Skip to main content

Lynnwood Link Connections (Amharic) - Programs & Projects

Lynnwood Link Connections

የ Link light rail እስከ Lynnwood ስለሚዘረጋ የ Lynnwood Link Connections የመጓጓዣ ፕሮጀክት ሰሜን ምዕራብ King County እና በደቡብ ምዕራብ Snohomish County ላሉ ማሕበረሰቦች የትራንዚት ፍላጎት መለዋወጥን ይፈታል በተጨማሪ የመንቀሳቀስ አማራጮችን ያሻሽላል። Metro ከማህበረሰቡ በሚሰጡ አስተያየቶች ላይ በመመስረት የአውቶቡስ መስመሮችን ለማስተባበር ከሌሎች አጋሮች መካከል ከ Sound Transit (በእንግሊዘኛ) እና Community Transit (በእንግሊዘኛ) ጋር በትብብር እየሠራ ነው።

የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ምልከታ

በ 2024 እና 2026 Seattle፣ Shoreline፣ Mountlake Terrace እና Lynnwood ላይ ያሉ አምስት አዳዲስ ጣብያዎችን ለማካተት Sound Transit የ Link light rail ያስፋፋል።

ከአዳዲሶቹ የቀላል ባቡር ጣቢያዎች በተጨማሪ፣ በ 2025 መጀመሪያ ላይ Sound Transit የ ST 522 Express route ን እቅድ ከተያዘለት Bus Rapid Transit አገልግሎት በ Bothell እና Shoreline መካከል ሊለውጥ ይችላል።

የ Link light rail አገልግሎት ወደ Lynnwood Transit Center ማስፋፋትን እና ወደ ST 522 Express አገልግሎት ለመቀየር ለመዘጋጀት፣ለሚለዋወጡ የእንቅስቃሴ ፍላጎቶች ምላሽ ለመስጠት እና በታሪክ ላልተጠበቁ ህዝቦች የእንቅስቃሴ ተደራሽነት ለማሻሻል Metro በአጠቃላይ ሰሜን Seattle፣ Shoreline፣ Lake Forest Park፣ Kenmore፣ Bothell እና Mountlake Terrace ላይ ያሉ ማሕበረሰቦችን የሚያገለግል በሰሜን ምዕራብ አዉራጃ King County የእንቅስቃሴ ፕሮጀክት እያስጀመረ ነዉ።

ይህ ፕሮጀክት ከ Sound Transit Link light rail ጋር የተገናኘ እና ከ Sound Transit እና Community Transit አገልግሎቶች ጋር የሚገናኝ የተሻሻለ የመጓጓዣ አውታረ-መረብን ያቀርባል።

ፕሮጀክቱ ከ Sound Transit፣ Seattle Department of Transportation (SDOT፣ የሲያትል የትራንስፖርት ክፍል)፣ ከ Shoreline፣ Community Transit፣ እና ሌሎች አጋሮች ጋር በመቀናጀት ይከናወናል።

የፕሮጀክቱ ግቦች

በ Lynnwood Link Connections ፕሮጀክት በኩል፣ የ Metro ዓላማዎች የሚከተሉት ናቸው፦

 1. የእኛ የአሁን እና የወደፊት ተደራሽ ደንበኞች አስፈላጊ አካል ለሆኑ፣ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ህዝቦች ተንቀሳቃሽነትን ማሻሻል (በ የ Mobility Framework - በእንግሊዘኛ እንደተገለጸው)።
 2. በፕሮጀክቱ አካባቢ የሚጓዙትን የአሁን እና የወደፊት ደንበኞችን በእኩልነት ማሳወቅ፣ ማሳተፍ እና ማበረታታት።
 3. ለ Link መስፋፋት በትራንዚት አውታር ላይ የሚደረጉ ለውጦችን እና የማህበረሰብ ፍላጎቶችን ምላሽ የሚሰጥ የተቀናጀ አገልግሎት ማቅረብ።
 4. የትራንዚት ስርዓቱን ቅልጥፍና፣ ውጤታማነት እና የአካባቢን ዘላቂነት ማሻሻል።

የእኩልነት ተፅእኖ ግምገማ

የ Lynnwood Link Connections ፕሮጀክት የታሰቡ የአማራጭ መስመር ለዉጦች መንቀሳቀስን እንደሚያሻሽሉ እና King County ላይ የሚኖሩ ቅድሚያ የሚሰጣቸዉ ህዝቦች የመንገድ ተደራሽነት ማግኘታቸዉን ለማረጋገጥ Equity Impact Review (EIR፣ የእኩልነት ተጽእኖ ግምገማ) ጥናት ያካትታል። በእያንዳንዱ የማቀድ ሂደት ላይ፣ Metro ቴክኒካዊ ውሂቦችን እና ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ህዝቦች ጋር በመገናኘት የተገኘውን ውጤት በመገምገም አገልግሎት ላልደረሳቸው ማህበረሰቦች ላይ ያለውን ተጽዕኖ በመረዳት እና የእቅድ ውሳኔዎችን ያሳውቃል። የሕዝብ ተሳትፎ እና የ EIR ማጠቃለያዎች ከዚህ በታች ባለው የሒደት እና የጊዜ ሰሌላ ክፍል ስር ከ ደረጃ 3 ተሳትፎ በኋላ ይጋራሉ።

የመንገድ መረጃ

የሚከተሉት መንገዶች እንደ Lynnwood Link Connections ፕሮጀክት ክፍል ሊሆኑ ለሚችሉ ለውጦች ይመረመራሉ።

የ Metro መንገዶች፦ 5፣ 16X፣ 20፣ 28፣ 45፣ 64፣ 65፣ 67፣ 73፣ 75፣ 301፣ 302፣ 303፣ 304፣ 320፣ 322፣ 330፣ 331፣ 345፣ 346፣ 347፣ 348፣ 372

የ Sound Transit Express መንገድ፦ 522

የ Lynnwood Link Connections ወቅታዊ የአውታረ መረብ አካባቢ ካርታ

የ PDF ካርታ ይክፈቱ

የ Sound Transit የጣቢያዎች ካርታ (በእንግሊዘኛ)፦

የእንቅስቃሴ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች

ሂደት 1 ላይ ከዳሰሳዎች፣ Community-Based Organizations (CBOs፣ ማህበረሰብ መሰረት ካደረጉ ድርጅቶች) ጋር የተደረጉ ውይይቶች እና ከእኛ Partner Review እና ከ Mobility Boards ቀጥተኛ አስተያየት አግኝተናል። አስተያየቶቹን ተመልክተን የጋራ የሆኑ መልእክቶችን አግኝተናል እና አዳዲስ የአውቶብስ መስመሮችን ለመፍጠር ጥቅም ላይ የሚውሉ የሚከተሉትን ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች አጠቃልለናል።

አዲስ እና የተሻሻሉ ምስራቅ-ምዕራብ ትራንዚት መገናኛዎችን መፍጠር።

ወደ/ከ አስፈላጊ፣ ቅድሚያ የሚሰጣቸዉ ህዝቦች የሚኖሩበት በማህበረሰብ የተለዩ መዳረሻዎች እና በ 2026 ብዙ የቤት ልማት እቅድ ያላቸዉ ቦታዎች ትራንዚት ማቅረብ።

ዋናዋና እና አስፈላጊ መዳረሻዎችን የሚያገለግሉ የምሽት ትራንዚት አገልግሎት ማሻሻል።

ወደ/ከ ዋና መዳረሻዎች እና/ወይም ትልቅ አቅም ያለዉ ዋና ትራንዚት (RapidRide፣ Link፣ Route522 BRT፣ ወዘተ) ጋር የሚያገናኙ መንገዶችን ድግግሞሽ መጠገን እና ማሻሻል።

ዋና እና አስፈላጊ መዳረሻዎችን የሚያገለግሉ የቅዳሜና እሁድ ትራንዚት አገልግሎትን ማሻሻል።

የትራንዚት መተላለፍያዎች ለሁሉም አሽከርካሪዎች በተለይም ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ህዝቦች ምቹ፣ ተደራሽ፣ አስተማማኝ እና በተቻለ መጠን እንከን የለሽ መሆናቸውንማረጋገጥ።

የአማራጭ መስመር እቅድ

Metro ለሰሜን ምዕራብ King County እና ለደቡብ Snohomish County የተወሰነ ክፍል የመጨረሻ የመስመር ሃሳቦችን እያቀረበ ነው። የእርስዎ ግብረ መልስ ከ 2024 ጀምሮ ከ Link የቀላል ባቡር ማስፋፊያ እስከ Lynnwood ዳርቻ የሚከፈተውን የአውቶቡስ አውታረመረብን ለማጠናቀቅ ይረዳል።

Lynnwood Link Connections – የምዕራፍ 3 አገልግሎት ፕሮፖዛል

የ PDF ካርታ ይክፈቱ

ፈጣን ፍቺዎችን

 • ፍትሃዊ ቅድሚያ የሚሰጠው ቦታ፦ ከፍተኛ መጠን ያለው ቅድሚያ የሚሰጠው ህዝብ ያለው ጂኦግራያዊ አካባቢ።
 • ድግግሞሽ፦ በአውቶቡስ ጉዞዎች መካከል ያለው የደቂቃዎች ብዛት።
 • ተደጋጋሚ አገልግሎት፦ በየ 15 ደቂቃው ወይም በተሻለ ከሰኞ እስከ አርብ ከ 6am እስከ 7pm እና በየ30 ደቂቃው ወይም በተሻለ በምሽት እና ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሰሩ የታቀዱ የአውቶቡስ አገልግሎት ደረጃዎች።
 • Metro Flex: በበርካታ የ King County አካባቢዎች ጉዞዎችን የሚያቀርብ በጥያቄ መሰረት የሚሰጥ የመጓጓዣ አገልግሎት። አሽከርካሪዎች የ Metro Flex ስማርት ስልክ መተግበሪያን በመጠቀም ወይም ለቦታ ማስያዣ መስመር ስልክ በመደወል ጉዞዎችን ማስያዝ ይችላሉ።
 • ማለዳ እና ከሰአት በኋላ ብቻ የሚሰጥ አገልግሎት፦ በማለዳ እና ከሰዓት በኋላ የሚሰጡ የጉዞ ጊዜያት (ከ 6 እስከ 9am እና ከ 3 እስከ 7pm
 • ቅድሚያ የሚሰጣቸው ህዝቦች፦ ጥቁር፣ ተወላጅ እና ጥቁር የማህበረሰብ አባላት፤ ዝቅተኛ ወይም ምንም ገቢ የሌላቸው፤ ስደተኞች ወይም ጥገኞች፤ አካል ጉዳተኞች፤ ወይም በቋንቋ የተለያየ የሆኑ ናቸው።

በምዕራፍ 2፣ Metro በመንገድ ሃሳቦች እና የቅድሚያ የሚሰጣቸው የእንቅስቃሴ ፍላጎቶች እንዴት መፍትሄ እንደሚሰጣቸው ግብረ መልስ አግኝቷል። Metro ከህዝብ ዳሰሳ ጥናት፣ ከማህበረሰብ አቀፍ ድርጅቶች፣ የትኩረት ቡድን ስብሰባዎች፣ በአካል ከተሰራጩ፣ በመስመር ላይ እና በአካል ከተደረጉ የማህበረሰብ ስብሰባዎች፣ ከአጋር ከተሞች እና ድርጅቶች የተሰጡ አስተያየቶችን ጥቅም ላይ በማዋል የምዕራፍ 2 ዋና ዋና ችግር ያለባቸው ቦታዎችን ዝርዝር አዘጋጅቷል።

Metro ከማህበረሰብ አቀፍ Mobility Board (የእንቅስቃሴ ቦርድ) እና Partner Review Board (አጋር የግምገማ ቦርድ) ጋር በመስራት የቅድሚያ የሚሰጣቸውን ደረጃዎች (ከትንሹ እስከ በጣም አስፈላጊ) በተሳትፎ ወቅት ተለይተው ለታወቁት ዋና ዋና ችግር ያለባቸው ቦታዎች መድቧል። የደረጃ አሰጣጡ Metro በመጀመሪያ ከፍተኛ ፍላጎት ባላቸው አካባቢዎች ላይ እንዲያተኩር ረድቶታል። ይህ የደረጃ አሰጣጥ ሂደት የማህበረሰብ ግብረመልስን፣ ፍትሃዊነትን እና የመጓጓዣ ስርዐት ንድፍ የተሻሉ ተሞክሮዎችን በመጠቀም ነው።

በምዕራፍ 2 ተሳትፎ ወቅት ተለይተው በቀረቡት ዋና ዋና ችግሮች ላይ ተጨማሪ መረጃ በምዕራፍ 2 የተሳትፎ ማጠቃለያ ውስጥ ተካትቷል.

የምዕራፍ 3 ፕሮዛሉ ሲዘጋጅ፣ Metro በማህበረሰብ የተለዩ ፍላጎቶችን መፍትሄ በመስጠት ላይ ያተኮረ እና በምዕራፍ 2 ውስጥ አዎንታዊ ግብረ መልስ ያገኘ አገልግሎት እንዲቆይ አድርጓል። የ Mobility Board እና Partner Review Board የምዕራፍ 3 ፕሮፖዛልን ለማሻሻል እና ለማጠናቀቅ ተጨማሪ ግብረ መልስ አቅርበዋል።

የምዕራፍ 3 ፕሮፖዛል ዋና ዋና ነጥቦች የሚከተሉትን ያካትታሉ።

 • Link ቀላል ባቡር ዛሬ ለሌለው የምስራቅ ምዕራብ የአውቶቡስ አገልግሎት በጣም ተደጋጋሚ የሆነ የሰሜን ደቡብ አገልግሎት ይሰጣል።
 • በመላው የፕሮጀክት አካባቢ አዲስ እና የተከለሱ የምስራቅ ምዕራብ ግንኙነቶችን መፍጠር።
 • ፍትሃዊ ለሆኑ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ቦታዎች እና ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ህዝቦች፣ Linden Ave እና Lake City አካባቢን ጨምሮ ምቹ የመጓጓዣ መዳረሻን መጠበቅ ወይም ማሻሻል።
 • ከትምህርት ቤቶች እና ከማህበረሰብ መዳረሻዎች ጋር፣ በተለይም በ Seattle እና Shoreline ውስጥ አዳዲስ ግንኙነቶችን መጠበቅ ወይም መፍጠር።
 • ተጨማሪ የምሽት እና የቅዳሜ እና እሁድ የአውቶቡስ አገልግሎት እና አነስተኛ በማለዳ እና ከሰአት በኋላ ብቻ የሚሰጥ አገልግሎትን ወደሚያጠቃልለው የሙሉ ቀን ተደጋጋሚ አውታረ መረብ ሽግግርን መቀጠል
 • በሰሜን Kenmore፣ Lake Forest Park ከ Mountlake Terrace Link light ቀላል ባቡር ጣቢያ ጋር የሚገናኝ አዲስ፣ ተፈላጊ የ Metro Flex አገልግሎት።
 • የተሻሻለ የምስራቅ/ምዕራብ ግንኙነቶች፣ ከአዲስ፣ ተደጋጋሚ የሙሉ ቀን አገልግሎት በ N 145th (Routes 72፣ 333 እና 522 BRT)፣ አዲስ ተከታታይ አገልግሎት ከ 125th እስከ 130th (አዲስ Route 77) ላይ፣ እና በ Lake City፣ Northgate እና Greenwood (አዲስ Route 61) መካከል አዲስ ግንኙነት።
 • Mበ Lake City እና Link መካከል ያሉ በርካታ አዳዲስ ግንኙነቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
  • Shoreline South/148th፦ Routes 65፣ 72 እና 522 BRT
  • NE 130th ጎዳና ጣቢያ፦ Route 77
  • Northgate ጣቢያ፦ Routes 61፣ 67፣ 75፣ 322፣ እና 348
  • Roosevelt ጣቢያ፦ Routes 67 እና 77
  • University of Washington ጣቢያ፦ Routes 65፣ 67፣ 72፣ 75 እና 77።
 • ከ Roosevelt ጣቢያ እና University of Washington (አዲስ Route 77) ጋር የሚገናኝ፣ በ Lake City Way ላይ አዲስ የሙሉ ቀን አገልግሎት።
 • ከሰሜን Lake City እስከ Nathan Hale High School እና Jane Addams Middle School (Route 65) የቀጠለ ግንኙነት፣ እና ከ Pinehurst (አዲሱ Route 77) ጀምሮ አዲስ ግንኙነት።
 • ለ Sanford Hildebrant Towers የቀጠለ አገልግሎት፣ ከ Shoreline Place እና Shoreline South/148th ጣቢያ ጋር (የተሻሻለ Route 345)።
 • ቀጥታ አገልግሎት ወደ Ingraham High School (አዲስ Route 365)።
 • ከ Northgate እስከ North Seattle College እና Northwest Hospital (የተሻሻለ Route 345 እና አዲስ Route 365) ተደጋጋሚ አገልግሎቶች።
 • በ Link, routes 5, 40, 62 እና RapidRide D እና E Lines በኩል ወደ ዳውንታውን Seattle የቀጠለ ተደጋጋሚ አገልግሎት።
 • በዚህ አካባቢ ያሉ አንዳንድ መንገዶች ከሲያትል ከተማ ጋር ተጨማሪ ትብብር ይፈልጋሉ።
 • የተሻሻሉ የምስራቅ/ምዕራብ ግንኙነቶች፣ አዲስ ተደጋጋሚ የሙሉ ቀን አገልግሎት በ N 145th (routes 72፣ 333፣ እና 522 BRT) እና N 175th (Route 333) ላይ፣ እና የተሻሻለ አገልግሎት በ N 185th (Route 348) እና N 155th (Route 345)
 • በ Link፣ Route 5 እና RapidRide E Line በኩል ወደ ዳውንታውን Seattle የቀጠለ ተደጋጋሚ አገልግሎት።
 • ከ Link (routes 72, 333, 348 እና 522 BRT) ጋር ግንኙነቶችን የሚያቀርቡ አዲስ ተደጋጋሚ የሙሉ ቀን መንገዶች።
 • ወደ Shoreline Community College የተሻሻሉ ግንኙነቶች ከShoreline South/148th Station ተደጋጋሚ የሙሉ ቀን አገልግሎት ከሚሰጥ አዲስ Route 333 እና ከMountlake Terrace Station ግንኙነት የሚያቀርበው የተሻሻለው Route 331 እንዲሁም ከዛሬ ምሽት በኋላ አገልግሎት ይሰጣል።
 • ወደ Shorewood High School (አዲስ Route 333 እና የተሻሻለ Route 331) እና Shorecrest High School (የተሻሻለ Route 65) የተሻሻለ አገልግሎት።
 • በ Shoreline South/148th Station እና Shoreline North/185th ጣቢያ መካከል በ 5th Ave NE ላይ ቀጣይነት ያለው አገልግሎት፣ ወደ Link (አዲስ Route 365) ቀጥተኛ ግንኙነትን ያቀርባል።
 • በ Shoreline South/148th Station እና Shoreline North/185th ጣቢያ መካከል በ 5th Ave NE ላይ ቀጣይነት ያለው አገልግሎት፣ ወደ Link (አዲስ Route 365) ቀጥተኛ ግንኙነትን ያቀርባል።
 • ወደ Northwest Hospital እና North Seattle College (የተሻሻለ Route 345 እና አዲስ Route 365) የቀጠሉ የቀን ሙሉ ግንኙነቶች።
 • በ Aurora Village፣ Northgate፣ downtown Seattle፣ እና First Hill (Route 303) መካከል የቀጠለ ማለዳ እና ከሰአት በኋላ የሚሰጥ አገልግሎት።
 • ወደ University of Washington Bothell የሚቀጥል ወደ Mountlake Terrace Station የሚደረግ አዲስ ግንኙነት፣ እና የተሻሻለ የምሽት እና የቅዳሜ እና እሁድ አገልግሎት (የተሻሻለ Route 331)።
 • አዲስ ፈጣን እና ተደጋጋሚ ግንኙነት ከ Bothell, Kenmore, እና Lake Forest Park ወደ Shoreline South/148th Link ጣቢያ(Sound Transit Route 522 Bus Rapid Transit).
 • በሰሜን Kenmore፣ ሰሜን Lake Forest Park እና ደቡብ ምስራቅ Mountlake Terrace አዲስ የMetro Flex የአገልግሎት አካባቢ: ይህ በጥያቄ መሰረት የሚቀርብ አገልግሎት ወደ Mountlake Terrace Station፣ Route 522 BRT፣ Lake Forest Park Town Center, Kenmore Park–and–Ride፣ እና ሌሎችም ጋር ግንኙነቶችን ያቀርባል።
 • አዲስ የሙሉ ቀን ተደጋጋሚ አገልግሎት ከMountlake Terrace በShoreline (Route 333) ወደሚገኙ ቁልፍ መዳረሻዎች።
 • በ Kenmore፣ Lake City፣ Northgate፣ downtown Seattle እና First Hill (የተሻሻለ Route 322) መካከል ያለው ማለዳ እና ከሰአት በኋላ የሚሰጥ አገልግሎት።
 • በ University of Washington Bothell እና በ Seattle ካምፓሶች መካከል የበለጠ ተደጋጋሚ እና ፈጣን አገልግሎት በ Route 522 BRT ወደ Link ቀላል ባቡር በ Shoreline South/148th Station ወይም ወደ አዲስ ተደጋጋሚ Route 72 በ 145th በኩል ይገኛል።

በእነዚህ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ግብረ መልሶች መሰረት፣ የመጨረሻዎቹ የመንገድ ለውጥ ካርታዎች እና ዝርዝሮች ከስር ባለው በእያንዳንዱ ሉህ ላይ ተካትተዋል።

በዚህ መንገድ ከተጓዙ፦ የታሰበ ለዉጥ፦ እነዚህን መንገዶች ይገምግሙ(PDFs)፦
5 5
16 5
20 44 45 61 62
28 5 28 77
45 31 32 45 75
64 62 65 link light rail iconLink
65 65
67 67
73 45 67 72 77 348
75 75
301 303 333 348
302 303 322 331 348
303 303
304 333 345 348
320 61 322 522 BRT link light rail icon Link
322 77 322
330 65 72 333 345
331 331
345 5 333 345
346 303 345 348 365
347 333 348 365
348 348
372 72 331 522 BRT link light rail icon Link
Metro Flex Metro Flex
ST 522 72 77 522 BRT link light rail icon Link
Link link light rail icon Link light rail

ሂደት እና የጊዜ መስመር

 • የቅድመ-ተሳትፎ እቅድ
 • ደረጃ 1 የፍላጎት ግምገማ
  Mobility Board ለፍላጎቶች ቅድሚያ ይሰጣል
 • ደረጃ 2 የአገልግሎት ፅንሰ ሀሳቦች
  Mobility Board ጥቆማዎችን ይመለከታል
 • ደረጃ 3 የአገልግሎት ፕሮፖዛል
  Mobility Board የመጨረሻ ፕሮፖዛል ይመለከታል
 • የ King County ካዉንስል

በዚህ የመጀመርያው የተሳትፎ ደረጃ Metro የተጎዱ ማህበረሰቦች አሽከርካሪዎችን ጨምሮ ስለ ፕሮጀክቱ ወሰን እና ራዕይ ለመላ ህዝቡ ያሳውቃል እና የአገልግሎት ፍላጎቶች መረጃን ከህዝቡ፣ አሽከርካሪዎች እና ዋና ባለድርሻ አካላት ይሰበስባል። ይህ መረጃ የ Mobility Board እና የ Metro ሰራተኞች በደረጃ 2 ተሳትፎ ወቅት ለህዝብ አስተያየት ረቂቅ አገልግሎት አብረዉ ጽንሰ-ሀሳብ ሲያዘጋጁ ይረዳል።

ክፍል 1 የተሳትፎ ማጠቃለያ (PDF)

በዚህ ሁለተኛ ምዕራፍ የተሳትፎ ወቅት፣ Metro የፕሮጀክቱን ወሰን፣ ራዕይ እና የታቀዱ የአውቶቡስ መሰመሮችን በምዕራፍ 1 ላይ ከተሰበሰቡ መረጃ ጋር በተጨናነቁ አካባቢዎች የሚገኙ አሽከርካሪዎችንም ጨምሮ ለጠቅላላው ህዝብ ያጋራል። ስለ ማህበረሰብ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች እና የመጨረሻውን የአውቶቡስ መስመሮች ጥቆማ እንዴት ማሳወቅ እንዳለባቸው የበለጠ ለማወቅ በታቀዱት የመንገድ ለውጦች ላይ የተሰጠ ግብረ መልስ እንሰበስባለን። 

ስለ ማህበረሰብ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች እና የአውቶቡስ መንገዶችን የመጨረሻ ፕሮፖዛል እንዴት ማሳወቅ እንዳለባቸው የበለጠ ለማወቅ በታቀደው የመንገድ ለውጦች ላይ ምላሽ እንሰበስባለን።

ስለ የተሳትፎ እድሎች ማህበረሰቦችን ለማሳወቅ የሚያገለግሉ እንቅስቃሴዎች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፦

 • Community–Based Organizations (CBOs) ጋር መስራት
 • ባለብዙ ቋንቋ የማስታወቂያ ስራዎችን ማስተናገድ
 • ጋዜጣዊ መግለጫ እና ባለብዙ ቋንቋ ብሎግ ልጥፍ
 • የትራንዚት ማንቂያዎች፣ የአሽከርካሪዎች ማንቂያዎች እና የአሰልጣኝ ፖስተሮች
 • ዲጂታል እና/ወይም የታተሙ ባለብዙ ቋንቋ ቁሳቁሶችን ማሰራጨት
 • Metro ድህረ ገጽ ላይ የሚገኝ ባለብዙ ቋንቋ መረጃ
 • በአውቶብስ ማቆሚያዎች፣ የትራንዚት ማዕከሎች እና የማህበረሰብ ዝግጅቶች ላይ በአካል መገኘት

ክፍል 2 የተሳትፎ ማጠቃለያ (PDF)

የቨርቹዋል ማህበረሰብ መረጃ ክፍለ ግዜዎቻችን ቅጂ፡

አንድን ቅጂ በተለያየ ቋንቋ መስማት የሚፈልጉ ከሆነ፣ ያሳውቁን! ኢሜይል የሚያደርጉልን (በፈለጉት ቋንቋ) በ፡ haveasay@kingcounty.gov

በመጨረሻ የተሳትፎ ደረጃ፣ Metro የአውቶቡስ አገልግሎት ፕሮፖዛል ለህዝብ ያቀርባል፣ ይህምም ከምዕራፍ 2 የተገኘው የማህበረሰብ ግብአት እንዴት እንደዚህ ማሻሻያዎች ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ያብራራል። የመጨረሻ ከማድረጋችን በፊት የአገልግሎት ፕሮፖዛል ማሻሻልያ መንገዶች ላይ አስተያየት እንጠይቃለን። በመቀጠል የማህበረሰቡ ግብአት፣ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች እና ፍትሃዊነት እንዴት በመጨረሻው የአገልግሎት ፕሮፖዛል ላይ እንዴት ተጽዕኖ እንዳሳደረ እንገመግማለን እንዲሁም ሌሎች ተዛማጅ የሆኑ ቀጣይ እርምጃዎችን እንገልጻልን። 

እንዴት መሳተፍ ይችላሉ

የማህበረሰብ ተሳትፎ

በባለ ሶስት-ደረጃ የማህበረሰብ ተሳትፎ ሂደት፣ Metro የመጓጓዣ ፍላጎቶችን በማዳመጥ ላይ፣ አሽከርካሪዎች ስለሚገጥሟቸው እንቅፋቶች ጥናት ማድረግ፣ እና በሰሜን ምዕራብ King County መጓጓዣን ማሻሻያ እድሎች ላይ ያተኩራል። የመንቀሳቀስ ችግሮችን ስለሚያስከትሉ የለውጦች ሁኔታዎች ከአካባቢው ማህበረሰቦች መረጃ በማግኘት፣ እና ከማህበረሰቡ አባላት እና ባለድርሻ አካላት ጋር የወደፊት የመጓጓዣ አማራጮችን የንግድ ልውውጥ እና ጥቅሞችን ማሰስ እንቀጥላለን።

የቨርቹዋል ማህበረሰብ መረጃ ክፍለ ግዜዎቻችን ቅጂ፡

Mobility Board

Metro ከትራንዚት ጋር በተያያዙ ከውሳኔ ሰጭ ንግግሮች በታሪክ የተተዉ እና በእነዚህ ውሳኔዎች ያልተመጣጠነ ተፅእኖ ያደረባቸዉ የሰዎች ቡድኖችን በእኩልነት የሚወክል 15 አባላትን የያዘ የ Lynnwood Link Connections Mobility Board ን ሰብስቧል። የ Mobility Board ዋና ሚና በሰሜን ምዕራብ King County የተቀናጀ የክልል ትራንዚት አውታረ-መረብን ለማዳበር እና ለማጣራት ከ Metro ሰራተኞች ጋር መተባበር ነው።

Partner Review Board

Metro ከፕሮጀክት አጋሮች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ካለው ግላዊ ተሳትፎ በተጨማሪ Metro የውጭ ባለድርሻ አካላትን ቡድን በማሰባሰብ እንደ የፅንሰ-ሃሳብ መገምገሚያ ቦርድ ሆኖ እንዲያገለግል Partner Review Board በመባል የሚታወቅ አምጥቷል። ይህ Board በፕሮጀክቱ አካባቢ ከሚገኙ ባለስልጣናት እና ዋና ዋና ተቋማት ተወካዮች፣ የማህበረሰብ-አቀፍ ድርጅቶች መሪዎች እና የአጋር ትራንዚት ኤጀንሲዎች ተወካዮችን ያካትታል። የ Partner Review Board ዋና ተግባር በ Mobility Board የተዘጋጁ የአገልግሎት ጽንሰ-ሐሳቦችን ማሳወቅ፣ መገምገም እና አስተያየት መስጠት ነው።

ስለ Partner Review Board የበለጠ ይወቁ።

እኛን ያግኙን

በሚመርጡት ቋንቋ ይህን ኢሜል ተጠቅመው haveasay@kingcounty.gov ያግኙን

ለአጠቃላይ አስተያየቶች

በ Metro አገልግሎቶች ላይ አጠቃላይ አስተያየቶች ወይም ግብረ መልስ ካሉዎት በ (206) 553-3000 ላይ ይደውሉልን። የትርጉም አገልግሎቶች አሉን!

ማሻሻያዎችን ለመቀበል ይመዝገቡ (በእንግሊዘኛ)

አዲስ ተመዝጋቢዎች

ስለ ዝግጅቶች እና ዋና ዋና ክስተቶች የፕሮጀክት ማሻሻያዎች እና ማስታወቂያዎች ያግኙ። ለመመዝገብ፣ የአድራሻ መረጃዎን ያስገቡ። (ሁለቱንም የኢሜል እና የጽሑፍ መልዕክቶች ለመቀበል ሁለት ጊዜ መመዝገብ ያስፈልግዎታል።)

በአሁኑ ጊዜ የተመዘገቡ ሰዎች

ምርጫዎችዎን ለማስተዳደር፣ ኢሜልዎን ወይም የሞባይል ቁጥርዎን ያስገቡ


Translation disclaimer

expand_less