚሳፈሩበት ጊዜ ሹፌርዎን በወረቀት እንዲያስተላልፍልዎት ይጠይቁት።

የትኛው ታሪፍ/ ክፍያ ለእርስዎ ይስማማል?

ለእርስዎ ተመራጭ የሆኑትን የታሪፍ/ ክፍያ አማራጮች ለማግኘት kingcounty.gov/WhichOrcaFareን ይጎብኙ።.

ብስክሌቶች እና መጓጓዣ

እያንዳንዱ የMetro አውቶቡስ በፊት ለፊት የእቃ ማስቀመጫው ላይ እስከ ሶስት ብስክሌቶች መጫን ይችላል። በመጓጓዣ ማቆሚያ ላይ መቼ ብስክሌት መጫን እና መቼ ማውረድ እንደሚፈልጉ ለሹፌሩ ያሳውቁት።

ተደራሽነት

ሁሉም አውቶቡሶች መወጣጫዎች አሏቸው። ተሽከርካሪ ወንበር ወይም ጋሪ ካሉዎ፣ ወይም አውቶቡስ ላይ ለመሳፈር ተጨማሪ እርዳታ ከፈለጉ ሹፌሩን መወጣጫ እንዲሰጥዎ ይጠይቁት።

ከሹፌሩ በቀጥታ በስተጀርባ ያሉት ወንበሮች ለአካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያን ወይም ልጆች ላሏቸው ወላጆች የተዘጋጁ ናቸው። እንደ ጋሪዎች ወይም ተሽከርካሪ ወንበሮች ለመሳሰሉ እቃዎች ደህንነት የደህንነት ማሰሪያዎችን ይጠቀሙ።

ደረጃ 4: ለማስቆም ይጠይቁና ይውረዱ

የእርስዎ ማቆሚያ ሲጠራ ይመልከቱ እንዲሁም ያዳምጡ። ቀጣዩ የእርስዎ መውረጃ ከሆነ ቢጫውን ገመድ ይሳቡት ወይም ቀዩን የ “አቁም/STOP” ቁልፍ ይጫኑ።

የ “ማቆም ተጠይቋል/STOP REQUESTED” ምልክት ይበራና ደወል ይደውላል። የፊት በር መወጣጫ ካላስፈለግዎ በቀር በጎን ወይም የኋላ በር ይውረዱ።

ተጨማሪ የጉዞ አማራጮችን ይወቁ

እኛ የአውቶቡስ ሲስተም እና ሌሎችንም ነን።

ተደራሽ አገልግሎቶች

Metro አገልግሎቶቻችንን በእኩል ደረጃ ተደራሽ ለማድረግ ይተጋል። የአውቶቡስ ተሳፋሪም ይሁኑ ወይም ከመጓጓዣ ፕሮግራሞቻችን መካከል አንዱን እየሞከሩ እርስዎን ከማህበረሰብዎ ጋር ለማገናኘት ዝግጁ ነን።

ስለተደራሽነት አማራጮች ይወቁ
Ride Pingo

ከKent Station እና ወደ Kent Station ለመጓዝ እንዲሁም ከKent Valley በአገልግሎቱ ክልል ውስጥ ወደሚገኝ ወደ የትኛውም መዳረሻ ለመጓዝ ጉዞዎን ያስመዝግቡ።

በ Ride Pingo ይጀምሩ
Via to Transit

ወደ Othello፣ Rainier Beach/Skyway፣ Renton እና Tukwila ለመሄድ እና ለመመለስ ጉዞዎን በVia to Transit መተግበሪያ አማካኝነት ያስመዝግቡ።

ይጀምሩ Via
የጉዞ አማራጮችን ይወቁ

Metro ለKing County የተለያዩ ተለዋዋጭ የመጓጓዣ አማራጮችን ያቀርባል። ከሰፊ የአውቶቡስ ኔትወርካችን፣ የፓራትራንዚት አገልግሎቶቻችን፣ ከWater Taxi፣ ቫንፑል፣Link ቀላል የጉዞ መስመር እና ሌሎችም መካከል ይምረጡ።

ሁሉንም የጉዞ አማራጮች ይመልከቱ

ከእኛ ጋር ይገናኙ

የመጓጓዣ ማሳወቂያ ምዝገባ

አዲስ ተመዝጋቢዎች

ለመመዝገብ የግንኙነት መረጃዎን ያስገቡ። በኢሜይልና በጽሁፍ ለመመዝገብ ከፈለጉ ሁለት ጊዜ መመዝገብ ይኖርብዎታል።

ወቅታዊ ተመዝጋቢዎች

ምርጫዎችዎን ለመቆጣጠር ኢሜይልዎን ወይም የሞባይል ቁጥርዎን ያስገቡ።